Saturday, July 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮኑ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን

የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮኑ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን

ቀን:

በሳምንቱ መጨረሻ የዓለም የመም ላይ ድንቅ አትሌቶች 18ኛው የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ለመካፈል በሰርቢያ ቤልግሬድ ከተማ ከትመው ነበር፡፡ ዘንድሮ በተለያዩ አውሮፓ ከተሞች ላይ ሲከናወኑ በነበሩት የቤት ውስጥ ውድድሮች የግል ሰዓታቸውን ሲያሻሽሉ እንዲሁም አዲስ ክብረ ወሰን ሲያስመዘግቡ የቆዩት አትሌቶች ዳግም መገናኘታቸው የበርካቶችን ቀልብ መግዛቱ አልቀረም፡፡

ኢትዮጵያም 800 1,500 እና 3,000 ሜትር ርቀቶች ላይ የሚካፈሉ አትሌቶችን በመያዝ ሻምፒዮናው ላይ መካፈል የቻለች ሲሆን አዳዲስ ክብረ ወሰኖች ጭምር በማምጣት በበላይነት ማጠናቀቅ ችላለች፡፡ ኢትዮጵያ ከረዥም ጊዜ በኋላ በደመቀችበት የቤልግሬዱ የዓለም ሻምፒዮና በአራት ወርቅ፣ ሦስት ብርና ሁለት የነሐስ ሜዳሊያ በድምሩ ዘጠኝ ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ከዓለም አንደኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች፡፡ ኢትዮጵያ በሴቶች 3,000 ሜትር ለምለም ኃይሉ፣ 1,500 ሜትር ጉዳፍ ፀጋይ ወርቅ ሲያስገኙ፣ በወንዶች 3000 ሜትር ሰለሞን ባረጋ እንዲሁም 1,500 ሜትር ሳሙኤል ተፈራ ወርቅ ማግኘት ችለዋል፡፡

በወንዶች 3,000 ሜትር አሸናፊው ሰለሞን ባረጋና የብር ሜዳሊያ ባለድሉ ለሜቻ ግርማ

በተለይ 1,500 ሜትር ሴቶች ጉዳፍ፣  አክሱማዊት እምባዬና ሒሩት መሸሻ ተከታትለው በመግባት ማሸነፋቸው ተረስቶ የነበረውን የአረንጓዴ ጎርፍ ትውስታን ቀስቅሷል፡፡ ኢትዮጵያ ሦስት የብር ሜዳሊያዎችን በአክሱማዊት እምባዬ 1,500 ሜትር፣ በፍሬወይኒ ኃይሉ 800 ሜትር እንዲሁም በወንዶች ለሜቻ ግርማ 3000 ሜትር ማምጣት ችለዋል፡፡

ሁለቱን የነሐስ ሜዳሊያዎችን በሴቶች ሒሩት መሸሻ 1500 ሜትር እንዲሁም እጅጋየሁ ታዬ 3000 ሜትር ማሳካት ችላለች፡፡ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. 2018 በእንግሊዝ በርኒንገሐም አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ይዛ ብታጠናቅቅም, አሜሪካ 7 ወርቅን በማምጣት አንደኛ ደረጃን ስትይዝ፤ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃ ነበር፡፡ 
ምንም እንኳን የዓለም የሚዲያ ተቋማት ኢትዮጵያ ሻምፒዮናውን በበላይነት ማጠናቀቋን በተለመደ ዘገባ ብቻ ቢያልፉትም፣ ውጤቱ ግን ለኢትዮጵያውያን አትሌቶች ትልቅ ስኬት ነበር፡፡

ለምለም ኃይሉ 3,000 ሜትር ወርቅ

3000 ሜትር ወርቅ   ተሸላሚዋ የ20 ዓመቷ ለምለም ርቀቱን ለማጠናቀቅ 841.82 የሆነ ጊዜ ፈጅቶባታል፡፡ እ.ኤ.አ. 2017 18 ዓመት በታች ሻምፒዮና እንዲሁም 2020 የዓለም የቤት  20 በታች ሻምፒዮና ክብረ ወሰንን 401.57 መጨበጥ የቻለችው አትሌቷ ለቤልግሬዱ የወርቅ ድል ብርታት ሆኗታል፡፡
ከሌሎቹ ኢትዮጵያውያት አትሌቶች ዳዊት ሥዩምና እጅጋየው ታዬ ጋር የተጣመረቸው ለምለም፣  የመጀመሪያው 900 መቶ ሜትር እስኪ ጋመስ ድረስ ወደ ፊት ለመውጣት አልደፈረችም ነበር፡: «ተቀናጅተን ስንወዳደር ነበር፡፡ በዚህም ስኬታማ መሆን ችለናል፡፡ የማመስገን ዕድሉን ካገኘሁ ሲደግፉኝ የነበሩትን ባለቤቴን እና አሰልጣኜን ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡ ምክንያቱም ይሄ የወርቅ ሜዳሊያ ለእነሱም ይገባቸዋል፤» በማለት ለምለም አስተያየቷን ሰጥታለች፡፡

በወንዶች 1,500 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቱ ሳሙኤል ተፈራ

ለምለምን ተከትላ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀችው አሜሪካዊቷ ኤሊ ፑሪሪ በበኩሏ፣ በጥሩ አቋም ላይ እንደነበረችና ለዚህ ውጤት ስትዘጋጅ እንደነበር አስረድታ፣ በቀጣይ ለምለምን ለመርታት ጠንክራ እንደምትሠራ ተናግራለች፡፡ አትሌቷ ርቀቱን 842.04 በሆነ ጊዜ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የብር ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች፡፡
ሌላዋ ኢትዮጵያዊት እጅጋየሁ ታዬ 842.23 በመግባት የነሐስ ሜዳሊያን ማግኘት ችላለች፡፡

ጉዳፍ ፀጋይ፣ አክሱማዊት እምባዬና ሒሩት መሸሻ 1500 ሜትር ገድል
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ ሻምፒዮናዎች ላይ የሚታወቁበትና ተከታትለው የሚገቡበት የአርንጓዴ ጎርፍ ገድል ከታየ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ አትሌቶቹ በአንድ ሻምፒዮና ላይ ተከታትለው ሲገቡ መመልከትን የናፈቁ በርካቶች ናቸው፡፡ በሰርቢያዋ ቤልግሬድ ከተማ 1500 ሜትር አትዮጵያን ያነገሧት ባንዲራ  ጉዳፍ፣ አክሱማዊትና ሒሩት አረንጓዴውን ጎርፍ ለማያውቁት የዘመኑ ወጣቶች  ማሳየት ችለዋል፡፡
የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና የክብረ ወሰን ባለቤቷ ጉዳፍ  1500 ሜትር ውድድርን በበላይነት ለማጠናቀቅ ምንም ዓይነት ዕድል አላባከነችም፡፡ ጉዳፍ ርቀቱተን ለማጠናቀቅ 357.19 በመግባት የሻምፒዮናውን ክብረ ወሰን መጨበጥ ችላለች፡፡

ሌላዋ ኢትዮጵያዊት አክሱማዊት 402.29 ሁለተኛ ሆና ስታጠናቅቅ፣ ሒሩት 403.39 በሆነ ጊዜ ሦስተኛ ሆናለች፡፡ «የሻምፒዮናውን ክብረ ወሰን ለመጨበጥ ዕቅዴ ነበር፡፡ ጥሩም ነበር፡፡ ርቀቱን 357 መጨረስ አንደምችል አሠልጣኜ ይነግረኝ ነበር፡፡ ኢትዮጵያውያን ተከታትለን በመግባታችን ደስተኛ ነኝ፤በማለት ጉዳፍ ከውድድሩ በኋላ አስተያየቷን ሰንዝራለች፡፡

በቶኪዮ ኦሊምፒክ ወቅት ገጥሟት ከነበረው የተረከዝ ጉዳት ሙሉ በሙሉ ማገገሟን የገለጸች ሲሆን፣ በቀጣይ 5000 ሜትር ክብረ ወሰንን መጨበጥ ፍላጎት እንዳለት ጠቁማለች፡፡ እ.ኤ.አ. 2008 በቫሌንሽያ በገለቴ ቡርቃ 359.75 ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን ለሰባት ተከታታይ ጊዜ በኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሲሻሻል ቆይቷል፡፡ ጉዳፍ የመጀመሪያውን ዙር 30.60 ስትዞር፤ 400 ሜትሩን ለመሮጥ 61.85 የሆነ ጊዜ እንዲሁም 800 ሜትሩን ለማጋመስ 206.18 የሆነ ጊዜ ወስዶባታል፡፡

2019 ጀምሮ በቤት ውስጥ ወይም ከቤት ውጪ በተደረጉ በሁሉም 1500 ሜትር ርቀቶች ያልተረታችው ጉዳፍአዲሷ ኢትዮጵያዊቷ ወርቃማ አትሌት” (The new Ethiopian golden girl) የሚል ስያሜ አግኝታለች፡፡ ጉዳፍ ለመጨረሻ ጊዜ በርቀቱ የተረታችው 2018 ቦስተን የዓለም የቤት ውስጥ የዙር ኩነት ላይ በተደረገው ውድድር ሦስተኛ ደረጃን ይዛ በወጣችበት ጊዜ ነበር፡፡ ከዚህም ባሻገር አትሌቷ በሻምፒዮናው ባስመዘገበችው ድልም፣  ገለቴ ቡርቃ (2008) ቃልኪዳን ገዛኸኝ(2010) ገንዘቤ ዲባባ (2018 እና 2012) እና ዜግነቷን ለስዊድን የቀየረችው አበባ አረጋዊ (2014) እንዲሁም ዜግነቷን ለኔዘርላንድ የቀየረችውን ሲፋን ሀሰን( 2016) በቅብብሎሽ ያስመዘገቡትን ማስቀጠል ችላለች፡፡

በወንዶች 3,000 ሜትር አሸናፊው ሰለሞን ባረጋና የብር ሜዳሊያ ባለድሉ ለሜቻ ግርማ

የሰለሞን ባረጋና ለሜቻ ግርማ 3000 ሜትር ድል

ለኢትዮጵያ ሌላኛውን ወርቅ ማስገኘት የቻለው ሰለሞን ባረጋ እና  የብር ሜዳሊያ ማግኘት ለሜቻ ግርማ ጥምረት የዘንድሮ የቤት ውስጥ ዓለም ሻምፒዮና ክስተት ነው፡፡ ከአራት ዓመት በፊት በበርኒግሀም የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና  3000 ሜትር የብር ሜዳሊያ ማሳካት የቻለው ሰለሞን ባረጋ፣ በቤልግሬድ 741.38 በመግባት ወርቁን አሳክቷል፡፡

በቶኪዮ ኦሊምፒክ 10 ሺሕ ሜትር ባለወርቁ  ሰለሞን፣ ኢትዮጵያ በወንዶች 3000 ሜትር ያገኘችውን የወርቅ ቁጥር ስምንት እንድታደርስ አስችሏታል፡፡
በቶኪዮ ኦሊምፒክ 3000 ሜትር መሰናክል የብር ሜዳሊያ ባለቤት መሆን የቻለው ለሜቻ ግርማ 741.38 በመግባት የብር ሜዳሊያውን አሳክቷል፡፡ እንደ ሰለሞን አስተያየት ከሆነ፣ ውድድሩ ከመጀመሩ ቀደም ብሎ የቡድን ሥራ  መሥራት እንደሚገባቸው ከሌላው የአገሩ ልጅ ጋር ሲወያዩ እንደነበር ያነሳ ሲሆን በዚህም ውጤታቸው ማማሩን አስረድቷል፡፡

«ወደ ቤልግሬድ ስንመጣ የኢትዮጵያን  የአትሌቲክስ  ቀጣይ ታሪክ ልንሠራ ነው፡፡ በአዕምሮ እንዲሁም በአካል ብቃት ጥሩ ዝግጅት አድርጌ ስለነበር፣ ጥሩ የውድድር ጊዜ ነበርኝ፤» ሲል ሰለሞን አስተያየቱን ሰንዝሯል፡፡ 
ከዚህ ቀደም በቤት ውስጥ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና 1500 ሜትር ኃይሌ ገብረሥላሴ (1999) እንዲሁም 3000 ሜትር (19971999 እና 2003) የወርቅ ሜዳሊያን ማግኘት ችሏል፡፡ ቀነኒሳ በቀለ (2006) ታሪኩ በቀለ (2008) እንዲሁም ዮሚፍ ቀጄልቻ (2016 እና 2018) በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 3000 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያን ያገኙ ናቸው፡፡

የሳሙኤል ተፈራ የ1,500 ሜትር ድል

በሻምፒዮናው የወንዶች 1500 ሜትር ውድድር የበርካቶችን ቀልብ የሳበና ትኩረት የተሰጠው ክስተት ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በኦሊምፒክ 1500 ሜትር ባለድሉና የክብረ ወሰን ባለቤት የሆነው የኖርዌዩ ጃኮብ ኢንግብሪግሰን የራሱን ክብረ ወሰን ይሰብራል የሚል ግምት ሚዛኑን ደፍቶ ስለነበር ነው፡፡

2018 በእንግሊዝ በርኒንገሃም የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና 1500 ሜትሩን 358.19 በመግባት አዲስ ክብረ ወሰን መስበር ችሎ የነበረው ሳሙኤል ተፈራ፣ በቤልግሬድ ግምት አግኝቶ የነበረው ኖርዌጂያኑን በ332.77 ቀድሞ በመግባት የሻምፒዮናውን ሪከርድ ዳግም በእጁ ማስገባት ችሏል፡፡

የበርካቶችን በተለይ የምዕራባውያንን አፍ ማስያዝ የቻለው የሳሙኤል ውጤት፣ በተፎካካሪ አትሌቶች ዘንድ እንኳን ያልተገመተ ድል እንደነበር ተጠቅሷል፡፡
«ምንም እንኳ ውድድሩን ማሸነፍ በመቻሌ ደስተኛ ብሆንም፣ የውድድሩን ክብደት ግን ሳልጠቅስ ማለፍ አልፈልግም፤» ሲል ሳሙኤል ከውድድሩ በኋላ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
በዚህ ባልጠበቀ ውድድር ላይ አፈትልኮ በመውጣት ድል ማድረግ የቻለው ሳሙኤል በቀጣይ ተስፋ የተጣለበት  እንደሆነ  በችሎታው ማሳየቱን በርካቶች መስክረዋል፡፡
እ.ኤ.አ. 1985 ጀምሮ በሻምፒዮናው የተሳተፈችው ኢትዮጵያ 31 ወርቅ፣ 13 ብር እና 15 ነሐስ በድምሩ 59 ሜዳሊያ ከዓለም ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የሰብዓዊ መብት ጉዳይና የመንግሥት አቋም

ሰኔ ወር አጋማሽ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ከፍተኛ የሰብዓዊ...

ከሰሜኑ ጦርነት አገግሞ በሁለት እግሩ ለመቆምና ወደ ባንክነት ለመሸጋገር የተለመው ደደቢት ማክሮ ፋይናንስ

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ በቀዳሚነት ስማቸው ከሚጠቀሱት ውስጥ ደደቢት...