Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየቀድሞ ሚኒስትሮችን ጨምሮ  አምስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ለመከላከያ ምስክርነት በፍርድ ቤት ተጠሩ

የቀድሞ ሚኒስትሮችን ጨምሮ  አምስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ለመከላከያ ምስክርነት በፍርድ ቤት ተጠሩ

ቀን:

አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ምስክርነታቸውን በበይነ-መረብ እንዲሰጡ ጠየቁ

የቀድሞ ብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው በመከላከያ ምስክርነት የተቆጠሩት የቀድሞ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትርና አሁን ላይ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) እና የአዲስ አበባ ከተማ የቀድሞ ከንቲባ ድሪባ ኩማ (አምባሳደር) ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ መጋቢት 8 ቀን 2014 ዓ.ም. ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡

ትዕዛዙን የሰጠው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ሲሆን፣ ከመኩሪያ (ዶ/ር) እና አቶ ድሪባ (አምባሳደር) በተጨማሪም፣ የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በመከላከያ ምስክርነት ስለተቆጠሩ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡

ባለሥልጣናቱን የቀድሞ የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ በመከላከያ ምስክርነት የቆጠራቸው፣ ሜቴክ ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ገዝቷቸዋል ከተባሉት ሁለት መርከቦች ጋር በተያያዘ ነው፡፡

መርከቦቹ ከ28 ዓመታት በላይ ያገለገሉና የአገልግሎታቸውን ዘመን እንዳጠናቀቁ እየታወቀ በ60 ሚሊዮን ብር በመግዛት፣ በከፍተኛ ወጪ ታድሰው ወደ ሥራ እንዲሰማሩ በመደረጋቸው በመንግሥትና ሕዝብ ላይ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ እንዲደርስ መደረጉን ዝርዝር ዓቃቤ ሕግ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

በመከላከያነት የተጠሩት ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ባለሥልጣናት ፈርድቤት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ የተሰጠው ከመርከቦቹ ጋር በተያያዘ ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ ነው፡፡ ምስክሮቹ ከመጋቢት 21 ቀን 2014 ዓ.ም. በፊት ጥሪው እንደደረሳቸውና ስለመቅረባቸው ለፍርድ ቤት ያሳውቃሉ፡፡

ከትራክተሮች ግዢ ጋር በተያያዘ በመከላከያ ምስክርነት የተቆጠሩት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ በተደጋጋሚ ጥሪ ተደርጎላቸው ባለመቅረባቸው ታስረው እንዲቀርቡ ትዕዛዝ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ ነገር ግን አቶ ኃይለ ማርያም መጥሪያው እንዳልደረሳቸውና በማኅበራዊ ትስስር ገጽ መስማታቸውን አስረድተው ለፍርድ ቤቱ ደብዳቤ ጽፈዋል፡፡ በማንኛውም ጊዜ ፍርድብ ቤት ለመቅረብ ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልጸው፣ በአሁኑ ጊዜ ለሥራ ጉዳይ በውጭ አገር መሆናቸውን በመጠቆም፣ ምስክርነታቸውን በበይነ መረብ እንዲሰጡ እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል፡፡

አቶ ኃይለ ማርያም በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት ባለመቅረባቸው የሮማንና ኃይለ ማርያምና ሮማን ፋውንዴሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ለምን መጥሪያቸውን እንዳላደረሱ ቀርበው እንዲያስረዱ ፍርድ ቤት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት፣ መጥሪያውን በኢሜይል እንደላኩላቸው መገለጹ ይታወሳል፡፡

አቶ ኃይለ ማርያም ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡትን ጥያቄ፣ የሜጀር ጀነራል ክንፈ ጠበቆችም ሆኑ ዓቃቤ ሕግ ተቃውሞ እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡ ሌላው በተመሳሳይ በመከላከያነት የተቆጠሩት የቀድሞ መከላከያና የትራንስፖርት ሚኒስትር አቶ ሲራጅ ፈጌሳም እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡

በተጨማሪም ኮሎኔል አዜብ ታደሰና ኮሎኔል ሸጋው ሙሉጌታን ጨምሮ ሌሎችም በመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ ታዘው ያልቀረቡ ምስክሮችን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከዓቃቤ ሕግ ጋር በመሆን አድራሻቸውን አፈላልጎ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ አቶ ኃይለ ማርያም ባቀረቡት ጥያቄ ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ለሰኞ መጋቢት 12 ቀን 2014 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...