Monday, December 4, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የአበባ ምርት የመላኪያ ዋጋን የሚወስን መመርያ ወጣ

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአበባ የወጪ ንግድን ለመቆጣጠርና የአበባ ላኪዎች የሚሸጡበትን ዝቅተኛ ዋጋ ገደብ ያስቀመጠ አዲስ መመርያ አወጣ፡፡ በባንኩ በመመርያ መሠረት ከተጠቀሰው ዋጋ በታች መሸጥ የሚያስጠይቅ መሆኑንም አመልክቷል፡፡

ከዓርብ መጋቢት 23 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል በተባለው መመርያ መሠረት፣ ሆለታና ዓለም ገና አካባቢ የሚመረቱ የደጋ የአበባ ምርቶች በኪሎ ግራም 4.2612 ዶላር፣ የሰመር አበባ ደግሞ 4.7822 ዶላር መሸጥ እንዳለበት ገደብ አስቀምጧል፡፡ በተመሳሳይ እንደ ደብረ ዘይት (ቢሸፍቱ) ባሉ ወይና ደጋ አካባቢዎች የሚመረቱ የአበባ ምርቶች ደግሞ 4.3340 ዶላር ዋጋ የተቀመጠላቸው ሲሆን፣ በዚሁ አካባቢ የሚመረቱ የሰመር አበቦች ደግሞ ከ4.547 ዶላር በታች መሸጥ እንደሌለባቸው በመመርያው ተመላክቷል፡፡

ቆላ አካባቢ የሚመረቱ የሮዝ አበባ ምርቶች በኪሎ ግራም 4.6602 ዶላር፣ የሰመር አበባዎች ደግሞ ከ6.3699 ዶላር በታች መሸጥ እንደሌለባቸው የደነገገው ይህ መመርያ፣ ቁርጥራጭ የአበባ እንቡጦች ደግሞ የሚሸጡ ላኪዎች ከገዥው ጋር ባደረጉት ውል መሠረት የሚሸጡ ይሆናል ብሏል፡፡ ይህም የግብይት ኮንትራቱን በማቅረብ የሚከናወን እንደሆነ አስታውቋል፡፡ ይህ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመርያ አብዛኛዎቹን የአበባ ላኪዎች ያላስደሰተ እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡

በዚህ መመርያ ዙሪያ ያነጋገርናቸው አንዳንድ የአበባ ላኪዎች፣ መመርያው በዚህ ሰዓት መውጣቱ ተገቢ ያለመሆኑንና የአገሪቱን የአበባ የወጪ ንግድ ሊጎዳ ይችላል የሚል ሥጋት አሳድሮባቸዋል፡፡ መመርያው በአግባቡ ተጠንቶ የቀረበ እንደማይመስላቸው የሚያመላክቱት ላኪዎቹ፣ ብሔራዊ ባንክ ይህንን መመርያ መልሶ እንዲያይላቸው የሚጠይቁ መሆኑን ሳይገልጹ አላለፉም፡፡ በተለይ የአበባ ዋጋ አሁን እየቀነሰ ባለበት ወቅት ባንኩ ባወጣው መመርያ መሠረት ለመሸጥ ይከብዳል ይላሉ፡፡ በመመርያው መሠረት በተጠቀሰው ዋጋ ካልሸጡ ላኪዎቹ በቀጣዩ ወር ላይ መላክ አይችሉም የሚል ድንጋጌ በመመርያው መካተቱም የአበባ ወጪ ንግድ ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥር ሊሆን ይችላል የሚል ሥጋታቸውንም ገልጸዋል፡፡ እስካሁን የአበባ የወጪ ንግድን በተመለከተ ብዙ የምርት ዓይነቶች ከአራት ዶላር በታች መሸጥ የማይችሉ እንደነበር የተለገጸ ሲሆን የአሁኑ መመርያ ግን ለላኪዎች ይከብዳል ተብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች