በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የባህል ፌስቲቫል ‹‹ባህላችን ለቱሪዝም ዕድገታችን›› በሚል መሪ ሐሳብ በሻሸመኔ ከተማ ከመጋቢት 18 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ለሦስት ቀናት ተካሂዷል፡፡ በጎዳና ላይ ትርዒት የተከፈተው ፌስቲቫሉ የክልሉ ዞኖች የባህል ቡድኖች ከተለያዩ ክልሎች የመጡ ቡድኖች የተሳተፉበት ሲሆን፣ የባህላዊ እሴቶች ዓውደ ርዕይ፣ በተለያዩ ሙዚቃ ባንዶች መካከል ውድድር መደረጉ ተገልጿል፡፡ ከክልሉ ባህል ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ፌስቲቫሉ ለባህል ዕድገት ትልቅ ጠቀሜታ አለው። ከመርሐ ግብሮቹ መካከል ለኦሮሞ ባህልና ኪነ ጥበብ ዕድገት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ዕውቅናና ምስጋና፣ የጥናትና ምርምር ሲምፖዚየም ይገኙበታል፡፡ ከሻሸመኔው ክልል አቀፍ ፌስቲቫል አስቀድሞ መሰንበቻውን በክልሉ ከወረዳ እስከ ዞን ባሉት መዋቅሮች የባህል ሳምንት መከበሩ ቢሮው ገልጿል። ፎቶዎቹ የፌስቲቫሉን ከፊል ገጽታዎች ያሳያሉ፡፡
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -
ፌርማታ ፅሁፎች
ትኩስ ፅሁፎች
- Advertisement -
- Advertisement -