Saturday, June 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናፌዴራልም ሆነ ክልሎች በታጣቂዎች እየተፈጸሙ ያሉ ጥቃቶችን በአፋጣኝ እንዲያስቆሙ ጥሪ ቀረበ

ፌዴራልም ሆነ ክልሎች በታጣቂዎች እየተፈጸሙ ያሉ ጥቃቶችን በአፋጣኝ እንዲያስቆሙ ጥሪ ቀረበ

ቀን:

የዜጎችን በሕይወት የመኖርና የአካል ደኅንነት መብት በጣሰ መልኩ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በታጣቂዎች እየተፈጸሙ ያሉ ጥቃቶችን፣ የፌዴራል መንግሥትም ሆነ ክልሎች በአፋጣኝ እንዲያስቆሙ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ጥሪ አቀረበ፡፡

ጉባዔው አስቸኳይ ጉዳይ የሚሹ አገራዊ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችን በተመለከተ ትናንት መጋቢት 13 ቀን 2014 ዓ.ም ጋዜጣዊ መግለጫ አውጥቷል፡፡

ለአብነት በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን በተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች በተደጋጋሚ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሲፈጸሙ እንደቆዩ ያስታወቀው ኢሰመጉ፣ ባሳለፍነው ሳምንት አርብ በአምቦ ወረዳ ኢላም ቀበሌ የሚገኙ ሁለት አዛውንቶች በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ በሸኔ ታጣቂዎች መገደላቸውንበአካባቢው ከሚገኙ የመረጃ ምንጮች አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

ኢሰመጉ በተጨማሪም በምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ አላጌ ቀበሌ ውስጥ መርቲ ፋብሪካ በተባለው አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት በርካታ ወጣቶች እንደተገደሉ፣ በተጨማሪም ቁጥራቸው የበዛ ወጣቶች እንዲሁ ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታል ውስጥ የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

 በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል እንዲሁ በተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች እየተፈጸሙ ያሉ ግድያዎች፣ የአካል ጉዳት፣ ማፈናቀልና ንብረት ማውደም አሁንም ተባብሶ መቀጠሉ አሳስቦኛል ያለው ኢሰመጉ፣ በደቡብ ክልል ጉራፈርዳ ወረዳ ልዩ ስሙ አርጌ ብርሃን በተባለ ሥፍራ 18 ዓመት ወጣት በአሰቃቂ ሁኔታ ማንነታቸው ባልታወቁ ቡድኖች ከሰሞኑ መገደሉን ጠቅሷል፡፡

በደቡብ ክልል በአማሮ ልዩ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ ቀበሌዎች በሚኖሩ ነዋሪዎች ላይ የሸኔ ታጣቂዎች በተለያዩ ጊዜያቶች በሚፈጽሙት ጥቃት በርካታ ሰዎችይወታቸውን እንዳጡ፣ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው እንዲሁም ከቤት ንብረታቸው እንደተፈናቀሉ በጉባዔው መግለጫ ተዳሷል፡፡

በአካባቢው ያለው ችግር በዚህ ወቅትም ተባብሶ ከዲላ ወደ አማሮ ከተሞች የሚወስደው መንገድ ከተዘጋ ከወር በላይ እንደሆነው፣ እንዲሁም  ከቡሌ ሆራ ወደ አማሮ ኬሌ የሚወሰደው መንገድም በሸኔ ታጣቂዎች መዘጋቱን ኢሰመጉ እንዳረጋገጠ አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን አማሮ፣ ቡርጂ፣ አሌ ልዩ ወረዳዎችና የቀድሞ የጉማይዴ ወረዳዎች ላይ ከማፈናቀል እስከ ግድያ የሚደርሱ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ሲፈጸሙ ቆይተዋል ያለው ጉባዔው፣ ለችግሮቹ ዘላቂ መፍትሔ ባለመቅረቡ በአካባቢዎቹ የሚደርሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳላቆመ አስረድቷል፡፡

በመሆኑም የፌዴራልና የሚመለከታቸው የክልል መንግሥታት በተለይም በኦሮሚያ፣ በአማራና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በታጣቂዎች እየተፈጸሙ ያሉ ጥቃቶችን በአፋጣኝ እንዲያስቆሙ ጉባዔው አሳስቧል፡፡

በተጨማሪም የፌዴራልና የክልል መንግሥታት ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ ዜጎችን በሕይወት የመኖርና የአካል ደኅንነት መብቶች እንዲያስከብሩ ኢሰመጉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በሌላ በኩል ጉባዔው ታጣቂዎች የሚያደርሱት ጥቃት እንዲቆም ካቀረበው ጥሪ በሻገር የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን አስመልክቶ ከመንግሥት በኩል የሚሰጡ ሰብዓዊ ድጋፎች በቂ ባለመሆናቸው ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ ከመሆናቸው በፊት መንግሥት ያለምንም አድልዎ በቂ የሆኑ ሰብዓዊ ድጋፎችን እንዲያቀርብ ጥሪ አቅርቧል፡፡ ጉባዔው መንግሥት የሰብዓዊ ድጋፉን ማቅረብ ባልቻለበት ወቅት ደግሞ መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶችና ለዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች ድጋፍ የሚያደርጉበትን ሁኔታዎች እንዲያመቻች ጠይቋል፡፡

2013 .ም. 12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ከተገለጸበት ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች ውጤታቸው አንደገና እንዲፈተሽላቸው ለሚመለከተው አካል ጥያቄ እያቀረቡ እንደሚገኙ በመግለጫው የተዳሰሰ ሲሆን፣ በጉዳዩ ዙሪያ ከተለያዩ አካላቶች የሚሰነዘሩ ሐሳቦች ማኅበረሰቡን ግራ እያጋቡና የተማሪዎችንም ሥነ ልቦና እየጎዱ በመሆናቸው የሚመለከተው አካል ተገቢውን ማብራሪያ እንዲሰጥና የዕርምት ዕርምጃ እንዲወስድ ኢሰመጉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...