Friday, June 2, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በዓለም አቀፍ ደረጃ የጨመረው የነዳጅ ዋጋ ኢትዮጵያን አሥር ቢሊዮን ብር እንዳከሰራት ተገለጸ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

በሩሲያና በዩክሬን መካከል በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ የጨመረው የነዳጅ ዋጋ በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ኢትዮጵያን አሥር ቢሊዮን ብር እንዳከሰራት ተገለጸ፡፡

ከኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የነዳጅ ዋጋ በበርሜል ይሸጥበት ከነበረው 60 እና 70 ዶላር ወደ 140 ዶላር ማሻቀቡ፣ ኢትዮጵያ አሥር ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ወጪ እንዳስወጣት ወይም እንዳከሰራት አመልክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ኃይለ ማርያም ለሪፖተር እንደገለጹት እንደ ሌሎቹ አገሮች ሁሉ የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ኢትዮጵያንም ዋጋ እያስከፈላት ሲሆን፣ በአንድ ወር ብቻ አሥር ቢሊዮ ብር እንድታጣ ምክንያት መሆኑ ትልቅ ጉዳት መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ በወርኃዊ የነዳጅ ወጪዋም ወደ 250 ሚሊዮ ዶላር ከፍ እንዲል አስገድዷል፡፡ ይህም መንግሥት ይህንን ልዩነት በመሸፈን በዓለም ዝቅተኛ በተባለ ዋጋ ነዳጅ እየተሸጠ የሚገኝ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ መጨመር የበለፀጉ አገሮችን ጭምር እየፈተነ የሚገኝ ሲሆን፣ እንደ ፈረንሣይ ያሉ አገሮች በነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ በማድረግ ኅብረተሰቡ ነዳጅን ቆጥቦ እንዲጠቀም ሁሉ ማወጃቸውን አቶ ታደሰ አስታውሰው፣ በኢትዮጵያ ነዳጅ ጭማሪ ባይደረግም ኅብረተሰቡ በቁጠባ የመጠቀም ባህሉን ማዳበር አለበት ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ አሁን ነዳጅ በምታስገባበት ዋጋ መሠረት ለገበያ ቢቀርብ የአንድ ሌትር የቤንዚን ዋጋ 76 ብር መሸጥ የነበረበት መሆኑንም ከአቶ ታደሰ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡ አሁን ላይ ግን የአንድ ሌትር ቤንዚን ዋጋ 31 ብር ከ74 ሳንቲም እየተሸጠ ይገኛል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች