Saturday, April 20, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቶ መስፍን ጣሰውን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ መሾሙን አስታወቀ፡፡

አቶ መስፍን በቶጎ የኤስካይ (ASKY) ማኔጂንግ ዳይረክተር በመሆን እየሰሩ ነበር፡፡

አቶ መስፍን በአየር መንገዱ ለ38 ዓመታት በተለያዩ ኃላፊነቶች ሲያገለግሉ እነደነበር ተጠቁሟል፡፡

አየር መንገዱ የቦርድ አባላቱን በአዲስ መልክ ያዋቀረ ሲሆን አቶ ግርማ ዋቄ የቦርድ ሰብሳቢ፣ የንግድ ባነክ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑትን አቶ ተክለወልድ አጥናፉ፣ የብሄራዊ መረጃና ደህንነትዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዢ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ፣ የኖክ ባለድርሻና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ጥላሁንና አቶ ረታና አቶ አለማየሁ አባላት ሆነዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን በትላንትናው እለት መግለጻችን ይታወሳል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች