Saturday, December 3, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናበእስር ላይ በሚገኙት የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላት ላይ ተጨማሪ የምርመራ ቀን...

  በእስር ላይ በሚገኙት የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላት ላይ ተጨማሪ የምርመራ ቀን ተፈቀደ

  ቀን:

  የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የቀድሞ አባላትና ኃላፊዎች የነበሩና በአፋር ክልል በእስር ላይ የሚገኙ ግለሰቦች፣ በክልሉ በሚገኝ አዋሽ ሰባት በሚባለው ፍርድ ቤት ቀርበው ለ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንደተፈቀደ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ፡፡

  የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንዳረጋገጡት፣ ታሳሪዎቹ በአፋር ክልል አዋሽ ሰባት በተባለው አካባቢ ፍርድ ቤት ከቀረቡ በኋላ፣ ፖሊስ ምርመራውን አለማጠናቀቁን አስረድቶ ለተጨማሪ ምርመራ 14 ቀናት እንዲፈቀድለት በመጠየቁ፣ ፍርድ ቤቱም የተጠየቀውን ጊዜ በመፍቀድ ታስረው እንዲቆዩ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ የታሳሪዎቹን ጉዳይ በተመለከተ ኮሚሽኑ ክትትል እያደረገ መሆኑን የገለጹት ዳንኤል (ዶ/ር)፣ ጉዳዩ ለምን በአፋር ክልል ፍርድ ቤት እንደቀረበና ለእስሩ ምክንያት የሆኑትን ጉዳዮች በተመለከተ ግልጽ የሆነ መረጃ አለመኖሩን አስታውቀዋል፡፡

  በእስር ላይ የሚገኙትን የጊዜያዊ አስተዳደሩ የቀድሞ አባላትና ኃላፊዎች ብዛትና ስም ዝርዝር ያልገለጹት ዋና ኮሚሽነሩ፣ ኢሰመኮ ስለ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር ክትትሉን የሚቀጥል መሆኑን አስረድተዋል፡፡

  ኢሰመኮ የታሳሪዎቹን ብዛት ባይገልጽም ሪፖርተር ያነጋገራቸው ለታሳሪቹ ቅርበት ያላቸው ግለሰቦች 13 ጊዜያዊ አስተዳደር የቀድሞ አባላትና ኃላፊዎች እንዲሁም አንድ ከታሳሪዎቹ ጋር የተያዘ ግለሰብ በአፋር ክልል ዞን አምስት በርታ የተባለ እስር ቤት ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

  በጊዜያዊ አስተዳደሩ የቀድሞ የመቀሌ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ከበደ አሰፋ፣ ታሳሪዎቹ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. በመከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ላይ ከሕወሓት አመራሮች ጋር ተባብረዋል የሚል በሽብር ወንጀል መጠርጠራቸውን ከታሳሪዎቹ መስማታቸውን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ ከታሳሪዎቹ መካከል አሥሩን አስጠልለው የነበሩትና ታሳሪቹን ማነጋጋራቸውን ሪፖርተር የገለጹት የሄዋኗ ራዕይ የበጎ አድራጎት ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ምፅላል ኃይለ ሥላሌም ይኼንኑ አረጋግጠዋል፡፡

  ግለሰቦቹ እንደገለጹት የታሳሪዎቹ ጉዳይ የቀረበለት የወረዳ ፍርድ ቤት ታሳሪዎቹ የተጠረጠሩበትን የሽብር ወንጀል የመመልከት ሥልጣን ያለው የፌዴራል ፍርድ ቤት እንደሆነና፣ የሽብር ጉዳዮችን ለመመልከት ሥልጣን እንደሌለው አስታውቋል፡፡ ይሁንና የጊዜ ቀጠሮ ለመስጠት ከፌዴራል ፍርድ ቤቶች ውክልና ስላለው ተጠርጣሪዎቹን ፍርድ ቤት ያቀረበው የፌዴራል ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል፡፡

  ተጠርጣሪዎቹም ፍርድ ቤቱ ይኼንን ጉዳይ የማየት ሥልጣን እንደሌለው መናገራቸውን የገለጹት አቶ ከበደ፣ ለእስር የዳረጋቸው ጉዳይ የሚያስጠይቃቸው ከሆነም መጠየቅ ያለባቸው በተያዙበትና በሚኖሩበት አዲስ አበባ ከተማ እንደሆነ ማስረዳታቸውን ተናግረዋል፡፡

  በአፋር ክልል በእስር ላይ ከሚገኙት የጊዜያዊ አስተዳደሩ የቀድሞ ኃላፊዎች መካከል፣ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ነበሩት አቶ አበራ ንጉሥ፣ የደቡባዊ ምሥራቅ ዞን አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ንጉሥ ካሳ፣ የትግራይ ቴሌቪዥን ምክትል ዳይሬክተር የነበረው ጋዜጠኛ ይስሃቅ ወልዳይ እንዲሁም የትግራይ ብልፅግና አመራር የነበሩት አቶ ሓጎስ ወልደኪዳን እንደሚገኙበት አቶ ከበደ ገልጸዋል፡፡

  በየካቲት መጨረሻና በመጋቢት ወራት የመጀመሪያ ቀናት ላይ ለእስር ከተዳረጉት ግለሰቦች  ውስጥ አሥሩ በቁጥጥር ስር የዋሉት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ከሚገኘው የሄዋኗ ራዕይ የበጎ አድራጎት ማኅበር እንደሆነና ቀሪዎቹ ከተያዩ ቦታዎች መወሰዳቸው ታውቋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...