Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊሦስተኛው የአፍላዎችና ወጣቶች ጤና ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

ሦስተኛው የአፍላዎችና ወጣቶች ጤና ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

ቀን:

በዓለም አቀፍ ደረጃ 1.8 ቢሊዮን ወጣቶችና አፍላ ወጣቶች ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል በየቀኑ ከ3,000 በላይ የሚሆኑት መከላከል በሚቻል የተለያዩ የጤና ችግሮች ሕይወታቸው እንደሚያልፍ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

የአፍላ ወጣቶች እርግዝና እ.ኤ.አ. በ2000 ከነበረው 16 በመቶ እ.ኤ.አ. በ2016 ወደ 13 በመቶ ዝቅ ብሏል፡፡ ለዚህም ከዚህ ቀደም የተተገበሩት ሁለት የአፍላዎችና ወጣቶች ጤና ስትራቴጂ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡ አሁን ላይ ደግሞ ሦስተኛው የአፍላዎችና ወጣቶች ጤና ስትራቴጂ ይፋ ሆኗል፡፡

በጤና ሚኒስቴር የእናቶች፣ ወጣቶችና ሕፃናት ጤና ዳይሬክቶሬት የወጣቶችና አፍላ ወጣቶች ቡድን አስተባባሪ ኤደን ፍሥሐ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የወጣት ቁጥር ካሏቸው አገሮች የምትመደብ ስትሆን፣ 33 በመቶ የሚሆነው የኅብረተሰብ ክፍሏ ደግሞ ከ10 እስከ 24 ዓመት የዕድሜ ክልል ይገኛል፡፡

- Advertisement -

በወጣቶችና አፍላ ወጣቶች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ መጋቢት 28 ቀን 2014 ዓ.ም. በተካሄደበት ሥነ ሥርዓት ላይ አስተባባሪዋ እንዳሉት፣ ይህንን ቁጥር ከግምት ውስጥ በማስገባት መንግሥትና የልማት አጋሮች አገሪቱ በኢኮኖሚ ዕድገት የላቀ እመርታ እንድታመጣ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

እ.ኤ.አ. በ1994 በካይሮ በተካሄደው የኢንተርናሽናል ፎር ፖፑሌሽን ደቨሎፕመንት ኮንፈረንስ ከተሳተፉት 176 አገሮች መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ የወጣቶችና አፍላ ወጣቶችን የሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት መብትን የተቀበለች አገር መሆኗን አስታውሰዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር የወጣቶችና አፍላ ወጣቶችን ጤና ለማሻሻል ከትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጅት መሥራት ይገባዋል ያሉት አስተባባሪዋ፣ እስካሁን ሁለት የሥነ ተዋልዶ ጤና ስትራቴጂዎችን (ከ2006-2015 እና ከ2016-2020) በመተግበር በኤችአይቪና በሌሎች በሥነ ተዋልዶ ጤና ላይ አበረታች ውጤት ተገኝቷል ብለዋል፡፡

አሁን ሦስተኛው የወጣቶችና አፍላ ወጣቶች ጤና የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ይፋ የተደረገ ሲሆን፣ ሁሉን አቀፍ የወጣቶችና አፍላ ወጣቶች ጤና ችግሮችን (የሥነ ተዋልዶ ጤና፣ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከልን፣ የአደንዛዥ ዕፅ መጠቀምና የአዕምሮ ጤና፣ የሥርዓተ ምግብ፣ ፆታን መሠረት ያደረገ ትንኮሳና ጎጂ ባህላዊ ድርጊቶች፣ ቴክኖሎጂና የወጣቶችና ጤና በሰብዓዊ ምላሽ ወቅት ጉዳዮችን በማካተት በዋናነት የጤናውን ዘርፍ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድን መሠረት አድርጎ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...