Sunday, April 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየትግራይ ጊዜያዊ አስተዳዳር አባላት መንግሥትንና ጊዜያዊ መስተዳድሩን ከሰሱ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳዳር አባላት መንግሥትንና ጊዜያዊ መስተዳድሩን ከሰሱ

ቀን:

የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳዳር ሲያዋቅር፣ ሹመት ተሰጥቷቸው በተለያዩ ደረጃዎች ሲያገለግሉ የነበሩ 82 የጊዜያዊ የአስተዳደሩ አባላት፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትና በትግራይ ክልል ጊዜያዊ መስተዳድር ላይ የ23.3 ሚሊዮን ብር ክስ መሠረቱ፡፡

አባላቱ በመንግሥት ላይ ክስ የመሠረቱት፣ የመከላከያ ሠራዊት ከትግራይ ክልል ከወጣ በኋላ ከሥራ፣ ቤተሰብና ቤት ንብረታቸው በማፈናቀል፣ ጎዳና ላይ እንደጣላቸውና ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም እንዲያጡ ስላደረጋቸው መሆኑን ማክሰኞ መጋቢት 6 ቀን 2014 ዓ.ም. በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሠረቱት የፍታብሔር ክስ ዝርዝር ላይ አስፍረዋል፡፡ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ ከቀበሌ እስከ ክልል በመንግሥት ሥራና በፓርቲ ውስጥ ሲሳተፉ እንደነበረ በክሳቸው፣ ላይ ያሰፈሩት 82 ከሳሾች መንግሥት ችላ ስላላቸው ለተጨማሪ ወጪና ኪሳራ መዳረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡

የክሱ ዝርዝር እንደሚያስረዳው ከሳሾቹ የመከላከያ ሠራዊት ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ከትግራይ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ በክልሉ ወደ መደበኛ እስቅስቃሴ እስዲመለስ ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡ የጊዜያዊ አስተዳደሩ አባላት ከፌዴራል መንግሥቱ ጋር መተባበር ‹‹በባንዳነት›› የሚያስፈርጅበትና ‹‹የሕይወት መስዋዕትነት የሚያስከፍልበት ጊዜ ውስጥ መሥራታቸውን፣ የሕወሓት ኃይሎች 50 የጊዜያዊ አስተዳደሩ አባላትን መግደላቸውን በክስ ዝርዝሩ ላይ በመጥቀስ አስረድተዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከሳሾቹ ‹‹ጊዜያዊ መስተዳድሩ ሕግ ባስቀመጠው አግባብ ሳይፈርስና ከሳሾችም የፌዴራሉ መንግሥት ከትግራይ ለመልቀቅ ውሳኔ ስለመተላለፉ ሳይነገረንና ሳንዘጋጅ ወደ አዲስ አበባ እንድንመጣ ተደርገናል፤›› ብለዋል፡፡

‹‹አዲስ አበባ ካመጡን በኋላ ያለ ምንም ሕጋዊና በቂ ምክንያት ጊዜያዊ መስተዳድሩ ፈርሷል፤›› በማለት ጎዳና ላይ በመጣል ሕግን በተቃረነና አድሎዓዊ በሆነ አኳኋን ለመረጡት ሰው ደመወዝና ጥቅማጥቅም በመክፈል፣ ከሳሾችን ግን ከሥራችንና ከደመወዛችን በማፈናቀል፣ ጎዳና ላይ በመጣል ለልዩ ልዩ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ችግሮች ዳርገውናል፤›› የሚል ወቀሳም በክስ ዝርዝሩ ላይ ሰፍሯል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ እንደ አዲስ ኑሮ ለመመሥረት መገደዳቸውን የገለጹት ከሳሾቹ፣ እያንዳንዳቸው ለቤት ኪራይ በወር ሰባት ሺሕ ብር እንደሚያወጡና ለወጪና ኪሳራ መዳረጋቸውን በክሳቸው ላይ ገልጸዋል፡፡

ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ሕወሓት በመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመክፈት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ ተግባር በመፈጸሙ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፌደራሉ መንግሥት ጣልቃ በመግባት ክልሉ በጊዜያዊ አስተዳደር እንዲመራ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤትም ከኅዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም. አንስቶ ተፈጻሚ የሚሆንና የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር አወቃቀር፣ ሥልጣንና ተግባር የሚደነግግ ደንብ ካፀደቀ በኋላ በሥራ ላይ ማዋሉን በክሱ ላይ ጠቅሰዋል፡፡                                                        

የጊዜያዊ አስተዳደር አባላቱ ደመወዝ ስላልተከፈላቸው ልጆችና ቤተሰቦቻቸው ለችግር እንደተጋለጡ በመጥቀስ፣ ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም እንዲከፈላቸውና መንግሥት ወደ ተመሳሳይ የመንግሥት ሥራ እንዲመድባቸው ክስ አቅርበዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እያንዳንዳቸው አዲስ አበባ ውስጥ ስምንት ወራት ለቆዩበት እያንዳንዱ ቀን ውሎ አበል፣ የስምንት ወርና የመጪው ወራት የቤት ኪራይ ዋጋ እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...