Friday, March 31, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአካባቢ ጥበቃን መሠረት ያደረገ የፈጠራ ሥራን የሚደግፍ ፕሮጀክት ሥራ ጀመረ

የአካባቢ ጥበቃን መሠረት ያደረገ የፈጠራ ሥራን የሚደግፍ ፕሮጀክት ሥራ ጀመረ

ቀን:

የአካባቢ ጥበቃን መሠረት ያደረገ የሥራ ዕድል የመፍጠር ዝንባሌ ያላቸውን ወጣት የሥራ ፈጣሪዎችን መደገፍ ዓላማው ያደረገ ፕሮጀክት ሥራ ጀመረ፡፡

አይኪያ ፋውንዴሽን የተሰኘው የስዊዲን ግብረሰናይ ድርጅት የአንድ ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግለት ይህ ፕሮጀክት፣ ሪች ፎር ቼንጅ በተባለ ድርጅት ለ18 ወራት ያህል አካባቢ ጥበቃን መሠረት ያደረገ የንግድ ፈጠራ ሥራ የሚያቀርቡ ወጣቶችን የሚደግፍ  እንደሆነ ተገልጿል፡፡       

መጋቢት 6 ቀን 2014 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ ሆቴል ይፋ በተደረገው የፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ ወቅት የተገኙት የሪች ፎር ቼንጅ በኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅ / ለምለም ስንቅነህ እንደተናገሩት፣ ሪች ፎር ቼንጅ በኢትዮጵያ የሚተገብረውን አረንጓዴ ሥራ ፈጣሪነት ፕሮጀከት ለመደገፍና ለማዳበር አይኪያ ፋውንዴሽን የአንድ ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አድርጎላቸዋል።

‹‹ካታላይዚንግ ግሪን ቢዝነስ ኢን ኢትዮጵያ›› በሚል ስያሜ ወደ ሥራ የገባው ይህ ፕሮጀክት ዓላማው፣ ሰፊ ቁጥር የሚሸፍነውን የኅብረተሰብ ክፍል በተለይም ወጣቱ አካባቢን የማይጎዳ ይዘት ያለው ሥራ እንዴት መፍጠር ይችላል? የሚለው ላይ አተኩሮ የሚሠራ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

የሪች ፎር ቼንጅ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሶፊያ ብራይትሆልትዝ በበኩላቸው፣ ድርጅታቸው በዋናነት ወጣት የሥራ ፈጣሪዎችን ማዕከል ያደረገ ሥራ ለማከናወን ሲያቅድ እንደ ዋነኛ ምክንያት የወሰደው ወጣት የሥራ ፈጣሪዎች ከማንኛውም የኅብተረተሰብ ክፍል ይልቅ፣ በዙሪያቸው ያለውን ችግር በመረዳት መፍትሔ ለማምጣት የሚስችል አቅም ባለቤት መሆናቸውን በማመን እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ሥራ ፈጣሪዎች ሐሳባቸውን ወደ ተግባር በመቀየር ሒደት ውስጥ የተለያዩ ችግሮች እንደሚገጥማቸው ያስታወቁት ሥራ አስፈጻሚዋ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚስተዋለው የኢንቨስትመንት ካፒታል እጥረት አንስቶ የአቅም ግንባታና የሥራ ላይ ትስስር እንደሚያስፈልጋቸው አስረድተዋል፡፡ ሪች ፎር ቼንጅም ይህንን መሰል ድጋፍ ለማቅረብ መነሳቱን አክለው ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ሁለት ዓበይት ጉዳዮችን ለማሳካት ያቀደ ሲሆን፣ አንደኛው በከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች እንዴት የአካባቢ ጥበቃ (አረንጓዴ) ሥራ ዕድል ፈጠራ ባለቤት መሆን ይችላሉ የሚለውን የሚደግፍ መሆኑ ተልክቷል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ገና ያቆጠቆጡ ጅምር የሥራ ፈጠራዎችን በመደገፍ እንዴት የተሻለ የፈጠራ አገልግሎትን ማቅረብ ይቻላል?  የሚለው ሌላው የድጋፍ አካል ነው፡፡

በሙከራ ደረጃ ለ18 ወራት በሚተገበረው ፕሮጀክት ውስጥ ለሚሳተፉ ፈቃደኛ ወጣቶች ጥሪ የሚቀርብ ሲሆን፣ ከዚያ በማስከተል ለተመረጡ ተማሪዎች የአቅም ግንባታና የፋይናንስ ድጋፎች ድርጅቱ እንዲያገኙ እንደሚያደርግ ፕሮጀክቱ ይፋ በተደረገበት መድረክ ተገልጿል፡፡ ሪች ፎር ቼንጅ ይህንን ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣ ከቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ፣  ከፌዴራል የቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት፣ እንዲሁም የግል የቴክኒክና ሙያ ትምህርት አቅራቢ ከሆነው አዲስ ኮሌጅ ለተወጣጡ 360 ወጣቶች ሥልጠና በመስጠት ሥራውን የሚጀምር እንደሆነ ወ/ሮ ለምለም ተናግረዋል፡፡

ከላይ በተጠቀሱት የትምህርት ተቋማት የሚገኙና ተመርቀው ለመውጣት በዝግጅት ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን በባለሙያዎች በማሠልጠን የሚጀምረው ይህ ፕሮጀክት፣ የሚሰጣቸውን ሥልጠና ተከትሎ ጥሩ የሆኑና ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የተገናኙ የሥራ ፈጠራዎችን የሚያቀርቡ 60 ተማሪዎችን በገንዘብ ይደግፋል ተብሏል፡፡

ላለፉት ሰባት ዓመታት ከ230 በላይ የሥራ ፈጣሪዎች ሲደገፉ እንደነበር የተናገሩት ወ/ሮ ለምለም፣ በዚህ ፕሮጀክት በመጨረሻ ተመርጠው የሚቀሩትም ሆኑ ጥሪ ቀርቦላቸው ወደ ሥልጠና የሚገቡት ተማሪዎች የሚያገኙት ሥልጠና በራሳቸው አቅም መሥራት እንዲችሉ የሚረዳና ግንዛቤ የሚጨብጡበት ይሆናል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተወግዘው የነበሩ ሦስቱ ሊቀጳጳሳትና 20 ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ውግዘት ተነሳ

_ቀሪዎቹ ሦስት ህገወጥ ተሿሚዎች የመጨረሻ እድል ተሰጥቷቸዋል ​ ጥር 14...

በሕወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶና በሂደት ላይ የነበረው የወንጀል ክስ ተቋረጠ

በቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤ,(ዶ/ር)ና ባለፈው ሳምንት በተሾሙት...

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...