Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትከዕድሜ ማጭበርበር መነጠል የተሳነው የታዳጊዎች አትሊቲክስ ሻምፒዮና

ከዕድሜ ማጭበርበር መነጠል የተሳነው የታዳጊዎች አትሊቲክስ ሻምፒዮና

ቀን:

የዓለም አትሌቲክስ፣ በዓመት ውስጥ የአዋቂ ውድድሮች ጨምሮ በርካታ የአትሌቲክስ ሻምፒዮናዎችን በተለያዩ አገሮች ያከናውናል፡፡ ሻምፒዮናዎቹ በርቀት፣ ዕድሜና በተለያዩ የአትሌቲክስ ዓይነቶች ተለይተው ይከናወናሉ፡፡ የዓለም አትሌቲክስ ማኅበር አባል የሆኑ አገሮችም በየአገራቸው የማጣሪያ ውድድሮችን አከናውነው፣ ብቁ የሆኑ አትሌቶችን መርጠው እንዲያቀርቡ ይደረጋል፡፡

በዚህም መሠረት የአትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሚያከናውናቸው ዓመታዊ የአትሌቲክስ ማጣሪያ ውድድሮች አንዱ የሆነው ከ18 እና ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮን በአሰላ ከተማ አከናውኗል፡፡

ከየካቲት 28 እስከ መጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ.ም. በተከናወነው በዚህ ውድድር ክለቦች፣ ክልሎች፣ የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ተቋማት በተለያዩ ርቀቶች ላይ ተካፍለዋል፡፡ ለአሥረኛ ጊዜ የተከናወነው ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮናና ለሦስተኛ ጊዜ የተከናወነው ከ18 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሳምንቱ የማኅበራዊ ሚዲያ አጀንዳ ሆኖ ስንብቷል፡፡

ለዓመታት ሲከናወን የሰነበተው አትሌቲክስ ሻምፒዮናው ‹‹የታዳጊዎች ሻምፒዮና›› የሚል ስያሜ ቢኖረውም፣ በዕድሜ ጠና ጠና ባሉ አትሌቶች መከናወኑ በርካቶችን ሲያነጋግር ቆይቷል፡፡ ሻምፒዮናው ተተኪ አትሎቶችን ለማፍራትና በታንዛንያ ዳሬሰላም ለሚከናወነው የምሥራቅ አፍሪካ ታዳጊና ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶችን ለመምረጥ ግብ ያለው እንደሆነ ቢገለጽም፣ ዓላማውና ሻምፒዮናው ግን ለየቅል መሆናቸውን በርካቶችን አስገርሟል፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ሻምፒዮናው ከመጀመሩ አስቀድሞ ‹‹በዕድሜ መወዳደር ለአትሌቲክስ ዕድገት ይጠቅማል፣ ታዳጊና ወጣት አትሌቶች የነገ ወርቆቻችን ናቸው፣ እንዲሁም በውድድር ወቅት ዕድሜ ማጭበርበር ወንጀል ነው፤›› የሚል መፈክር ይዞ ቢወጣም የሰማው ያለ አይመስልም፡፡

በተለያዩ ርቀቶች ላይ የተሳተፉ አትሌቶች ገጽታና ተክለ ሰውነት በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ሳይሆን፣ ሊያወዳድሩ የመጡ ወላጆች መምሰላቸው የበርካቶች አግራሞትን ጭሯል፡፡ በዚህም በሻምፒዮና ላይ ሲሳተፉ የነበሩትን አትሌቶች ፎቶ የተመለከተ ሁሉ ‹‹ጉድ›› ሲል ውሏል፡፡ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲዘዋወር የዋለውን የተሳታፊ አትሌቶች ፎቶ አማካይነት አወዳዳሪው አካል ምን እየሠራ ነው የሚል ጥያቄን አስነስቶ ነበር፡፡

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተሳትፎና የውድድር ዳይሬክተር አቶ አስፋው ዳኜ፣ አስተያየት ከሆነ፣ ያለ ዕድሜያቸው የተወዳደሩ አትሌቶች በብሔራዊ ቡድን ውስጥ እንደማይካተቱ አስረድተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ያለ ዕድሚያቸው የሚሳተፉ አትሌቶችን መቆጣጠር የሚገባቸው ክልሎች፣ የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም  ክለቦችና የስፖርት ማዕከላት እንደሆኑ ያብራራሉ፡፡

የታዳጊ ወጣቶች ሻምፒዮና የነገ ተተኪ አትሌቶችን ለማግኘት ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ይታመናል፡፡ በየትኛውም የስፖርት ዘርፍ ውጤታማ ለመሆን በታዲጊዎች ላይ መሥራት አትራፊ ያደርጋል፡፡ በዓለም ላይ የሚገኙ ግዙፍ የስፖርት ተቋማት የነገ ውጤታቸው የዛሬ ታዳጊዎች ላይ መሠረት ያደረገ ነው፡፡

ምንም እንኳን ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ዕድሜ ያጭበረበሩ አትሌቶችን በብሔራዊ ቡድን ውስጥ እንደማይካተቱ ቢገልጽም፣ በውድድሩ ላይ በመካፈላቸውና የነገ ተተኪዎችን ዕድል መቀማታቸውን የሚያነሱ አሉ፡፡

ከዚያም ባሻገር ሻምፒዮናው በተሰናዳ ቁጥር የዕድሜ ማጭበርበሩ ጉዳይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱና አሳሳቢ እንደሆነ የሚያነሱ አሉ፡፡ በሻምፒዮናው የሚካፈሉት ክለቦችና የከተማ አስተዳደሮች ኃላፊነታቸውን አለመወጣታቸው፣ የነገ ተተኪ አትሌቶችን የማሳጣት ዕድሉ ሰፊ እንደሆነ የሚያስረዱ አሉ፡፡

ሻምፒዮናው በመጣ ቁጥር የዕድሜ ጉዳይ ማነጋገሪያ ሆኖ ሲያልፍ የተሳታፊዎች ግዴታ ነው በሚል በቸልተኝነት የሚያልፈው ፌዴሬሽኑም ኃላፊነቱም መወጣት እንዳለበት የሚያነሱ አሉ፡፡

ክለቦች፣ የከተማ አስዳደሮች፣ አካዴሚዎች እንዲሁም ክልሎች ችግሩን ለመፍታት የአንበሳውን ድርሻ መውሰድ እንደሚገባቸው ይታመናል፡፡ በመሆኑም ፌዴሬሽኑ በሻምፒዮናው ተገቢ ባልሆነ ዕድሜ የተካፈሉ አትሌቶችን በጥንቃቄ እንደሚለይና ለብሔራዊ ቡድኑ እንደሚመርጥ አስታውቋል፡፡ 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹በየቦታው ምርት እየገዙ የሚያከማቹ ከበርቴ ገበሬዎች ተፈጥረዋል››

አቶ ኡስማን ስሩር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር...

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...