Tuesday, April 16, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

መቶ ዶላርና ተመሳሳይ ምንዛሪ ያላቸውን የውጭ ገንዘብ ይዞ የተገኘን ከማሰር ይልቅ እንዲወረስ አቅጣጫ ተሰጠ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የውጭ አገር ገንዘብ ማለትም አንድ መቶ ዶላርና ተመሳሳይ ምንዛሪ ያላቸው የሌሎች አገሮች ገንዘቦችን ይዞ የተገኘን ሰው ከማሰር ይልቅ ገንዘቡ እንዲወረስ ፍትሕ ሚኒስቴር አቅጣጫ አስቀመጠ፡፡

 

በፍትሕ ሚኒስትሩ ጌዴዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ፊርማ ውጪ በተደረገ ደብዳቤ ለተቋሙ የኢኮኖሚ ወንጀል ጉዳዮች ዓቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት በተሰጠ አቅጣጫ፣ መቶ ዶላርና ከዚያ በታች የውጭ አገሮች ገንዘብ ይዞ የተገኘ ገንዘቡ ይወረሳል፡፡

በሚኒስትሩ ፊርማ ወጪ የተደረገው ደብዳቤ እንደሚያትተው፣ መቶ ዶላርና ከዚያ በታች ያለው የውጭ አገሮች ገንዘብ መጠኑ አነስተኛ በመሆኑ፣ ገንዘቡን ይዘው የተገኙ ሰዎችን ይዞ የወንጀል ክስ መመሥረት፣ የዓቃቤ ሕግንና የፍርድ ቤትን ጊዜ እንዲሁም ሀብትን ከማባከን ባለፈ ፋይዳ እንደሌለውም በመግለጽ፣ ገንዘቡን ይዘው የተገኙ ሰዎችን መክሰስ እንዲቀር ዳይሬክቶሬቱ ጥያቄ በማቅረቡ ምክንያት፣ ክሱ ቀርቶ ገንዘቡ እንዲወረስ አቅጣጫ መሰጠቱን ደብዳቤው ያስረዳል፡፡

በመሆኑም ከመጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ የተጠቀሰውን ያህል የውጭ አገሮች ገንዘብ ይዘው የተገኙ ሰዎችን ሳይታሰሩ፣ ገንዘቡን ብቻ መውረስ በቂ መሆኑን፣ ቀደም ብሎ ክስ የተመሠረተባቸው ካሉ ክሱ እንዲቋረጥ እንዲደረግና የተፈረደባቸው ካሉም በይቅርታ ሥርዓት የሚታይላቸው መሆኑን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች