በተሾመ ብርሃኑ ከማል
ኢስላማዊቱሪዝምየሚባለውቱሪስቶችኢስላማዊተጨባጭቅርሶችንእንዲጎበኙናረቂቅቅርሶቻቸውንእንዲገነዘቡየሚያስችልመስክነው፡፡ዓለም አቀፋዊይዘትያላቸውኢስላማዊየቱሪዝምጉባዔዎችበተለያዩኢስላማዊአገሮችእየተካሄዱለቱሪስቶችመስህብየሆኑኢስላማዊቅርሶችመቅረባቸውአልቀረም፡፡ይሁንናበኢስላማዊመንግሥታትአገሮችያሉቅርሶችሁሉኢስላማዊናቸውማለትአይደለም፡፡ሙስሊምናሙስሊምያልሆኑቱሪስቶችምከአገርአገርየሚዞሩትበግንባርቀደምትነትኢስላማዊቅርሶችንለመጎብኘትቢሆንምእንኳን፣ሌሎችንጥንታዊናአስደናቂየሆኑቅርሶችንአይጎበኙምማለትአይደለም፡፡ለምሳሌወደግብፅ፣ወደሶሪያ፣ኢራቅ፣ሊቢያ፣ቱኒዝያ፣ህንድ፣ፓኪስታንናሌሎችምአገሮችየሚጓዙቱሪስቶችቅድመእስልምናየነበሩቅርሶችንእግረመንገዳቸውንሊጎበኙይችላሉ፡፡
ኢስላማዊ ቅርሶች ጥንታዊ መስጊዶች፣ ትልልቅ መድረሳዎች (ኢስላማዊ ትምህርት ቤቶች)፣ ጥንታዊ ቤተ መንግሥት መኖሪያ ቤቶች፣ በመስጊዶቹ፣ በቤተ መንግሥታቱና በየቤቶቹ ያረፉ ውበትና ጌጥ ያላቸው ቅርፃ ቅርፆች፣ በድንጋይ ላይ የተጻፉ ወይም የተቀረፁ ኢስላማዊ መልዕክቶችና ልዩ ልዩ የመጠቀሚያ ቁሳቁሶች፣ መጻሕፍት፣ ሉሆችና መቃብሮች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የተጠቀሱት የቱሪስት መስህብ የሚሆኑ ቅርሶች የሚገኙት በተሟላ ሁኔታ ወይም ሳይሟላ ሊሆን ይችላል፡፡
ቱሪዝምየሆቴል፣የትራንስፖርትናየገበያልውውጥአገልግሎትክፍሉንብቻሳይሆንየቁሳቁስማምረቻኢንዱስትሪውን፣የሪልስቴትዘርፉን፣የባህልልውውጡንናየቱሪዝምኢንዱስትሪሥልጠናትምህርቱን ለማዳበርያስችላል፡፡ምንምእንኳንእንደ አፋርበሚሊዮንየሚቆጠርዕድሜያስቆጠሩየቅድመ ሰው ዝርያቅሪቶች፣የረዥምጊዜዕድሜያላቸውታሪካዊቦታዎችናቅርሶችእንደ አርትአሌያሉህያውቅልጥዓለቶች፣በዓለምየመጨረሻውዝቅተኛሥፍራዎች፣ውብናድንቅየሆኑየተፈጥሮፍልውኃዎች፣በየትኛውምቦታየማይገኙኢስላማዊታሪካዊሥፍራዎችናየመቃብርቦታዎችባይኖራቸውምበጥቂትመቶዓመታትዕድሜያቸውያዳበሯቸውንእንደ አፋርካሉግዛቶችምየዘረፏቸውንሀብትናንብረቶችበማሰባሰብከፍተኛየሆነገቢእያስገኙእንደሆነይታወቃል፡፡የቱሪስቶቻቸውናበቱሪስቶችየሚያገኙትገቢምበየጊዜውበከፍተኛደረጃእያደገነው፡፡
ይህምእውነታየሚያመለክተውበአፋርውስጥከፍተኛየቱሪስትመስህቦችናከፍተኛየቱሪስትገቢየሚያስገኙ ሥፍራዎችመኖራቸውንሲሆን፣እነዚህምሥፍራዎችየተፈጥሮመስህቦች፣የቅሪተአካልቁፋሮየተገኘባቸውሥፍራዎች፣ጥንታዊከተማዎች፣ቤተመንግሥቶች፣መስጊዶች፣የመቃብርሥፍራዎች፣ሙስሊሞችእምነታቸውንመሠረትበማድረግየሚጎበኟቸውቦታዎች፣ለባህላዊወይምእምነታዊሕክምናየሚመጡባቸውሥፍራዎች፣ከተለያዩየአገሪቱክፍሎችለሃይማኖትትምህርትየሚመጡተማሪዎች፣የደንናዱርእንስሳክልሎችናየገበያሥፍራዎችተብለውሊተነተኑይችላሉ፡፡ምንምእንኳንጦርነትእንደ ጥፋትእንጂልማትየማይቆጠርቢሆንም፣ሕዝብበሰላምእንዲኖርያለፈውጥፋትምንእንደሆነበትክክልለመረዳትስለሚጠቅምየጦርነትሥፍራዎችንየቱሪስትመስህብማድረግየራሱየሆነጠቃሚጎንአለው፡፡ከዚህምበተጨማሪየሕዝቡጥንታዊባህልናአኗኗርለማየት፣ለመዝናናት፣ለማጥናትየሚመጡቱሪስቶችየሚመለከቷቸውሥፍራዎችበሰፊውይገኛሉ፡፡
በኢትዮጵያ የሚገኙ ኢስላማዊ የቱሪስት መስህቦች በጥቂቱ
በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙት ኢስላማዊ ቅርሶች የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ በአፋር፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ድሬዳዋ፣ ሲዳማ፣ ሶማሌ፣ ትግራይ፣ ደቡብና በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙትን በከፊል የጎበኘ ሲሆን የተወሰኑትን በደምሳሳውም ቢሆን እንመልከት፡፡
በሶማሌ ክልል ከሚገኙ ጥንታዊ መስጊዶች አንዱ ኢስላማዊ ሥርወ መንግሥት የመሠረቱት የሼህ ዳሩድ ጀበርቲና ሼሕ ዒሳ (የወረሰን ገሌዎቹና) ቁሉንቑል በተባለ ሥፍራ የሚገኘውና ከ1250-1300ዕድሜያለው ሲሆን፣በሺዎችየሚቆጠሩዓሊሞችንያፈራነው።የኢማምአህመድምርጥሙረሺዶችከዚህአካባቢእንደ ሄዱይነገራል።እዚህቦታሼሕዓብዱራህማንአል-ዘይላዒበጣምየታወቁሼሕነበሩ። ከዚህምበተጨማሪየታወቁገጣሚ፣ጀግናጦረኛ፣ከብትአርቢሰይድመሐመድዓብዲልሐሰንየተባሉበእምነትምበጦርመሪነትምየታወቁነበሩ።
በቀላፎ ሼሕ ዓሊ በርኸሌና መስጊዳቸው እንዲሁም በርካታ ደረሶቻቸው ነበሩ። በነገሌ ሼሕ ማሕሙድ ማዕሊል ዑመር፣ በድሬዳዋ ሼሕ ዑመር አዝሃ፣ በጅግጅጋ እነ ሼሕ ዩሱፍ ባህሩ፣ ሼሕ ዓሊ ጉሬ፣ በዋርዴር እነ ሼሕ ሙሐመድ ራቢዕ ይጠቀሳሉ፡፡
በመሠረቱ የሶማሌ ክልል ከሶማሊያ ሪፐብሊክ ጋር የተያያዘ ስለሆነ ሼሕ ዳሩድንም ሆነ ሼሕ ዒሳ፣ እንዲሁም አው በርኸሌ ስናነሳ ሰሜን ሶማሊያ መነሳቷ አይቀርም።
አማራ
በአማራ ክልል ከሚጠቀሱት ውስጥ ጀማ ንጉሥ መስጅድ፣ ገታ መስጅድ፣ መጅት መስጅድ፣ ደባት መስጅድ፣ ደገር መስጅድ፣ አርባ ጫማ መስጅድ፣ ሚሌ/ሀጅ አቡየ/መስጅድ፣ ቢለን/የሼሕ ዓሊ ጅሩ መስጅድ፣ የሼሕ ጀማል ፍል ውኃ/ሀርቡ/፣ ገርዋ መስጅድ፣ አረባቴ የሼሕ ሁሴን ጠገሀዲ መስጅድ፣ የአሏህ ድልድይ /ታሪካዊ ቦታ/፣ ሾንኬ ታሪካዊ መስጅድ፣ የግራኝ አህመድ የመካነ መቃብር ቦታ ይገኙባቸዋል፡፡
አፋር ውስጥ የሚገኙ
ከቢር ሐምዛ የከቢርቶ ጎሳ ሲሆኑ ከጥንታውያን ሀረላ ጎሳ ጋር የሚዛመድ (ቀብሩና ደሪህ አውሳ አፋምቦ ወረዳ ይገኛል) ኩላይ ተብሎ የሚታወቅ ቤተሰብ ሲሆኑ፣ የሳቸውም ዘሮች በአፋር ክልል ውስጥ ተሠራጭተው የእስልምና ሃይማኖትን በማስፋፋት መስጊዶችንና የእስልምና ትምህርት ቤቶችን በማሠራት እንዲሁም የታላላቅ የሃይማኖት አባቶች መቃብሮች እንዳይጠፉ በመንከባከብና እንዲታወሱ በማድረግ ዓይነተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡
ሼክ ቦርዋሊ ቀብሩና ዶሪህ ቦታው አይሳኢታ ቦራውሊ ተራራ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ እነዚህ ሼኮች ወይም ወልዮች በ1770አካባቢየነበሩናቸው፡፡
ቐዛሊናየሐጅዓብዱሰመድከእነዚህምበተጨማሪበዞኑበርካታየሸኾችናየቅዱሳንሲኖሩ፣ከእነዚህምውስጥከዓረቢያየመጡስደተኞችመቃብሮችአሉ፡፡ በዳሎልወረዳኩሉሊበሚባለውሥፍራየሙሐረምናየዓሹራበዓልየሚከበርባቸውሥፍራዎችይገኛሉ፡፡በእነዚህሥፍራዎችምብዙከብቶችንበማረድበዓሎቹንማክበርየተለመደነገርነው፡፡በእነዚህአካባቢዎችየሚገኙመቃብሮችከነጋሺጋር ግንኙነትየነበራቸውእንደሆኑይገመታል፡፡በራጋሊምእንደዚሁሌላየመቃብርሥፍራሲኖርከመቃብሮቹአንዱኦካሻየተባለውየነብዩሙሐመድተከታይነውተብሎይታመናል፡፡
በኩነባውስጥየሼሕሙሐመድአዘንመቃብርየሼሕሙሳዓይድሩስመቃብርዳጋርንወረዳበፈርስደጌይገኛል፡፡በመጋሌወረዳምብዙመስጊዶችናደሪሐዎችሲኖሩከእነዚህምውስጥበዓድዋዘመቻጊዜየነበሩትወሊገዳአንዱናቸው፡፡አኒይናጎጎሎበመባልየሚታወቁደሪሐዎችከመኖራቸውምበተጨማሪከአጼዮሐንስጋርበተደረገውጦርነትየወደቁ አፋሮችታሪካዊሥፍራምይገኛል፡፡
ትግራይ ውስጥ
በሰሜን ወሎ በኩል ከደቡብ ትግራይ ወደ ሰሜን አቅጣጫ ስንጓዝ ራያ ውስጥ ሆጂራ ፎቂሳና ሆጂራ ዋራባዬ፣ ጨርጨር፣ ሐሸንጌ፣ አራ (ዓዲ ጉዶም)፣ ቢሌት (ኩዊሐ አካባቢ)፣ ግጀት፣ ተቐራቂራ (ዓቢ ዓዲ)፣ አጉላዕ፣ ነጃሺ (ውቕሮ)፣ ሼሕ ባህሮ (ሐውዜን)፣ ዓዲርጉድና (ነበለት)፣ ሽሬ አካባቢ ያሉት ኢስላማዊ ሥልጣኔ ለረዥም ዘመናት የተንፀባረቀባቸው ማዕከላት እናገኛለን። ከእነዚህም ውስጥም ከጥቂት ቦታዎች በስተቀር የጥንት መቃብር ሥፍራዎች ሆነዋል። የተወሰኑትም ቢሆኑ እንደሚከተለው ቀርበዋል።
በትግራይ የነበረው የኢስላማዊ ሥልጣኔ መገለጫ በትግራይ ውስጥ በጉልህ የሚታዩት የኢስላማዊ ሥልጣኔ መገለጫ ባህሪያት በትምህርት በሥነ ሕንፃ፣ በንግድ፣ በእርሻ፣ በከብት ዕርባታ፣ በዕደ ጥበብ፣ በሕክምና የሚተነተኑ ሲሆኑ፣ ኢስላም ምን ያህል በትግራይ ሰርፆ እንደነበር ዛሬ በራያ፣ በሐሸንጌ መድረሳዎች፣ በቢለት፣ በአራና በኩዊሐ የተገኙት የመቃብር ድንጋዮች፣ ትግራይ የሚኖሩ ሸማኔዎች፣ ለዓመታት ሳይጠፉ የኖሩ ከሐርላ፣ ከሐረርና ከአርጎባ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ የሕንፃ ፍርስራሾች፣ ከቀይ ባህር ወደቦች ወደ ጎንደር፣ ጎጃምና ወሎ ይነግዱ የነበሩ ሰዎች፣ ገበሬዎችና ከብት አርቢዎች ታሪክ ያስረዳናል። በነበለት፣ በተቐራቒራ፣ በግጀት፣ በራያ ያሉ ታላላቅ መድረሳዎችም የአካባቢውና ከአካባቢው ርቀው የሚመጡ ሕሙማን የሚፈወሱባቸው የጤና ማዕከላት ናቸው። ሙስሊም ሊቃውንት ገበሬዎች መቼ ማረስ እንዳለባቸው፣ ነጋዴዎች በምን ሰዓት መንቀሳቀስ እንዳለባቸው የሰማይ ከዋክብትን ተመልክተው ይመክሩ ነበር።
ሆኖምበትግራይየነበረውንኢስላማዊሥልጣኔበቀላሉማቅረብየማይቻልስለሆነወደፊትበሰፊውለማቅረብጥረትይደረጋል።
ሐረር
ሐረር የምሥራቅ አፍሪካ የኢስላማዊ ሥልጣኔ ምንጭ ናት፡፡ ምንጭ እንድትሆን ያስቻላትም በሌሎቹ የምሥራቅ አፍሪካ የነበሩ ኢስላማዊ ሥልጣኔ አንፀባራቂ ቅርሶች ሲጠፉ ሐረር ጠብቃ በመቆየቷ ነው፡፡ ሆኖም ባለፉት 100 ዓመታት በነበረባት ተፅዕኖ ምክንያት በርካታ ጠቀሚ ቅርሶቿን እንዳጣች ደግሞ እውነት ነው፡፡ ይልቁንም ሕዝቧ ከኖረበት ቀዬ ተፈናቅሎ ወደ ሌላ ሥፍራ ሲጋዝ፣ በከተማ ትርፍ ቤቶችና በመሬት ላራሹ ሕግ ምክንያት ክትትልና ክብካቤ ያደርግላቸው የነበሩ እንደ መስጊዶችና መድረሳዎች ያሉ ቅርሶች ቀስ በቀስ ወደ ወናነት ተቀይረዋል፡፡ ለምሳሌ የአው ቡርቃን ጥንታዊና ውብ መስጊድን በምሳሌ መጥቀስ ይቻላል፡፡
ይህም ሆኖ ሐረር ከሌሎች ክልሎች አንፃር መልካም በሚባል ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ እያንዳንዱ ጥንታዊ ቤት ጥንታዊ መልኩን ጠብቆ እንዲገኝ በተደረገው ጥረት ዛሬ ቱሪስቶች ወደ ጥንታዊ ቤቶች እየሄዱ ይጎበኛሉ፡፡ ጥንታዊ ቤቶቹ የዓሊሞችና የትልልቅ ሰዎች መቀመጫዎች ወዘተ ያሏቸው ከመሆናቸውም በላይ የቁርዓንና የኪታብ ማስቀመጫዎች፣ የመስገጃ ምንጣፎችና ቆጦች ጥንታዊ ቅርሶች ይገኙባቸዋል፡፡ እያንዳንዱ ጎረቤት በግንብ የተከለለ ሲሆን፣ መንገዶቹም በሁሉም አቅጣጫ ወደ አምስቱ በሮች የሚወስዱ ናቸው፡፡ 100 ያህል መስጊዶችን 300 ያህል የታላላቅ ሰዎች መቃብሮችና መቃሞች የሚገኙ ሲሆን፣ እነዚህም በዝርዝር ተለይተው የሚታወቁ ናቸው፡፡ በሐረር ውስጥ አምስት ሙዚየሞች ሲኖሩ ከእነዚህ ውስጥ ሦስቱ መንግሥት የሚያስተዳድራቸው ናቸው፡፡ በሐረር የሚገኙ ጉሊቶች የጎብኝን ስሜት የሚስቡ ሲሆን እነሱም በአምስቱም በሮች ይገኛሉ፡፡
የሐረር ቅርሶች በጂጎል ውስጥ ብቻ ሳይሆን በከተማ ዙሪያና ከከተማዋ ርቀው የሚገኙ ናቸው፡፡ በዚህ ረገድ እነ አውከረሚ፣ አው ሱፊ፣ አው ቡርቃ፣ አው ሐኪም የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ኢስላማዊ ቱሪዝም ማኅበራዊ ሕይወትን የሰዎች ባህሪን፣ ኢኮኖሚያቸውን፣ ፖለቲካቸውን፣ ባህላቸውንና የአየር ንብረታቸውን ሊያጠቃልል ይችላል፡፡ ኢስላማዊ ቱሪዝም ታላላቅ የሃይማኖት አባቶችን መጎብኘትን፣ በሃይማኖት አባቶች ዙሪያ የሚከናወነውን ሊጨምር ይችላል፡፡ ስለሆነም ሐረር ኢስላማዊ ቱሪዝምን ለማካሄድ የሚያስችል ተጨባጭ ሁኔታ አላት፡፡
ስለሐረር ተጨባጭና ረቂቅ ቅርስ በርካታ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ጸሐፍት አስተያየቸውን አሥፍረዋል፡፡ በማሥፈራቸውም ሐረር ዝናዋ በአውሮፓም ሆነ በእስያ በመታወቁም በዓለማችን ዕውቅ የታሪክ ጸሐፊዎች፣ የሥነ ጽሑፍ ሰዎችና ባለሀብቶች ጎብኝተዋታል፡፡ ስለሐረር ኮረብታዎችና ሜዳዎች፣ እንዲሁም ስለሕዝቧም በሰፊው ጽፈዋል፡፡ በርካታ ሐረሪዎችም ወደ ውጭ ሄደው ስለሐረር/ኢትዮጵያ ታሪክ በሰፊው አስረድተዋል፡፡ ይሁንና በእጃችን ያሉት መረጃዎች ውስኖች በመሆናቸው በዚህ ረገድም ትኩረት ሰጥተን በአርኪዮሎጂ ጥናት ጭምር ልንንቀሳቀስ ይገባል፡፡
እነሱም ሐረርለሺሕዓመታትያህልበአፍሪካቀንድአንፀባራቂሥልጣኔእንደነበራትናየሥልጣኔዋየብርሃንጮራም በጥንታዊግዛቷፈንጥቆእንደነበረየሚታወቅሲሆን፣በአሁኑጊዜምየአካባቢዋታሪካዊናባህላዊቅርሶች፣የኅብረተሰብመተኪያየሌላቸውውድተጨባጭናረቂቅእሴቶችበመሆንቀጥለዋል፡፡እነዚህእሴቶችበአሁኑጊዜያለውንናመጪውንትውልድድልድይሆነውየሚያገናኙከመሆናቸውምበላይየኅብረተሰቡንማኅበራዊ፣ኢኮኖሚያዊናባህላዊዕድገትእንዲጨምርያላቸውፋይዳከፍተኛነው፡፡
ሐረርጥንትምሆነዛሬ የምሥራቅኢትዮጵያየንግድመስመርበመሆንበአገሪቱኢኮኖሚልማትየምትጫወተውሚናበጣምከፍተኛነው፡፡ይልቁንምከመካከለኛውምሥራቅከባህረሰላጤውናከሩቅምሥራቅአገሮችጋርለነበረውየንግድትስስርሐረርከፍተኛውንድርሻእንዳበረከተችአያጠያይቅም፡፡በሐረርበኩልከኢትዮጵያለሚወጡጥሬዕቃዎችናወደ አገርውስጥይገቡለነበሩየውጭአገርምርቶችደረቅወደብበመሆንአገልግላለች፡፡አሁንምሆነወደፊትእንደምታገለግልምእናምናለን፡፡
አንድሚሌኒየምወዳስቆጠረውታሪኳመለስብለንስንመለከትም፣ሐረርየአክሱም ሥልጣኔበልዩልዩምክንያቶችበተዳከመበትበሁለተኛውሚሌኒየምመጀመርያ ላይስሟንያገኘችከመሆኗምበላይከአክሱምቀጥላየራሷገንዘብየነበራትክልልናት፡፡በተከታታይለሺሕዓመታትያህልሳትጠፋበመቆየቷደግሞከኢትዮጵያከተሞችግንባርቀደምናት፡፡ዛሬየሰላም፣የመቻቻልናየመተሳሰብናየዕድገትተምሳሌትተብላበዩኔስኮመመረጧዓይነተኛምስክርነው፡፡የሐረርሕዝብበተሻለየኢኮኖሚ፣የማኅበራዊናየፖለቲካደረጃእንደነበረየሚያመላክቱ፣ነገርግንእዚህምእዚያምየተበታተኑየታሪክማስረጃዎችአሉ፡፡
የስልጤ ሕዝብ ረቂቅና ተጨባጭ ቅርሶች
ስልጤንበዞንደረጃእንድትዋቀርካደረጓትምክንያቶችአንዱረቂቅናተጨባጭቅርሷሲሆን፣በዞኑበሁሉምወረዳዎችየታወቁናገናብዙመታወቅያለባቸውበርካታረቂቅናተጨባጭቅርሶችይገኛሉ።ይህንበሚመለከትየተደረጉትጥናቶችግንበጣምአናሳናቸው።
ምንያህልአናሳናቸው? ለሚለውጥያቄመልስባይሆንምለንፅፅርይረዳንዘንድየሐረሪንጥረትእንመልከት።በዚህጽሑፍአዘጋጅእምነትእስካሁንየተከናወነውጥናትበቂባይሆንምየሐረሪንታሪክስንመለከትቢያንስከ300 በማያንሱየአገርውስጥናየውጭአገርጸሐፍትተጠንቷል።የሐረሪባህልቱሪዝምናቅርስቢሮከ2010 እስከ 2013 ዓ.ም. ባለውጊዜብቻከ15 በላይየሆኑመጻሕፍትአስጠንቶናአስተርጉሞለንባብአብቅቷል።ስለሆነምስልጢዞንገናብዙይቀራታል።ይህምሆኖበስልጢዞንከወራቤበመነሳትጥናትቢደረግበጣምብዙመጻሕፍትየሚወጣውሥራለኅትመትማብቃትይቻላል።ዋናውቁምነገርበታሪክ፣በተጨባጭናረቂቅቅርሶችላይትኩረትአድርጎመሥራትለዕድገትአስፈላጊመሆኑንከመረዳቱላይነው።በዚህረገድአዲሱ (የግንባታሥራውእንኳንያልተጠናቀቀው) የወራቤዩኒቨርሲቲባለውሁኔታእየተንቀሳቀሰመገኘቱየሚያስደሰትነው።ነገርግንየዞኑባህልናቱሪዝምቢሮምቁልፍሚናእንዲጫወትማስቻልይኖርበታል።የክልሉምኃላፊነትነው።
ያምሆነይህየዚህጽሑፍአዘጋጅበ2000ላይየኢማምአህመድኢብራሂምመጽሐፍንለመሥራትበአካባቢውሲንቀሳቀስብዙመጠናትያለባቸውንረቂቅናተጨባጭቅርሶችያለብዙአስረጅበዓይኑ ዓይቶተረድቷል።የተወሰነውንምበመጽሐፉአሥፍሯል።ከእነዚህምውስጥየጊስቲዎቹመቃብብ፣የሐጅዓሊዬመድረሳ፣ኻልዋናዶሪሕ፣የአልከሶመድረሳ፣መስጊድናኻልዋይገኙበታል።በየመንገዱያላንዳችክብካቤናትኩረትያልተደረገላቸውበመቶዎችየሚቆጠሩትክልድንጋዮች፣የመቃብርድንጋዮችዕድሜበፅናትማሳለፋቸውንምተመልክቷል።
በስልጢዞንየሚገኙትጥርብድንጋዮችየሴትናየወንድመሆናቸውንየሚያመለክቱሲሆን፣የወንዶቹየወንድብልት፣የሴቶቹደግሞበአራትማዕዘንመጎድጎዳቸውነው።ከዚህምበተጨማሪበአሊቾወሪሮበቃዋቆቱአካባቢየሚገኙትባለሁለትጡትጥርብድንጋዮችኢማምአህመድኢብራሂምፈረሶቻቸውንያስሩባቸውየነበሩናቸውየሚልትውፊትቢኖርም፣በሌላበኩልደግሞጡቶቻቸውበጣምትልልቅየነበሩቅዱሳንሴቶችነበሩስለሚባልበጥርብድንጋዮቹየሚገኙትሁለትየጡትቅርሶችየሴቶቹቀብሮችሊሆኑእንደሚችሉጸሐፊውይገምታል።ድንጋዮቹከዚህምሌላበወቅቱየጥበብሥራከፍተኛእንደነበረየሚያመለክቱናቸው።
በዚህረገድመደረግያለበትጥናትጠለቅያለቢሆንም፣የመቃብርድንጋይበሌሎችእስልምናንበሚከተሉአገሮችእንዴትይቀመጣል? ብሎመጠየቅያስፈልጋል።ከተለያዩልምዶችመረዳትእንደሚቻለውየሙስሊምመቃብርለታይታወይም «የእገሌመቃብርእንዴትያምራል!›› ተብሎእንዲደነቅተደርጎየሚዘጋጅአይደለም።ነብዩሙሐመድም (ሱዓወ) ሁሉምከፍተደርገውየተገነቡመካነመቃብራትከመሬትእኩልእንዲሆንአዘዋልብለውየሚያወሱሐዲሶችአሉ።ይሁንናከጥንታዊታሪክጋርበተያያዘመልኩሰዎችከመሬትከፍያለትልቅሰውከሆነምቤትያሠራሉ።
በስልጢ ዞን እንደሚታየው ሁሉ በመቃብሮች ላይ እንደ ቁልቋል፣ ቅንጭብና የመሳሰሉ ተክሎችን መትከል በኋላም ሌላ ተክል መትከል የተለመደ ሲሆን፣ ይህም ማን እንደተቀበረበት ለማስታወስና ልጆችና ዘመዶች ለሞቱት ሰዎች ጸሎት ለማድረስ በሚመጡበት ጊዜ የዘመዶቻቸው የቱ እንደሆነ ለይተው ለማወቅ እንዲረዳቸው ነው።
ይሁንናበጣትከሚቆጠሩትበስተቀርየብዙዎቹመቃብሮችበተለይምየተቀበሩባቸውታላላቅሰዎችእነማንእንደሆኑየሚታወቀውእጅግበጣምአነስተኛነው።ትልልቅሰዎችሲጠየቁእንኳንመረጃመስጠትያስቸግራቸዋል።ስለዚህምኢትዮጵያውያንሙስሊሞችታሪክበእነዚህመቃብሮችውስጥምስለሚገኝበዚህአቅጣጫምትኩረትመሰጠትይኖርበታል።በተለይሥልጢዎችበዚህረገድየደለበታሪክእንዳላቸውበሚመሰክሩላቸውመቃብሮችፍተሻማድረግይጠበቅባቸዋል።
ይህም ሆኖ ደግሞ አንዳንድ ስለታሪክ ደንታ የሌላቸው (የማያውቁ) እነዚህን የአገርና የዓለም ሀብቶች ካላጠፋን ብለው እንደሚገለገሉም ተገንዝቧል። በመሠረቱ እንኳን ግለሰቦች መንግሥትም እንኳን በተለያዩ ምክንያቶች የማጥፋት መብት የለውም። ቢያጠፋቸውም በታሪክ ተጠያቂ ከመሆን አይድንም። እነዚህ ፀረ ታሪክ ኃይሎች ጉዳት እንዳያደርሱ ነቅቶ መጠበቅ ያስፈልጋል።
የስልጢዞንአንዲትአነስተኛሥፍራልትሆንትችላለች።ነገርበውስጧብዙየታሪክመረጃዎችአሉ።ለጊዜውያልጠቀስኳቸውነገርግንጨፍግገውየሚገኙመረጃዎችአሉ።ለምሳሌስለጡፋሐይቅናስለ ጨዋማሥፍራውብዙመነገርይችላል።የአንዳንድጸሐፍትሥራዎችበመስክጥናትላይየተመሠረተባለመሆኑወደአሰብወስደውታል።ስለ ገርቢበሮየተባለነገርየለም።በሚቶ፣በሀላባ፣በወለኔስላሉትድልብየታሪክመረጃዎችአልተነኩም።ስለመልክዓምድራዊአቀማመጧናስለአየርንብረቷአልተወሳም።
ሆነም ቀረ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ አዲስ የታሪክ ትኩረት አቅጣጫ ነው የሚለው ስልጢ/ስልጤ ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ ጥንታዊ ግዛቱ እስከ የት እንደነበር፣ በሰበበ ገን ስልጤ ሐጅ ዓልዬ ዑመር አል-በርበር በስልጤ ዞንና በአካባቢው የሚገኙ በርበሬ፣ ማረቆ፣ እነቆር፣ ሶሌና የሚሉ ስሞች በአፈ ታሪኩ መሠረት ከሞሮኮ ጋር ይያዙ እንደሆነ፣ ወራቤ የሚለው ቃል ከየትኛው ቃል ሊገኝ እንደሚችልና በተለያዩ የመረጃ ምንጮች እንዴትና ምን ያህል እንደተጠቀሰ መመርመር አለበት፡፡
በአካባቢው መዳሰስያለባቸውበርካታነገሮችናቸው።ሆኖምሐረሪዎች፣ስልጢዎች፣ወለኔዎች፣አርጎባዎች፣ወርጅዎች፣ዛዮችጋፋቶችየሚገናኙባቸውየታሪክመስመሮችስላሉያንንየደበዘዘመስመርማድመቅያስፈልጋል።የታሪክክፍተትንለመሙላትጥረትማድረግይገባል።ይህደብዛዛመስመርከደመቀሌላበጎኑየሚገኙነገርግንለጊዜውየማይታዩመስመሮችመከሰትይጀምራሉ።የእያንዳንዱማንነትእየጎላይመጣል።
ቅርስን ለመጠበቅ መደረግ የሚገባቸው መሠረታዊ ነገሮች
በአገራችን ኢስላማዊ ታሪክን ለማጥናትና እስካሁን የአንድ ወገን ታሪክ ሆኖ የቆየውን አመለካከት ለመቀየር የሚችሉ ረቂቅና ተጨባጭ ቅርሶች ቢኖሩም፣ በተደጋጋሚ ለማውሳት እንደተሞከረው እስካሁን ድረስ ትኩረት ሳይሰጠው ቆይቷል፡፡
በአካልየሚገኙምሆኑፍርስራሽጥንታዊመስጊዶች፣ መድረሳዎችና የዓሊሞች መኖሪያ ቤቶችየትእንደሚገኙናበምንሁኔታላይእንደሚገኙተለይቶክብካቤናዕድሳትሊደረግላቸውይገባል፡፡
ጥንታዊ የእጅ ጽሑፎች (ቁርዓኖች፣ ሌሎች ኪታቦች፣ መንዙማዎች፣ ሌሎች የትልልቅ ሰዎች የግል ማስታወሻዎች፣ ሰነዶች፣ ወዘተ) በያሉበት እንዲጠበቁና ክብካቤ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡
እንደ ለውህ፣ መጻፊያ ቀሰምና የቀለም አዘገጃጀት አዲሱ ትውልድ ለማወቅ እንዲችል በሚያስችል ሁኔታ ተዘጋጅተው መገኘት አለባቸው፡፡ መቃብሮቻችን ስላልተጠኑና እስካሁን ታሪክን ሲመሰክሩ የነበሩ ቅርሶች መሆናቸው ታውቆ ክብካቤ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡
በአገራችን በርካታ ጦርነት የተደረገባቸው ሥፍራዎች ቢኖሩ፣፣ እነዚህ የጦርነት ሥፍራዎች ኢስላማዊ ታሪክን ለማጥናት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት ትኩረት ሳይሰጣቸው ቆይቷል፡፡ ስለሆነም እነዚህን ቦታዎች በማጥናት ለይቶ ማወቅና ዋናዎቹ ጎብኚዎች በቀላሉ እንዲያውቋቸው የሚያስችል መንገድ መፍጠር ይኖርበታል፡፡
ከኢስላማዊ ታሪክ ጋር የተያያዙ በርካታ ረቂቅ (የማይዳሰስ) ቅርሶች ማለትም አፈ ታሪኮች፣ ትውፊቶች በአጠቃላይ ፎክሎሮች አሉ፡፡ እነዚህም ረቂቅ ቅርሶች ታሪክን ለማጥናት የሚረዱና ወደ ትክክለኛው ምንጭ ለመድረስ የሚያግዙ ናቸው፡፡ ስለሆነም ብስሉን ከጥሬው ለመለየት የሚቻለው እነዚህን ቅርሶች በማጥናት ስለሆነ ትኩረት ሰጥቶ መሰብሰብና ማጥናት እንዲሁም መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡
ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊው አንጋፋ ጋዜጠኛ፣ ደራሲ፣ የእስልምና ጉዳዮች ተመራማሪ፣ እንዲሁም የታሪክ አጥኚ ሲሆኑ፣ ጽሑፉ የእሳቸውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን፣ በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡