Friday, July 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህል‹‹የዘመናችን ወግ››

‹‹የዘመናችን ወግ››

ቀን:

ዘመናት በተለያዩ ሁነቶች ይገለጻሉ፡፡ በሙዚቃ፣ በግጥም፣ በሥዕልና በሌሎች ሙያዎችም ዘመን መተረኩ መተቸቱ አልቀረም፡፡ ለዚህም ዘመናት ያለፉት ጊዜያት ሥራዎች ምስክር ናቸው፡፡

‹‹የዘመን ወግ›› የሚለው የሥዕል ዓውደ ርዕይ በሠዓሊ ኪሩቤል መልኬ የተሣሉ ሥዕሎች የቀረቡበት ሲሆን፣ ዘመኑ በሰጠው ርዕስ ውስጥ እየዋኘና ከፍ ዝቅ ሲል የደረሰበትን ድካምና ብርታት፣ እፎይታና ሐሴት ለማድረግ የሠራቸው ሥራዎች የቀረበበት ነው፡፡

እያንዳንዱ ቀን ቢሆን እንደ ዘመን ነው፡፡ የራሱ ሐሳብና ስሜትም አለው፡፡ የዛሬና የነገ እውነታዎች ሊለያዩ እንደሚችል መረዳት፣ ይህም የምንኖርበት ዘመን ከሌለ አቅጣጫ አይተን መረዳት ላይ ለመድረስ የማመዛዘኛ ዕድል ይሰጣል›› ብሎ ሠዓሊው የገለጸበት ነው፡፡

የሥዕሉ የመግለጫ ሐሳብ ተመልካቾች ሥራዎቹን ሲያዩ አዕምሮአቸው ውስጥ የሚከሰተው ነገር መሆኑንም ይገልጻል፡፡

ሠዓሊ ኪሩቤል ሦስተኛውን የግል የሥዕል ዓውደ ርዕዩን እንደየዘመኑ በተፈጠሩ ክንውኖች ያቀረባቸው ሲሆን፣ ሥራዎቹ ሐሳባቸው እንደሚለያዩ ይጠቁማል፡፡ በፈንድቃ የሥዕል ማዕከል እየተጎበኘ የሚገኘው የሥዕል ዓውደ ርዕይ መጋቢት 16 ቀን የተከፈተ ሲሆን፣ ሚያዝያ 10 ቀን 2014 ዓ.ም. መዝጊያው መሆኑንም ሠዓሊ ኪሩቤል ተናግሯል፡፡

ሠዓሊ ኪሩቤል እንደተናገረው፣ የዘመን ወግ ያለበት ምክንያት፣ በአገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ጉዳይ ስላነሳሳው ነው፡፡ እነዚህ ጉዳዮች በታክሲ ውስጥና በመንገድ ላይ ከማያውቃቸው ሰዎች ጋር ጭምር የሚወያይበት መሆኑን ገልጿል፡፡

እነዚህ ምልልሶች በአዕምሮ ውስጥ የሚፈጥሩት ሥዕሎች እንዳሉ፣ ገጣሚዎች በግጥማቸው፣ ሙዚቀኞች በሙዚቃቸው እንደሚገልጹት ሁሉ ሠዓሊውም ባለው ሙያ በሥዕል የገለጹበት መሆኑን አብራርቷል፡፡

ከዚህ ቀደም ለሕዝብ የታዩት ሁለቱ ሥራዎች በቴክኒክ ደረጃ አንድ ዓይነትና የመጀመርያዎቹ ሥራዎቹ ከመመረቂያው ጋር ተያይዘው የመጡ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

ሥራዎቹ ብዙ የሐሳብ ርቀት ባይኖራቸውም፣ በጊዜው ሁነቶች ላይና ውስን ነገሮች ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ ሠዓሊው ያስረዳል፡፡

የመጀመርያውና ሁለተኛው  ሥራዎቹ ከባህልና ከዘመናዊነት ጋር ተያይዘው የማኅበረሰቡ የአለባበስ ሁኔታ እንዴት እንደተቀየረና በመቀየራቸው አገር ምን ተጠቀመች፣ ምን ተጎዳች የሚለው ላይ አተኩሮ ኢኮኖሚ ማኅበራዊ ጉዳዮችን  የሚዳሰሱ ሥራዎች መሆናቸውን ያስረዳል፡፡

ለሕዝብ ካበቃቸው ሁለቱ በይበልጥ ሦስተኛው ዓውደ ርዕይ ኢትዮጵያ የምትገኝበትን ሁኔታ የዳሰሰ ሥራዎች የቀረቡበት ሲሆን፣ በኢትዮጵያና በዓለም ላይ የሚለዋወጡ ነገሮችን ዝም ብሎ ማለፍ አለመፈለጉ መነሻ ሆኖታል፡፡

 ሠዓሊው እንደተናገረው፣ ‹‹የዘመናችን ወግ›› የሥዕል ዓውደ ርዕይ ለኢትዮጵያ የሥዕል ገበያ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ የሰው አቀባበል አስደሳች እንደሆነ፣ ብዙ ተመለካቾችን ያወያየ፣ ያከራከረ ሥራ መሆኑን ተናግሯል፡፡

ከመጋቢት እስከ ሚያዝያ 10 ቀን 2014 ዓ.ም. ሦስተኛው የሥዕል ዓውደ ርዕይ 22 ሥራዎች ቀርበዋል፡፡ በሚቆየውና በቀረቡት ሥዕሎች መካከል ርዕስ የተሰጣቸው ሥራዎች የቀረቡ ሲሆን፣ በሮቹ፣ የመጽሐፍ መደርደሪያው አራት፣ የመጽሐፍ መደርደሪያው አምስት እና እክል ናቸው፡፡

የዘመናችን ወግ የሥዕል ዓውደ ርዕይ ዋጋቸው እንደ ሥዕሉ መልዕክት የሚለያዩ ሲሆን፣ አንድ ሥዕል ከ3,000 እስከ 50 ሺሕ ብር ይሸጣል፡፡

ከቀረቡት ሥዕሎች ሐሳብ መካከል

ለዓሳ አጥማጅ አሳ ሳይሆን መረቡን ስጠው የተባለውን ብሒል የሚተርከው አንደኛው ሥራው ሰውን ከመርዳት መስጠት የበለጠ አያስራቸውም ወይ? የሚለውን ሐሳብ ያዘለ ነው፡፡

ዓለም አቀፋዊ ተፅዕኖ፣ በአገር በግለሰብ ደረጃ ያለውን የሚተርክ የሥዕል ሥራም መሆኑን፣ በሚያደርጉልን ልክ መጠፍነግ የሚፈልጉ መኖራቸውን የሚጠቁም ነው ብሏል፡፡ ዕርዳታው (ልገሳው) አሁን ለተፈጠረው ቀውስ ምክንያት እንጂ መፍትሔ እንዳልሆነ ያወራበት ሥራው መሆኑን ገልጿል፡፡

የሌላኛው ሥራው ትርጓሜ ትምህርት ላይ የሚያተኩር ሲሆን፣ አንዳንዴ ትምህርት ሰዎችን አጉድሎ፣ ከሰብዓዊነት አውጥቷቸው እንደሚታዩ ገልጿል፡፡ ምክንያቱን ሲያስረዳ ደግሞ አነበብን የሚሉ፣ ምሁር ናቸው የሚባሉ ሰዎች፣ የሚያወሩትና የሚተገብሩት ከተማረ ሰው ጭንቅላት የወጡ ንግግሮችን እንደማይመስሉ ያስረዳል፡፡

 ትምህርት ሰዎች ያላቸውን ተፈጥሮአዊ ሞራል ካጎደለ ጤነኛ (ትክክለኛ) ነው ተብሎ ስለማይወስድ፣ የሥዕሉ ርዕስም ‹‹ጉድለት›› እንዳለው ገልጿል፡፡

የቡድን የሥዕል ዓውደ ርዕይ

ሠዓሊ ኪሩቤል የቡድን የሥዕል ሥራዎች ከዚህ ቀደም   ለበርካታ ጊዜ ያሳየ ሲሆን፣ ሚያዝያ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. በገብረክርስቶስ ደስታ ማዕከል ከሁለት ሠዓሊያን ጋር ተጣምሮም ሥራዎቹን ያቀርባል፡፡

በገብረ ክርስቶስ ደስታ ማዕከል ይቀርባል የተባለው የቡድን ሥራዎቹ ላይ ለብቻው የሚያቀርበው ከሦስተኛው የቀጠለ የሥዕል ሐሳቦች መሆኑን ገልጿል፡፡

የሥዕል ጎብኚዎች

አብዛኛው የሥዕል ዓውደ ርዕይ ጎብኚዎች ሠዓሊያን ሲሆኑ፣ ጥቂቶች ደግሞ ከሌሎች ሙያ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ በሥዕል ሥራዎች አገራዊ ፋይዳና መልዕክት ያላቸው ሥራዎች ይዘው የሚቀርቡ ሠዓሊያን ቢኖሩም፣ ከመንግሥት በኩል ከጥቂት ሰዎች ውጪ የሥዕል ዓውደ ርዕይ የሚያዩ እንደሌሉ ይታወቃል፡፡

በሌሎች የሥነ ጥበብ ሙያ ቴአትር፣ ሙዚቃ፣ ግጥም ውስጥ መንግሥት በሐሳብ የሚያግዙ፣ የሚተቹ ሥራዎች በተዘዋዋሪ የተፈለገው ቦታ ይደርሳል፡፡

በዓለም ትልቅ ቦታ ያለውን ኪነጥበብ ወደ ጎን አድርጎ ማኅበረሰብን መምራት አስቸጋሪ መሆኑን የሚገልጸው ሠዓሊ ኪሩቤል፣ በማኅበረሰቡ የሚሰጠው አስተያየት፣ ዕይታ፣ ሐሳብና የአገር ባህል የተገለጸበት መንገድ፣ ዘመኑ የሚናገረው የፈለገውን ነገሮችና ሌሎች ሐሳቦች ለመረዳት የመንግሥት ባለሥልጣናት ቢጎበኙት ያተርፉበታል ብሏል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አቶ ሰብስብ አባፊራ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

ከአዋጅና መመሪያ ውጪ ለዓመታት ሳይካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ...

ቀጣናዊ ገጽታ የያዘው የኢትዮ ሶማሊያ ውዝግብ

ከአሥር ቀናት ቀደም ብሎ በተካሄደው የፓርላማ 36ኛ መደበኛ ስብሰባ፣...

የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በዓረቦንና የጉዳት ካሳ ክፍያዎች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ መጣሉን ተቃወሙ

በአዲሱ ተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ውስጥ የኢንሹራንስ ከባንያዎች ለሚሰበስቡት...