Monday, May 29, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

አቶ ግርማ ዋቄ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ግርማ ዋቄ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ።

የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት የቀድሞው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ ተነስተው በምትካቸው የአየር መንገዱ ቦርድ አባል የነበሩት አቶ ግርማ ዋቄ ተሹመዋል።

አቶ ግርማ ዋቄ ከቦርድ ሰብሳቢነታቸው በተጨማሪ የኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ መመደባቸውንም ምንጮቹ ገልጸዋል።

አቶ ግርማ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመደቡት ለአንድ ዓመት ብቻ እንደሆነና ዋና ተልእኳቸውም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የተረጋጋ የማኔጅመንት ቡድን መገንባት እንደሆነ ታውቋል።

በአዲሱ የድርጅቱ አወቃቀር መሠረት፣ ከፕሬዚዳንቱ ስር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ አስፈጻሚ ሊኖር እንደሚችል ምንጮቹ ገልጸዋል።

አቶ ግርማን የኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ ፕሬዚዳንት አድርጎ የመደባቸው በቅርቡ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እንደሆነ ምንጮች ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ማሞ ምህረቱ መረጃውን እንዲያረጋግጡ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

የአቶ ግርማ ዋቄ ሹመት ከመሰማቱ አስቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ተወልደ ገብረማርያም ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ረፖርተር መዘገቡ ይታወሳል። 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም በፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን አስታውቀዋል፡፡

አቶ ተወልደ በህክምና ላይ ባሉበት አሜሪካን አገረ ሆነው ለተቋሙ ማኔጅመንት በላኩት የኢሜል መልእክት፣ በገጠማቸው የጤና እክል ምክንያት በኃላፊነት መቀጠል እንዳልቻሉ ጠቅሰው፣ በፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው በጡረታ መገለላቸውን አሳውቀዋል።

አቶ ተወልደ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚነትን የተረከቡት ከአቶ ገርማ ዋቄ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ በአየር መንገዱ በተለያዩ ኃላፊነቶች ለ37 ዓመታት አገልግለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ አባላት ስብሰባ ላይ መሆናቸውን የጠቀሱት ምንጮቹ ፣ በዚህ ስብሰባ ለአየር መንገዱ አዲስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ምደባ ሊወሰን እንደሚችል ጠቁመዋል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች