Sunday, March 26, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በኦጋዴን የሚገኘውን የተፈጥሮ ነዳጅ መጠን የሚያጠና የአሜሪካ ኩባንያ ሥራ ሊጀምር ነው

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

  • ማዕድን ሚኒስቴር ከኩባንያው ጋር የአራት ወራት ስምምነት ተፈራርሟል

በኢትዮጵያ ደቡብ ምሥራቅ ክፍል በኦጋዴን ቤዚን በጥናትና በቁፋሮ የተገኘውን የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት ለኢንቨስትመንት ጥቅም ለማዋል የሚያግዝ የማማከርና የጥናት ሥራ ለማከናወን የተስማማው፣ የአሜሪካ ኔዘርላንድ ስዌል ኤንድ አሶሼትስ ኢንክ ኩባንያ ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ ሥራ ሊጀምር ነው፡፡

ኩባንያው የሚያካሂደው ጥናት ውጤት በኦጋዴን የሚገኘውን የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት ለማዳበሪያናኢነርጂ ኢንቨስትመንቶች ጥቅም ላይ እንዲውል፣ እንዲሁም ከጋዝ ወደ ፈሳሽ ነዳጅ ለመቀየር ተብሏል፡፡

የማማከርና የጥናት ሥራውን ለማከናወን ዓለም አቀፍ ጨረታ ወጥቶ የኔዘርላንድ ስዌል ኤንድ አሶሼትስ ኢንክ ኩባንያ አሸናፊ መሆኑን የማዕድን ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ኩባንያው በሶማሌ ክልል አጋዴን ቤዚን 3,500 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ላይ የተከናወኑ የፍለጋና የጥናት ውጤቶችን መነሻ በማድረግ፣ በቤዚኑ ያለውን የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት መጠን የሚያሳውቅና ኢኮኖሚያዊ ግምገማ የሚያሳይ ጥናት የሚያከናውን እንደሆነ ተመላክቷል፡፡

ማክሰኞ መጋቢት 13 ቀን 2014 .ም. ከማዕድን ሚኒስቴር ጋር ስምምነት ያደረገው ኩባንያው፣ በዘርፉ ያሉት ባለሙያዎችና በበርካታ አገሮች ያከናወናቸውን ሥራዎች ከግንዛቤ ተወስደው፣ የማዕድን ሚኒስቴር እንደመረጠው ገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብቶች እንዳሉ በጥናትና በቁፋሮ የተረጋገጠ እንደሆነ ያስታወቀው የማዕድን ሚኒስቴር፣ብቱን ወደ ኢንቨስትመንት ደረጃ ለማሳደግ የተለያዩ ተግዳሮቶች ሲያጋጥሙ መቆየታቸውን አክሏል፡፡

የኢትዮጵያ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ማረጋገጫ እንዲኖረው ማድረግ ሌላው በኩባንያው የሚከናወን የጥናት ዓላማ እንደሆነ በስምምነት ፊርማው ወቅት የተገለጸ ሲሆን፣ ይህ ዓለም አቀፍ ማረጋገጫ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብቱን እንደ አገር ሀብት የሚያስቆጥረው በመሆኑ ኢትዮጵያ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ለሚኖራት ተሳትፎ እንደ መንደራደሪያነት የሚጠቅማት ይሆናል ተብሏል፡፡

የኔዘርላንድ ስዌል ኤንድ አሶሼትስ ኢንክ ኩባንያ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ዎልፍ ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ የአማካሪ ኩባንያው በዓለም አቀፍና በአፍሪካ ደረጃ አገሮች ያላቸውን የማዕድን ሀብት መጠን የተመለከተ ጥናቶችን ያከናውናል፡፡ ይህም አገሮች ያላቸውን የማዕድን ሀብት መጠን መሠረት አድርገው እንዴት ለራሳቸውና በውጭ ገበያ ለገቢ ማግኛ ምንጭነት ሊጠቀሙባት የሚያስላቸው እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

ኩባንያው ከማዕድን ሚኒስቴር ጋር የተፈራረመው ስምምነት በደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ የኦጋዴን ቤዚን የሚገኘውን የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት በምን ያህል መጠን እንደሚገኝ፣ ይህንንም ማዕድን ሚኒስቴር በሚያስቀምጠው አሠራር መሠረት ሌሎች በነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ማውጣት ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ሊጠቀሙበት በሚቻልበት መንገድ መረጃ ለመተንትን መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኩባንያው ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር የተፈራረመው ስምምነት የአራት ወራት የጊዜ ገደብ ያለው እንደሆነ የተናገሩት ሚስተር ዎልፍ፣ ድርጅቱ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ወደ ትግበራ የሚሸጋገር እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ በተጠቀሱት ወራት ውስጥ  የተጠናቀረ መረጃ በሪፖርት መልክ ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሚቀርብ መሆኑን፣ ይህም ተቋሙ በቀጣይ ለሚያደርገው ሥራ የሚጠቅመው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ኩባንያው የሚጠቀመው መረጃ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በኩል የተዘጋጀ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ ከዚያ ውጪ አዲስ መረጃ ማዘጋጀት እንደማይጠበቅበት ተገልጿል፡፡ አገሪቱ ከነዳጅ ሀብቷ ጋር የተገናኙ በርካታ የሴስሚክና የሰብኮር መረጃዎች ስላሏት፣ ይህንን መረጃ በመጠቀም ምን ያህል የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብቱ መጠን ይገኛል? ምን ያህልስ ማምረት ይቻላል? የሚለው የሚወሰን እንደሆነ ምክትል ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል፡፡

የመጀመሪያውን የስምምነት ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ወዲያውኑ ቀጣይ ስምምነት የማድረግ ዕቅድ በዚህ ወቅተ ይደረጋል ተብሎ መገመት እንደማይቻል ያስታወቁት ሚስተር ዎልፍ፣ ከኮንትራቱ መጠናቀቅ በኋላ የሚከናወኑ ጉዳዮች ካሉ በሁለቱ አካላት የጋራ ስምምነት መሠረት እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

በስምምነትነ ሥርዓቱ ላይ የማዕድን ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር)፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን፣ እንዲሁም የኩባንያው ተወካዮችና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የማዕድን ሚኒስቴር በጥናትና ቁፋሮ የተገኙ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት ውጤቶችን ለማልማት፣ ለማሳደግና በኢንቨስትመንት ደረጃ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማድረግ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ እንደሚገኝ የማዕድን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በሰኔ ወር 2013 ዓ.ም. የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር በሶማሌ  ክልል  የተገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ አልምቶ ኤክስፖርት ለማድረግና ለተጨማሪ የፔትሮሊየም (የነዳጅ ዘይት) ፍለጋና ልማት፣ በዚሁ አካባቢ ለማካሄድ  ፈቃድ  ላገኘው የቻይና ፖሊጂሲኤል  ኩባንያ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ይታወሳል።

የቻይና ኩባንያው  በሶማሌ  ክልል  ካሉብና ኢላላ የተገኘውን  ከፍተኛ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት አልምቶ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ፈቃድ ያገኘው እ... 2013 ቢሆንም፣ በአካባቢው የሚገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ አልምቶ ለገበያ ለማቅረብ እያደረገ ያለው ጥረት እጅግ ደካማ ከመሆኑም በላይ፣ ለመንግሥት ባቀረበው መርሐ ግብር መሠረት እያከናወነ አለመሆኑን በመጥቀስ ሕጋዊ ዕርምጃ ከመውሰዱ በፊት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንደሰጠው መዘገቡ አይዘነጋም።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች