Sunday, April 14, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የምግብ ዘይት የፋብሪካ ዋጋ መወሰኛ ሊወጣ ነው

ተዛማጅ ፅሁፎች

የፋብሪካዎች ዝቅተኛ የማምረት አቅም ገደብ ሊቀመጥ ነው

የምግብ ዘይት የፋብሪካ ዋጋ መወሰኛ በአንድ ወር ውስጥ ተግባራዊ እንደሚያደርግ የንግድና ቀናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ያለቀለት የፓልም ምግብ ዘይት ለሚያስመጡና ከድፍድፍ የምግብ ዘይት ለሚያጣሩ የገር ውስጥ ፋብሪካዎች ምርቱ ከፋብሪካ ለአከፋፋዮች የሚሸጥበት ዋጋ እንደሚወ በንግድና ቀናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድ ቃዎች ዋጋ ጥናት ቡድን መሪ አቶ አሸናፊ ማሙዬ ገልጸዋል።

ከዚህ በፊት አልፎ አልፎ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ፋብሪካዎች ላይ ቁጥጥር ለማድረግ ቢሞከርም ውጤታማ አለመሆኑንና ጥ የሆነ አራር እንዳልነበረው ተናግረዋል።

በመሆኑም በተለይ ፋብሪካዎቹ ለድፍድፍ ዘይት ማስመጫ የሚወስዱት የውጭ ምንዛ ዋጋን ከማረጋጋት አንር የሚቀርብ ቢሆንም በዋጋ ላይ ግን ጭማሪ መኖሩን ገልጸዋል። ለዚህም በአከፋፋዮችና ቸርቻሪዎች ላይ ከሚደረገው ቁጥጥር በተጨማሪ የፋብሪካ ዋጋ መወሰን ማስፈለጉን አቶ አሸናፊ አክለዋል።

‹‹እስካሁን በሊትር ከፋብሪካ የሚወጣበት ዋጋ ባይወሰንም በአንድ ወር ውስጥ ግን ተወስኖ ወደ ራ ይገባል፤›› ብለዋል። በአሁኑ ወቅት ገበያ ውስጥ አምስት ሊትር ፓልም ዘይት እስከ 650 ብር የሚሸጥ ሲሆን ፈሳሽ የምግብ ዘይት ደግሞ ከ950 ብር በላይ እየተሸጠ ነው

ከዋጋ መወሰኛው በተጨማሪ ፋብሪካዎች እንዲያመርቱ የሚጠበቅባቸው የዘይት መጠን እንደሚወሰን የገለጹት አቶ አሸናፊ፣ አዲስ ወደ ዘርፉ የሚገቡም ሆኑ የነባሮቹ ፋብሪካዎች ዝቅተኛ የማምረት አቅም ገደብ ይቀመጥለታል ብለዋል። 

በዚህም መረት ፋብሪካዎቹ በቀን እስከ 200 ቶን እንዲያመርቱ ሊወሰን እንደሚችል፣ ይህንን ለማድረግ የሚያስችል የማሽነሪና የቴክኖሎጂ አቅም እንዲኖራቸው ያስገድዳል ሲሉ አስረድተዋል። 

አምራቹ ለድፍድፍ ፓልም ግብዓት በመንግሥት የሚመደብለትን የውጭ ምንዛሪ ሙሉ በሙሉ ለተመደበለት ግብዓት ግዥ ብቻ መጠቀም እንዳለበት፣ ከድፍድፍ ፓልም ግብዓት የሚመረተው ምርት የገበያ ዋጋ ከውጭ አገር ተጣርቶ ከሚመጣው የፓልም ምግብ ዘይት ዋጋ የተሻለና ሸማቹን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆን እንደሚገባው አቶ አሸናፊ ጠቁመዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ፋብሪካዎች ያመረቱትን ዘይት የሚያሠራጩበት አሠራር ግልጽነት እንዲኖረው እንደሚፈለግ፣ ትክክለኛውን የሥርጭት መንገድ ጠብቀው ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ማከፋፈል ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። በተቀመጠው መፈርት መረት የማይራ አምራችም ሆነ አስመጪ የአምራችነትና የአስመጪነት ፈቃዱ እንደሚሰረዝ አክለዋል።

የዋጋና የማምረት አቅም መወሰኛውን በተመለከተ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የሸሙ የምግብ ዘይት ፋብሪካ የኮዩኒኬሽን ላፊ አቶ ቴዎድሮስ ታደሰ አምራቾችን የሚጎዳ ውሳኔ መሆኑን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት የሸሙ የምግብ ዘይት ፋብሪካ አንድ ሊትር የምግብ ዘይት የፋብሪካ ዋጋ 81 ብር መሆኑን ገልጸው ነገር ግን የምርት ወጪው ከዚህ በፊት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን አስረድተዋል። ለአብነትም ከዚህ ቀደም ለትራንስፖርት ብቻ እስከ 700 ዶላር በቶን ይከፈልበት የነበረው ድፍድፍ ዘይት አሁን 3‚000 ዶላር ደርሷል ብለዋል፡፡ በመሆኑም አምራቾች በግብዓትም ሆነ በሌሎች የምርት ወጪዎች ላይ የሚያጋጥሟቸውን የዋጋ ልዩነቶች መረት አድርገው ዋጋ ካላስተካከሉ በስተቀር የመሸጫ ዋጋ መወሰኑ እንደሚጎዳቸው አክለዋል።

የማምረት አቅም መወሰኑም በተለይ አሁን ካለው የምግብ ዘይት እጥረትና የዋጋ ከፍ ማለት አንር ትክክለኛ ርምጃ እንደማይሆን ተናግረዋል። አዳዲስ ወደ ዘርፉ የሚመጡትንም የማያበረታታ ነው ብለዋል፡፡ የግብዓት እጥረት ፈታኝ በመሆኑ አሁን ያሉት ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው እንደማያመርቱ የገለጹት አቶ ቴዎድሮስ ሸሙ የምግብ ዘይት ፋብሪካ በቀን 1‚187 ቶን የማምረት አቅም ቢኖረውም ከ30 በመቶ በታች አቅሙን እየተጠቀመ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

ሪፖርተር ከሸሙ ዘይት ምግብ ፋብሪካ በተጨማሪ የሌሎች አምራቾችን አስተያየት ለማካፈል ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም ሊሳካ አይችልም፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች