Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአዲስ አበባ ባለቤት አልባ ሆነው የተገኙ አውሮፕላንን ጨምሮ ሕንፃዎችና ተሽከርካሪዎች ማስታወቂያ ወጣባቸው

በአዲስ አበባ ባለቤት አልባ ሆነው የተገኙ አውሮፕላንን ጨምሮ ሕንፃዎችና ተሽከርካሪዎች ማስታወቂያ ወጣባቸው

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ የመንግሥት ንብረት አስተዳደር ባለሥልጣን፣ በከተማዋ ሁሉም ክፍላተ ከተሞች በሚገኙ የተለያዩ የመንግሥት ቢሮዎችና አካባቢዎች ለተገኙ ባለቤት አልባ ሕንፃዎች፣ አነስተኛ አውሮፕላን፣ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች፣ የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመሮች፣ ጄኔሬተሮችና ሌሎች ንብረቶች ባለቤቶችን እያፈላለገ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የንብረቶቹ ባለቤት የሆኑ ግለሰቦች ወይም ተቋማት የባለቤትነት ማረጋገጫቸውን ይዘው በቅርብ ንብረቶቻቸውን እንዲወስዱ በጋዜጦች ማስታወቂያ የወጣ ቢሆንም፣ እስካሁን አንድ መቶ ገደማ ለሆኑት እነዚህ ንብረቶች የባለቤትነት ጥያቄ ያነሱ ሁለት ግለሰቦች ብቻ ናቸው ብሏል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ ሥር የሚገኙ የመንግሥት ንብረቶች የማስተዳደር ኃላፊነት ያለው ባለሥልጣኑ በከተማዋ ውስጥ ባሉ የተለያዩ መሥሪያ ቤቶችና አካባቢዎች ባደረገው የባለቤትነት ምዝገባ፣ ብዛት ያላቸው ንብረቶች ያለ ባለቤት ቆመው መገኘታቸውን የባለሥልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሙሉነህ አያና ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ አንድ ንብረት ባለቤት አልባ በሚል በባለሥልጣኑ የሚያዘው አሥርና ከዚያ በላይ ዓመት ያለ ምንም እንቅስቃሴ ቆሞ ሲገኝ ነው፡፡

በዚህ ዓይነት ሁኔታ በከተማዋ ተገኝተዋል ከተባሉት ቋሚ ንብረቶች ውስጥ ዘጠኝ ሕንፃዎች ይገኙበታል፡፡ ባለሥልጣኑ በተለይ የመንግሥት ሕንፃዎች ሲገነቡና ሲታደሱ ክትትል እንደሚያደርግ የገለጹት አቶ ሙሉነህ በዚህ ክትትል ጊዜ ሕንፃዎች ተሠርተው ሳይጠናቀቁ ቆመው ወይም ከተጠናቀቁ በኋላ ታሽገው እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡ አሁን ተገኙ የተባሉት ሕንፃዎችን በዚህ ዓይነት መንገድ ባለሥልጣኑ እጅ ላይ መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡

እንዲህ ዓይነት ሕንፃዎችን የተመለከቱ ጥቆማዎች ከኅብረተሰቡ እንደሚመጡና  በዚህ መሠረት ባለቤትነታቸውን የማጣራት እንደሚደረግ አብራርተዋል፡፡ ባለቤት ነኝ የሚሉ አካላትም የግንባታ ፈቃድና ባለቤትነት ካርታ እንዲያመጡ በጋዜጣ ተጠይቆ ባለቤት ከጠፋ ሕንፃዎቹ ላሉበት ወረዳ ወይም ክፍለ ከተማ ለመንግሥት ሥራ እንደሚውሉ ገልጸዋል፡፡

ባለሥልጣኑ አሁን ማስታወቂያ ካወጣባቸው ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ውስጥ አብዛኛውን ድርሻ የሚይዙት ተሽከርካሪዎች ናቸው፡፡ ተሽከርካሪዎቹ ከሞተር ብስክሌት አንስቶ፣ የተለያዩ የቤት መኪናዎች፣ የሕዝብ ማመላለሻዎች፣ የደረቅ ጭነትና ተሳቢ ቦቴዎች ይገኙበታል፡፡

ከተሽከርካሪ ባሸገር አንድ አነስተኛ አውሮፕላን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት፣ የካ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ዝቅ ብሎ መገኙት ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ አውሮፕላኑ የድሮ መሆኑንና ከጊዜ ብዛት አንዳንድ አካላቱ መጉደላቸውን አቶ ሙሉነህ አክለዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት በዕድገት የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ እያንዳንዳቸው ሁለት ትልልቅ የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመሮችን  የያዙ አምስት ኮንቴይነሮች መገኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት አስተዳደር ግቢ ውስጥ ደግሞ ትልቅ አቅም ያለው ጄኔሬተር መገኘቱን ገልጸዋል፡፡

በአጠቃላይ ንብረቶቹ ባለቤት የሚገኝላቸው ከሆነ እየጠበቀ ቢሆንም፣ ማስታወቂያ የወጣበት ቀነ ገደብ እየተጠናቀቀ ስለሆነ ባለቤት ካልተገኘ በቅርቡ ባለሥልጣኑ ተረክቦ ሊያስተዳደራቸው መሆኑን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

አሁን የተገኙት እነዚህ ንብረቶች የማስታወቂያው ጊዜ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ባለቤት ነኝ የሚል ግለሰብ ሊመጣ ስለሚችል፣ ንብረቶቹ እስካሁን ዋጋቸው አልተተመነም፡፡ ከቀነ ገደቡ መጠናቀቅ በኋላ ንብረቶቹ በአጠቃላይ ዋጋ ተተምኖላቸው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ፣ ካልሆነም እንዲወገዱ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...