Thursday, February 22, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ቡና ባንክ ከምሥረታው ጀምሮ የተጠቀመበትን መለያ ሎጎ ቀየረ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ከተመሠረተ 12 ዓመታትን ያስቆጠረው ቡና ባንክ ከዚህ ቀደም ሲጠቀምበት የቆየው መለያ ምልክት በቀላሉ ለመታወስ አስቸጋሪና ለመረዳትም ውስብስብ በመሆኑ አዲስ የብራንድ ዓርማና ቀለም ይፋ አድርጓል፡፡

ባንኩ ከዚህ ቀደም የነበረውን ዓርማን ከመቀየሩ በፊት ከባለአክሲዮኖቹ፣ ከደንበኞቹ፣ ከሠራተኞቹና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት አስተያየት መሰብሰቡን ያስታወቀ ሲሆን፣ አዲሱ ዓርማ ለማንኛውም አጠቃቀም ምቹ፣ በኅብረተሰቡ ዘንድም በቀላሉ መታወስ እንዲችል ተደርጎ የተቀረጸ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ቤሪ አድቨርታይዚንግ በተባለ የግል ተቋም የተዘጋጀውን አዲሱ የባንኩ ብራድ ዓርማና ቀለም ሠርቶ ለማጠናቀቅ አንድ ዓመት ከመንፈቅ መውሰዱን፣ ባንኩ ረቡዕ መጋቢት 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ዓርማውን ይፋ ባደረገበት ወቅት ተገልጿል፡፡ አዲሱ የብራንድ ዓርማና ቀለም የባንኩን ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች እንዲወክል ተደርጎ መዘጋጀቱም ተነግሯል፡፡

ከዓይን፣ አድማስና ክብ ቅርጽ ምስሎች የተዋቀረው አዲሱ የቡና ባንክ ብራንድ ዓርማ የሎጎው የታችኛው ክፍል  ላይ የተቀመጠው የዓይን ቅርጽ መንቃትን ይወክላል ተብሏል፡፡ በሎጎው መካከለኛ ክፍል ላይ ያለው የአድማስ ቅርፅ ደግሞ የአዲስ ቀን ጅማሮና የብሩህ ተስፋ መገለጫ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የባንኩ ሎጎ ሙሉ ቅርጽ ክብ ሲሆን ይኼም ‹‹ብዙ ሆነን እንደ አንድ የምንሰባሰብበት፣ የምንመክርበት፣ የምንረዳዳበት፣ ክፉና ደግን የምንካፈልበት፣ ከትውልድ ትውልድ የተቀባበልነውን ትውፊት፣ ባህልና ልማዳችንን የሚወክል ምልክት ነው፤›› ሲሉ የቤሪ አድቨርታይዚንግ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መላኩ ባህሩ ተናግረዋል፡፡

ከአንድ ዓመት በፊት ‹‹ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ›› የሚለውን ስያሜ ‹‹ቡና ባንክ›› ወደሚል መጠሪያ የቀየረው ባንኩ በ12 ዓመት ጉዞው 1.8 ሚሊዮን ደንበኞችን እንዳፈራ አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች