Monday, September 25, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየሚትዮሮሎጂ ትንበያ መሣሪያዎች የተገጠሙባቸውን ቦታዎች ክልሎች እየተቀራመቷቸው መሆኑ ተገለጸ

የሚትዮሮሎጂ ትንበያ መሣሪያዎች የተገጠሙባቸውን ቦታዎች ክልሎች እየተቀራመቷቸው መሆኑ ተገለጸ

ቀን:

የአየር ሁኔታ ትንበያን የሚቆጣጠሩ መሣሪያዎች የተተከሉባቸው ቦታዎች፣ በክልሎች ያለአግባብ እየተወሰዱና ጥያቄ እየቀረበባቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ሚትዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ዘመናዊ የአየር ትንበያ መሣሪያዎች በተገጠሙባቸውን ቦታዎች በሕገወጥ መንገድ በሚካሄድ የመሬት ወረራ ምክንያት የመረጃ ጥራት አደጋ ውስጥ መግባቱን የተናገሩት የኢንስቲትዩቱ የዕቅድና በጀት ዳይሬክተር አቶ አሰፋ መኮንን ናቸው፡፡

ዳይሬክተሩ ይህን የተናገሩት የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም. የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሐሙስ ሚያዝያ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውኃ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅተ ነበር፡፡

ክልሎች የተለያዩ ምክንያቶችን በማቅረብ የትንበያ መሣሪያ የተገጠሙባቸውን ቦታዎች ወደ ግል ጥቅም ለማዘዋወር የሚደረጉ ሩጫዎች በሁሉም ክልሎች መኖራቸውን፣ በተለይም በአማራ፣ ሞጣና ባህርዳር፣ በኦሮሚያ ቡሌሆራ፣ ጊኒር፣  በደቡብ ሆሳዕናና ሌሎች አካባቢዎችም መሰል የመሬት መቀራመቶች ለሥራቸው መሰናክል እንደሆነባቸው ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

መሬት ላይ የተገጠሙ መሣሪያዎች ያሉባቸውን ቦታዎች ከፋፍሎ ለሰዎች የማደል ሩጫ በብዙ አካባቢዎች ከሳተላይት ከሚገኘው መረጃ በተጨማሪ መሬት ላይ ጥራት ያለው የትንበያ መረጃ ለማግኘት ከባድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኢንስትቲዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ በበኩላቸው በመላ አገሪቱ ከሚገኙ 1,300 የትንበያ ጣቢያዎች መካከል በክልሎች የሚታየውን የመሬት ግፊያ፣ ቀረጥና ግብር ክፈሉ መባልና ከዚህ ቀደም ያልነበሩ ጥያቄዎች በስፋት እየመጡ በመሆኑ ፓርላማው ትብብር ያድርግልን ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ኢንስትቲዩቱ ከሰው ልጅ ንክኪ ንፁህ የሆኑ፣ ዘመናዊ የሆኑና መረጃን በራሳቸው ሊመዘግቡና ወደ ማዕከላዊ ሰርቨር መላክ የሚችሉ ጣቢያዎችን በመገንባት ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ የጣቢያዎችን ግንባታ ለማካሄድ የሚረዱ መሣሪያዎች ከውጭ የሚገዙ በመሆናቸው በተያዘው ዓመት ካለው አገራዊ ሁኔታ ጋር በተገናኘ ከውጭ ማስገባት ባለመቻሉ በአገር ቤት እንዲመረት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...