በብርሃኑ በላቸው አሰፋ
ከኮንዶሚንየም ተጠራርተው የወጡ ሦስት ሴት ልጆች ሞቅ ያለ ጨዋታ ይጫወታሉ፡፡ ድንገት አንዷ ጨዋታውን ታቋርጥና ስቅስቅ ብላ ታለቅሳለች፡፡ በሁኔታው የተደናገጡ ጓደኞቿ፡-
‹‹ምን ሆነሽ ነው የምታለቅሺው?›› እያሉ ደጋግመው ቢጠይቋትም ማልቀሷን አላቋረጠችም፡፡
‹‹ያስቀየምንሽ ነገር አለ?››
‹‹እናንተ አትፈልጉኝም›› አለቻቸው፡፡ ወዲያውም አንዷ ጓደኛዋ፡-
‹‹እኛ ባንፈልግሽ እቤትሽ መጥተን ለጨዋታ እንጠራሻለን?›› አለቻት በሁኔታው ግራ እየገባት፡፡ ሌላኛዋ ጓደኛ ደግሞ
‹‹እኛ እኮ እንወድሻለን›› ስትላት
‹‹እናትናአባቴግንወንድሜንእንጂእኔንአይወዱኝም፡፡እኔንአይፈልጉኝም፣ሁሉምነገርየሚደረግለትለእሱነው፤›› አለቻቸው፡፡
ይህ መጣጥፍ በቤተሰብ መካከል ባለ አድሎዓዊነት ዙሪያ ላይ ያተኩራል፡፡
አንድ በቤተሰብ ዙርያ የተደረገ ጥናት እንዳረጋገጠው 70 በመቶ የሚሆኑ እናቶች በልጆቻቸው አድልዖ እንደሚያደርጉ አምነዋል፡፡ በሌላ ጥናት ደግሞ በአድሎዓዊነት ዙርያ ጥያቄ ከቀረበላቸው ልጆች መካካል 85 በመቶ የሚሆኑት ከወላጆቻቸው እኩል እንክብካቤ እንደማያገኙ ተናግረዋል፡፡
የወላጅ አድሎዓዊነት የሚባለው እናት/አባት አልያም ሁለቱም ከሌሎች ልጆች በተለየ ለአንዱ ወይም ለሌሎች ልጆች በተከታታይ ልዩ ትኩረት ሲሰጡ ነው፡፡ ከአድሎዓዊነት መገለጫዎች መካከል ረዘም ያለ ጊዜ ከልጅ ጋር ማሳለፍ፣ ትኩረት የተሰጠውን ልጅ መስማት፣ ፍላጎቱን በቀላሉ ማሟላት፣ በተከታታይ ማድነቅ፣ ሲያጠፋም ቅጣቱ እንደ ሌሎች ልጆች አለማክበድ ተጠቃሽ ናቸው፡፡
አንዳንድአድሎዓዊነትንወላጆችሳያውቁሊፈጽሙይችላሉ፡፡ለአብነትም ‹‹ልጄእኔንይመስላል›› በሚልራስንበልጅውስጥማየትየሚፈጥረውየኩራትስሜትበሥውርየአድሎዓዊነትወጥመድውስጥሊከትይችላል፡፡
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ለአድሎዓዊነት መነሻ የምናደርጋቸው ምክንያቶች በአብዛኛው ሰው ሠራሽ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የልጆችን ፀባይ፣ መልክ፣ የትምህርት ውጤት፣ የሥራ ሁኔታ በመነሳት ሊሆን ይችላል፡፡
በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሚከናወን አድሎዓዊነት በልጆች ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ከፍተኛ ነው፡፡ ትኩረት የተነፈገ ልጅ በራስ የመተማመን ስሜቱ ይሸረሸራል፡፡ የጭንቀትና የድበታ ስሜት ይታይበታል፡፡ ማኅበራዊ ግንኙነቱም እየተቀዛቀዘ ይመጣል፡፡ የወላጅ አድሎዓዊ ባህሪ በልጆች መካከል ፀብን ይዘራል፡፡ ይህ አለመግባባት ከዕለት ዕለት በፉክክርና በጭቅጭቅ እየተጠናከረ ወደ ለየለት ጠላትነት ሊያመራ ይችላል፡፡
‹‹እኔ አልፈለግም››፣ ‹‹ተቀባይነት የለኝም›› የሚል የውስጥ አመለካከት ይዘው ያድጋሉ፡፡ ልጆች በወላጆቻቸው ተቀባይነት የማግኘት መሠረታዊ መብት አላቸው፡፡ ይህንን ፍላጎት ለማርካት ልጆች ተገደው በገዛ ወላጆቻቸው ተቀባይነት ለማግኘት አቅም የፈቀደላቸው ሁሉ ያደርጋሉ፡፡
እንኳን ልጆች አዋቂዎችም ሰውን ለማስደሰት የሚያደርጉት ጥረት አይሳካም፡፡ ምክንያቱም የሰውን ፍላጎት ለማርካት መሞከር እንጂ ማርካት አይቻልም፡፡ ልጆች ይህ ሳይካላቸው ሲቀር ደግሞ መልሰው ራሳቸውን የመውቀስ አዝማሚያ ይስተዋልባቸዋል፡፡ እነዚህ ስሜታዊና ሥነ ልቦናዊ ቀውሶች ደግሞ ልጆች አድገው በሥራ ቦታቸው፣ በትምህርት ቤት፣ በትዳር አጋራቸውና በማኅበራዊ ግንኙነታቸው ተፅዕኖው አብሯቸው ሊቀጥል ይችላል፡፡
ጥናቶችእንደሚያመለክቱትአንዳንድ ጊዜበወላጆችቸልተኝነትጥቃቱየደረሰባቸውልጆችላይበጎተፅዕኖምይስተዋላል፡፡በተለይምልጆቹሕይወትንያለማንምድጋፍለብቻቸውእንዲጋፈጡየሚያስችላቸውየአመለካከትቁመናያጎናጽፋቸዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ከሌሎች ልጆች በተሻለ ትኩረት እየተሰጣቸው ያደጉ ልጆች ላይ በተደረገ ጥናት ልጆቹ ስለራሳቸው ያላቸው አመለካከት የተዛባ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በአብዛኛው እነዚህ ልጆች ‹‹ለይገባኛል›› አመለካከት የተጋለጡ ናቸው፡፡ የበላይነት ስሜት ይስተዋልባቸዋል፡፡ እንዲሁም ለሕግና ለሥርዓት መገዛት እንዳለባቸው አይረዱም፡፡ እናም ከጓደኞቻቸው ጋር ባላቸው ግንኙነት ፈተና ውስጥ ይገባሉ፡፡
ጤናማ የወላጅ አድሎዓዊነት መካከል አዲስ ለተወለደ ልጅ፣ ለታመመ ልጅና ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ልጆች ልዩ እንክብካቤ መስጠት ይጠቀሳሉ፡፡ ይህ በሚሆንበት ወቅት ግን ወላጆች ትኩረት ላልተሰጠው ልጅ ለምን ይህንን ልዩ እንክብካቤ የተሰጠበትን ምክንያት በሚገባቸው መንገድ ማስረዳት ይመከራል፡፡
የወላጅ ድርሻ በልጆች መካከል አንድነትን፣ መተሳሰብንና መከባበርን ማዳበር እንጂ ልጆችን በመከፋፈል በትውልዱ መርዛማ አመለካከትን መትከል ሊሆን አይገባም፡፡ ይህ ችግር እልባት እንዲያገኝ በተለይ ወላጆች የአመለካከት ለውጥ ሊያመጡ ይገባል፡፡
እያንዳንዱልጅየራሱየሆነለየትያለማንነትእንዳለውመረዳትያስፈልጋል፡፡የልጆችየማንነትልዩነትሊደነቅየሚገባውእንጂበልጆችመካከልጎጂአድሎዓዊአመለካከትማቀንቀኛሊሆንአይገባል፡፡
ሰላማችሁ ይብዛ፡፡
ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን፣ በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡