Wednesday, March 29, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን የሚያግዙ የፈጠራ ሥራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ተገለጸ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለየ መልኩ የአግሮ ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ለማጠናከር በሚል የተቋቋሙት ኢንዱስትሪ ፓርኮችን የሚያግዙ የፈጠራና የምርት ሥራዎች  ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአዳዲስ የሥራ ዕድሎችና ፕሮጀክቶች ዳይሬክተር / ዓለምፀሐይ ደርሶልኝ ለሪፖርተር እንዳስረዱት፣ ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሚያስገኙትን የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመደገፍ ከተወጠኑት ጉዳዮች ውስጥ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በግብርና ሙያ የሚማሩና የሚመረቁ ተማሪዎች ለአግሮ ኢንዱስትሪዎች አዳዲስ ሐሳቦችን እንዲያፈልቁ የሚደረገው ጥረት ይጠቀሳል፡፡

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከመንግሥት፣ የግል እንዲሁም የልማት አጋሮች ጋር ኅብረት መፍጠር ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለምርታማነት እንዲሁም ለወጣቶች አዳዲስ የሥራ ዕድል ፈጠራ የሚያደርገው እንቅስቃሴ የጋራ ጥረትን እንደሚጠይቅ ዳይሬክተሯ አስታውቀዋል፡፡

ከዩኒቨርሲቲ የሚወጡ ተማሪዎች ሁሉም ሥራ ፈጣሪ፣ ሁሉም ተቀጣሪ አይሆኑም ያሉት / ዓለምፀሐይ፣ ለቅጥር የሚያበቃ ክህሎት (Employability skill) እንዲሁም የሥራ ዕድል ፈጠራ ክህሎት እንዲያዳብሩ ሥልጠናዎች እየተሰጡ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

በሐዋሳ፣ አዳማ፣ ደብረማርቆስና ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የአግሮ ኢንዱስትሪ የሥራ ፈጠራ ውድድር መጋቢት 08 ቀን 2014 ዓ.ም. በስካይ ላይት ሆቴል ተካሂዷል፡፡  

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአዳዲስ ሥራ ዕድል ፈጠራና ፕሮጀክቶች ዳይሬክቶሬትና አጋር አካላት ትብብር በአራት በዩኒቨርሲቲዎች መካከል ሲካሄድ የቆየው ይህ ውድድር አምስት በአግሮ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሻለሥራ ፈጠራ ሐሳብና ምርት ያቀረቡ ወጣቶችን በመለየትና በመሸለም ተጠናቋል፡፡

በመሰል የፈጠራ ውድድር የተሳተፉ ሰዎች ሁሉም የራሳቸው ድርጅት ባያቋቁሙ አንኳን አገልግሎት እየሰጡ በሚገኙት የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ በሚከፈቱ ኢንዱስትሪዎች ሐሳቦቻቸውን በማቅረብ ፓርኮቹ ሥራቸውን የሚያቀርቡበትን ሁኔታ መደገፍ እንደሚቻል ዳይሬክተሯ አስታውቀዋል፡፡

በዚህ የአግሮ ኢንዱስትሪ የሥራ ፈጠራ ውድድር ያሸነፉት አምስቱ ቡድኖች እያንዳንዳቸው ብር 230 ሺሕ ብር የሥራ ማስጀመሪያ ገንዘብናምስክር ወረቀት በዕለቱ ተሰጥቷቸዋል፡፡

በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከፍተኛ የፕሮግራም ኃላፊ የሆኑት አቶ ሮቤል ሳምሶን እንደተናገሩት፣ የግብርናና የንግድ ሐሳብ ውድድር በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በተለይም ግብርናን መሠረት ያደረገ የፈጠራ ሐሳብ የሚሠሩ ተማሪዎች ሥልጠና አግኝተው ተወዳድረው በመጨረሻም የተሸለሙበት መርሐ ግብር በርካታ ተማሪዎችን የሚያነቃቃና የሚያዘጋጅ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ወጣቶች ከዩኒቨርሲቲ ተመርቀው ከወጡ በኋላ ለ18 ወራት ያህል ሥራ ፍለጋ ውስጥ ይቆያሉ፡፡ ይህንን ለመቅረፍ ተማሪዎቹ ገና ከዩኒቨርሲቲ ተመርቀው ሳይወጡ ዝግጅት ማድረጋቸው ተመርቀው ሲወጡ ከእነሱም አልፈው ለሌሎች ወገኖች የሥራ ዕድል የሚፈጥሩበት አጋጣሚ እንደሚፈጥር አቶ ሮቤል አስታውቀዋል፡፡                               

አሸናፊ ተማሪዎች ካቀረቧቸው የአሸናፊነት የአግሮ ኢንዱስትሪ የፈጠራሳቦችና ሥራዎች መካከል ከተረፈ ምርት የተሠራ ማዳበሪያ፣ ከቀርከሃ የተሠራ ብስክሌት፣ ከውኃ አካላት የተዘጋጁ የእንስሳት መኖ፣ ከቡና ቅጠል በዘመናዊ መልክ የተመረተ ሻይ ቅጠል እንዲሁም የኤክስፖርት ደረጃ ሊያሟላ የሚችል አገር በቀል ምግቦች ይጠቀሳሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች