በተመሳሳይ ጊዜ በአፕላይድ ሒስትሪና በሥነ ጥበብ ለመመረቅ በቅቷል፡፡ ታሪክና ቅርስ አስተዳደርን በሁለተኛ ዲግሪ መማሩንም ይናገራል፡፡ የመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክን የወሰነው የሽምብራ ቁሬ ጦርነት በተካሄደበት ዱከም ከተማ ነው የተወለድኩትና ያደኩት የሚለው አቶ ወንድወሰን ከበደ፣ ከሥነ ጥበብ በተጨማሪ በታሪክና ቅርስ ዙሪያ የሚነሱ ውዝግቦች ላይ በድፍረት አስተያየት በመስጠትም ይታወቃል፡፡ አባቴ እንዲሁም አጎቴ ሠዓሊ መሆናቸው አነሳስቶኛል የሚለው አቶ ወንድወሰን ፈጠራን ያበረታቱ የነበሩ እንደ ሥዕል፣ የእጅ ሥራ፣ ኑሮ በዘዴ፣ እርሻና ስፖርት የመሳሰሉ ትምህርቶችን ሲማር ማደጉንም ይናገራል፡፡ ስለጥበብ ዘርፉና ከጥበብ ጋር ስለተገናኙ ጉዳዮች ዮናስ አማረ የሠዓሊያን ማኅበር ፕሬዚዳንት ከሆነው አቶ ወንድወሰን ከበደ ጋር ያደረገው ቆይታ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
ሪፖርተር፡- የኢትዮጵያ ሥነ ጥበብ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?
አቶ ወንድወሰን፡- የእኛየኢትዮጵያሥነ ጥበብበቴክኖሎጂየዘመነወይምበቂድጋፍአግኝቶማደግምሆነበዓለምአቀፍደረጃመድረክለማግኘትያልቻለይሁንእንጂ፣ነገርግንእጅግጥንታዊየሚባልታሪክያለውነው፡፡ከድንጋይዘመንጀምሮእስከ እኛዕድሜድረስሥነ ጥበባችንራሱንችሎየዘለቀጥንታዊመሠረትያለውነው፡፡በጊዜ፣በዘመን፣በዘይቤ፣በአስተሳሰብናበዘውግየተለየ ፍልስፍናአለው፣ውበት (ኤስቴቲክ) አለው፡፡ሥነ መለኮታዊ፣ሕክምና፣ሥነ ፈለክ (ህዋ)፣ሌላምሳይንሳዊሐሳቦችንየያዘሥዕልነውያለው፡፡አውሮፓውያንብታያቸውበስምንተኛውወይምበአራተኛውክፍለዘመንላይከእኛጋርየሚነፃፀሩአልነበሩም፡፡እኛበዚያጊዜአልፈናቸውሄደንድንጋይየምናቀልጥበትቴክኖሎጂላይደርሰናል፡፡የድንጋይጥርቦቻችንናቅርፆቻችንላይየምንጽፋቸውጽሑፎችናምልክቶችፍፁምጥበባዊየሆኑናየተመሰጠሩነበሩ፡፡በፖለቲካውም፣ በኢኮኖሚውም፣በሥነ ጥበቡምበጊዜውዓለምንየምንመራበትከፍታላይነበርን፡፡መርከብገንብተንከዓለምጋርስንነግድነበር፡፡ታላላቅየዓለምነገሥታትንከሩቁየሚያሸብርጦር ኃይልገንብተንምነበር፡፡ከአራተኛውክፍለዘመንአልፈንወደኋላበመመለስወደኢተያወይምደሸትሥልጣኔዘመንየነበረውንብናይ፣የኢትዮጵያሥነ ጥበባዊታሪክብዙገናያልታወቁታሪኮችእንዳሉትመናገርይቻላል፡፡
ከሥነ ጥበብ ባለፈ በምሕንድስናው፣ በኪነ ሕንፃው ወይም በከተማ ግንባታው በኩልም ብዙ ሥልጣኔዎች ነበሩን፡፡ የእኛ የኢትዮጵያ ሥነ ጥበብ በአብዛኛው ከኪነ ሕንፃና ምሕንድስናው ጋር የተቆራኘ ነበር፡፡ አክሱም የምታየው ኪነ ሕንፃና የድንጋይ ሥራ በሙሉ በዚያን ዘመን ኢትዮጵያ የተራቀቀ የጂኦሜትሪ ሥራ ላይ እንደነበረች ያረጋግጣል፡፡ በዚያው የአክሱም ዘመን የተሠሩ ሥራዎችን ጌዴኦ አካባቢ ሄደህ ስታይ ደግሞ ዛሬ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ‹‹ሲምፕሊሲቲ›› (ቅለት መፍጠር) የሚባለውን የድንጋይ ሥራ ታገኛለህ፡፡ ቱቱ ፈላ፣ ጨልበ ቱቲ፣ ጨልበ ሰዲ የሚባሉ አፈር ላይ የተተከሉ እስከ 12 ሜትር የሚረዝሙ የድንጋይ ሐውልቶችን ታገኛለህ፡፡ ጥያ፣ ኮንሶ፣ ሌሎችም ቦታዎች ልክ እንደዚሁ ትክል ድንጋዮችን እናገኛለን፡፡ አንዳንዶቹ ትክል ድንጋዮች የብልት ቅርፅ ያላቸው ሊመስሉ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ራሱን የቻለ የባህል፣ የማኅበራዊ መስተጋብርና የፖለቲካ መልዕክት ያላቸው ናቸው ብዙዎቹ፡፡ አሸናፊነትን፣ ትልቅነትን፣ ዘር መተካትንና ሌላም መልዕክትን ይዘው የተቀመጡ ናቸው፡፡ ድንጋዮቹ በሚፈለገው ልክ ተጠርበው መውጣታቸው ብቻም ሳይሆን መሬት ላይ ተተክለው ያን ሁሉ ዘመን መቆየታቸውም አስገራሚ ነው፡፡ ይህን ሁሉ አልፎ የዓድዋ ጦርነትን የተሻገረው ሥነ ጥበባችን በእጅጉ ተቀየረ፡፡ ዓለማዊ ሥዕል ከዚያ በፊት አይሣልም ነበር፡፡ በሌላ በኩል በፊት የሚሠሩት ራሱን የቻለ ወጥ ታሪክ የያዙ (ለምሳሌ ኢየሱስ ክርስቶስን ከውልደቱ እስከ ስቅለቱ ያለፈበትን ታሪክ) ሆነው፣ በአሣሣላቸው ብዙ ጥልቀት የሌላቸው ሥራዎች ነበሩ፡፡ ከዓድዋ በኋላ ግን ይህ መለወጥ ጀመረ፡፡ አውሮፓውያን ‹‹ኢምፕሬሽኒዝም፣ ዳይዳኒዝም፣ ማነሪዝም፣ ሒዩማኒዝም፣ ኤክስፕሬሽኒዝም ሪያሊዝም፣›› ወዘተ እያሉ ጥበባቸውን አራቀውታል፡፡ ነገር ግን በእኛ ዘንድ መለኮታዊ ታሪኮችን ለማስተላለፍ የሚረዱ ዝርግ ሥዕሎች አሠራር ላይ ተገድቦ ነበር ሥነ ጥበባችን፡፡ አሣሣላችን ጥልቀት፣ አየር፣ ሚዛን የሚባሉ የአሣሣል መለኪያዎች የማይታዩበት ነበር፡፡ ከዓድዋ በኋላ ንግድ ሲስፋፋ፣ የውጭ ግንኙነታችን ሲያድግና ከተሜነት ሲጨምር በፊት ሃይማኖታዊ ግፋ ቢል ዘውዳዊ ገድሎች ላይ ያተኩር የነበረው ሥነ ጥበባችን በእጅጉ እየተለወጠ መጣ፡፡
ሪፖርተር፡– የኢትዮጵያ ሥነ ጥበብ ጥንታዊ የታሪክ መሠረት ካለው ዛሬ የሚታየው የጥበብ አድናቆትም ሆነ አጠቃቀም በምዕራባውያን ተፅዕኖ ሥር ለምን ወደቀ? በእምነት ተቋማት ጭምር ከውጭ የሚመጡ ሥዕሎችና ቅርፆች ነው ጥቅም ላይ የሚውሉት የውጭ ማድነቅና መጠቀም የተለመደው ለምንድነው?
አቶ ወንድወሰን፡- የከተማ አኗኗር ከዓድዋ በኋላ ሲስፋፋ የሰውም አስተሳሰብ እየተቀየረ መጣ፡፡ በንግድና በዲፕሎማሲ ማደግ የሚገባው የውጭ ባህል ተፅዕኖ ጨመረ፡፡ ወደ ውጭ አገሮች እንደ አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ፣ ጌታቸው ደፈርሳ፣ ዘሪሁን ዶሚኒክ የመሳሰሉና ሌሎችም ሠዓሊያን ወደ ውጭ ለትምህርት መላክ ሲጀምሩ የምዕራባውያኑን አሣሣል በሰፊው ይዘው መጡ፡፡ ከዚያ በፊት የውጭ ሠዓሊያን ወደ አገራችን መጥተው የነበረ ቢሆንም፣ ነገር ግን የጎላ ተፅዕኖ አልነበራቸውም፡፡ ከዓድዋ በኋላ ከውጭው ዓለም ጋር የምንገናኝበት መንገድ በመስፋቱ፣ የሩሲያ 40 አባላት ያሉት የኪነ ጥበብ ቡድን ከጦርነቱ በፊት መግባቱና ከእነሱ ጋር እንደ ጆርጅ ኮሎኮቭ ያሉ ታዋቂ ሠዓሊያን መምጣታቸው፣ ንጉሡንና በዙሪያቸው ያሉ ባለሥልጣናትን ስለ ዘመናዊ የአውሮፓ ሥነ ጥበብ ብዙ መረጃ የሰጣቸው አጋጣሚ ሊባል ይችላል፡፡ ኮሎኮቭ ንጉሡንና ንግሥቲቱን መሣሉ የእኛ ሠዓሊያን ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ አይቀርም፡፡ በውጭ የተማሩ እንደ አገኘሁ እንግዳ ያሉ ሠዓሊያን የኢትዮጵያን ጥንታዊ አሣሣል ወደ ዓለማዊ ሥራዎች በመቀየር፣ የኢትዮጵያውያንን አሸናፊነትና የጣሊያንን ሽንፈት የሚያሳዩ ፖለቲካዊ መልዕክቶችን ያስተላልፉበት ጀመር፡፡ ከፋሺስት ጣሊያን ወረራ በኋላ በአፄ ኃይለ ሥላሴ ተልከው ውጭ ተምረው የመጡ ሠዓሊያን ሥነ ጥበብን በከፍተኛ ሁኔታ አሳድገውታል፡፡ እንደ እስክንድር ቦጎሲያን፣ ገብረ ክርስቶስ ደስታና ሌሎችም አርቲስቶች የውጭ አገር አሣሣልን ከነባሩ አሣሣል ዘዬአችን ጋር ቀይጠው ብዙ ሥራዎችን አበርክተዋል፡፡ ሠዓሊያኑ በዚያ ዘመን በቡድን የሚሥሉበት ዘመንም ነበር፡፡ እንደዚህም ሆኖ ከውጭው ዓለም ጋር ግንኙነታችን በሰፊው እየተጠናከረ በመምጣቱ የውጭ ተፅዕኖ በሥነ ጥበብ ዕይታችንና አጠቃቀማችን ላይ ጫና አሳድሮብን ቆይቷል፡፡
ሪፖርተር፡– ይህ ታዲያ ምዕራባውያኑ የሥነ ጥበብ ውጤቶቻቸውን ስኬታማ በሆነ መንገድ ከማስተዋወቃቸውና ለገበያ ከማቅረባቸው ጋር የተገናኘ አይደለም ወይ?
አቶ ወንድወሰን፡- አይ አይመስለኝም፣ እነሱ ሥነ ጥበባቸውን የሚሸቅጡት ለንግድ ብቻ ብለው አይደለም፡፡
ሪፖርተር፡– በኢትዮጵያ ጥንታዊ ሥነ ጥበብ ቢኖርም እነሱ ግን በማስተዋወቅም ሆነ በሰፊው ለገበያ በማቅረብ ስለበለጡ ነው የኢትዮጵያን የጥበብ ባህል ያጥለቀለቁት?
አቶ ወንድወሰን፡- ቢዝነስአድርገውታልየምንለውበካፒታሊስትገጹስናየውብቻነው፡፡እነሱከዚያባለፈምሥነ ጥበባቸውንየሚያበለፅጉትናየሚነግዱትለታሪክሽሚያብለውጭምርነው፡፡የእነሱየሥነ ጥበብታሪክያደገውበዚሁለተፅዕኖፍላጎታቸውማስፈጸሚያብለውዘርፉላይበመሥራታቸውነው፡፡
ሪፖርተር፡– የሥነ ጥበብ ውጤቶቻቸውን ለገበያ ብለውም ይሁን ለተፅዕኖ ፍላጎታቸው ማሳኪያ ለሌሎች በሰፊው በማስተዋወቅና በመላክ የሥነ ጥበብ ዕይታም ሆነ በአጠቃቀም ባህል ላይ ተፅዕኖ ፈጥረዋል፡፡ በዚህ ከመቆጨት ባለፈ ከእነሱ ለመኮረጅ ለመማር መፈለግ ተገቢ ጉዳይ አይደለም ወይ?
አቶ ወንድወሰን፡- አገረመንግሥትየሚመራበትየፖለቲካና የአስተዳደርፈሊጥ (ፖሊሲ) አለው፡፡ሌሎችአገሮችመደበኛየተጻፈፈሊጥከማበጀታቸውበፊትባልተጻፈ፣ነገርግንሁሉንምባግባባፈሊጥብዙ የሥነ ጥበብሥልጣኔሲሠሩቆይተዋል፡፡ማይክልአንጀሎየሠራው ‹‹ዘላስትጀጅመንት››የተባለሥራ 500 ካሬሜትር (ግማሽኳስሜዳ) የሚያህልስፋትያለውታላቅሥራነው፡፡ይህንበጣሊያንአገርአንድቄስ/ጳጳስሲያሠራውለገበያብሎሳይሆን፣አገሩንከፈረንሣይወይምከሌላአገርየበለጠሥልጣኔእንዳላትለማሳየትነው፡፡ይህበዘልማድይካሄድየነበረየሥነ ጥበብፉክክርወደ እዚህዘመንሲሻገርደግሞበተጻፈሕግያሳድጉትጀመር፡፡በመንግሥትደረጃሥነ ጥበባቸውንበመደገፍብዙኢንቨስትማድረግበመቻላቸው፣በዘርፉበዓለምደረጃስማቸውለመጠራትበቅቷል፡፡
ሪፖርተር፡– ይህንን እዚህ ማድረግ ለምን ተሳነ ታዲያ?
አቶ ወንድወሰን፡- የእኛአገርጥበብበፖሊሲየተደገፈአይደለም፡፡አገረመንግሥቱከተፈጠረጀምሮበውዝግቦችውስጥነውየቆየው፡፡ትውልድላይበጎተፅዕኖየሚያሳርፉየጥበብዘርፎችንትቶፖለቲካውላይመሥራት ላይነውያተኮረው፡፡የአገረመንግሥቱመሠረታዊትርክቶች (ግራንድናሬቲቭስ) በሙሉአንዱሥርዓትበሌላኛውላይጣትመቀሰርንየሚያስቀድሙናቸው፡፡ለምሳሌየአፄኃይለ ሥላሴመንግሥትከዳግማዊምኒልክመንግሥትበልጦከተገኘወይምልጅኢያሱአጥፍተዋልብሎየሚያምንከሆነ፣በእነሱላይጣትከመቀሰርይልቅከእነሱበጎየሆኑነገሮችንይዞመቀጠልላይማተኮርነበረበት፡፡ከዚያ ይልቅግንመንግሥታቶቻችንየሌላውንስምማጉደፍ (ካራክተርአሳሲኔሽን) ስለሚያስበልጡናሁሌምየኃይልፉክክርላይስላሉበጎውንማስቀጠልአይታያቸውም፡፡
አውሮፓዎቹከረዥምጊዜበፊትይህንችግርፈትተውታል፡፡ሊኦናርዶዳቪንቺበችግርይዟትሲንከራተትየነበረችውየሞናሊዛሥዕልንበክብርይዘዋታል፡፡ሞናሊዛዛሬበተቀመጠችበትፓሪስሉቭ ሙዚየምእኔራሴበአካልሄጄእንዳየሁትበዓመት 50 ሚሊዮንቱሪስትየሚጎበኛትሀብትናት፡፡ለሙዚየሙመግቢያ 20 ዩሮይከፈላል፡፡ 20 ዩሮንበ50 ሚሊዮንበማብዛትሞናሊዛየምታመርተውንገንዘብማስላትትችላለህ፡፡የጋሊሊዮና የኮፐርኒከስዕውቀቶችበጊዜውበሃይማኖትግጭትየተነሳውግዝቢደረጉም፣ዛሬግንለትውልድእንዲሸጋገሩእየተደረገነው፡፡ጊሎቲንየተባለአንገትማረጃመሣሪያያስተዋወቀውናየፈረንሣይሕዝብንበመጨፍጨፍየሚወነጀለውሉዊ 14ኛየዛሬውየፈረንሣይፕሬዚዳንትመኖሪያቤተ መንግሥትንየገነባነው፡፡ የሉዊ 14ኛቨርሳይልሙዚየምበጥብቅይጠበቃል፡፡ያለፈውንታሪኩንከማውደምይልቅየፈረንሣይታሪክአድርገውይጠብቁታል፡፡አውሮፓዎቹከዚህምከዚያምዘርፈውቅርስናየሥነጥበብውጤትበመሰብሰብብዙእያተረፉይገኛሉ፡፡
እኛ አገር ግን ደርግ ሲመጣ የአፄው ነበር ያለውን ቅርስ አወደመ፡፡ ኢሕአዴግ በቦታው ሲተካ ደግሞ ኮሙዩኒስታዊ ቅርሶች የመውደም ዕጣው ደረሳቸው፡፡ ሌላው ቀርቶ የሌኒን በብር የተሠራ ሐውልት ፈርሶ በአንድ ጋራዥ ውስጥ ይገኛል፡፡ ድላችን ሐውልትንም እናውድም ተብሎ ነበር፡፡ ሌላው አገር ነባሩን ጥበብ መማሪያ ሲያደርገው እኛ ጋ ግን የነበረውን ማውደም ባህል በመሆኑ ዘርፉ እንዳያድግ እንቅፋት ሆኖበታል፡፡ የሩሲያን አብዮት የመራው እኮ ጥበብ ነበር፡፡ ቦልሼቪክና ሜንሼቪክ የሚባሉ ሁለቱም ጎራዎች የራሳቸውን ሥነ ጥበብ የማበልፀግ ሥራ በማከናወን ኅብረተሰቡን ለልማትና ለተቃውሞ ያነሳሱበት ነበር፡፡ በእኛ አገር ግን ጥበብ ይፈራል፡፡ እያንዳንዱ ነገር ሳንሱር ይደረግ ነበር፡፡ የሺሕ ዓመታት የሥነ ጥበብ ታሪክ ያላት አገር ዘርፉን የሚመራ ፖሊሲ የላትም፣ የረቡ የሥነ ጥበብ ሥራዎች የሉንም፡፡ የረቡ ሙዚየሞች የሉንም፡፡ የሥነ ጥበብ ቁሳቁሶች ወይም ቅርሶች እንጂ የሥነ ጥበብ ሀብት ብዙም የለንም፡፡ አውሮፓዎቹ በአጭር ዘመን የደረሱበትን ዕድገት እኛ በረዥም ዘመናት ታሪክ ማሳካት አልቻልንም፡፡ አውሮፓዎቹ በጉልበት ቅኝ በመግዛት ባህላቸውንና ሥነ ጥበባቸውን በፊት እንዳስፋፉት ሁሉ፣ አሁን ደግሞ በዲጂታል መንገድ በቴክኖሎጂ የባህል ተፅዕኖ ሰለባ እያደረጉን ነው፡፡
ሪፖርተር፡– ጥበብ ነው ፖለቲካ ላይ የተለጠፈው? ወይስ ፖለቲካው ነው የጥበብ ሸክም የሆነው?
አቶ ወንድወሰን፡- ቅድም ‹‹ግራንድ ናሬቲቭስ›› ብዬ የጠቀስኩትን ልድገመው፡፡ ፖለቲካችን ሁልጊዜ ጥበብን የመሠረታዊ ትርክቶች መተረኪያ አድርጎ ነው የሚጠቀምበት፡፡ ለምሳሌ ባለፉት 30 ዓመታት ፖለቲካችን የሚከተለውን የጨቋኝ ተጨቋኝ ትርክት በጥበብ ውስጥ ደጋግሞ ሲያንፀባረቅ ዓይተናል፡፡ ኢትዮጵያ ከሚለው ለሁሉም ገዥና አስማሚ ከሆነው የአንድነት መንፈስ ይልቅ፣ አንዱ በሌላው ላይ ያለውን ተፅዕኖ ሲያጎሉበት ነበር በጥበብ፡፡ ብአዴን የራሱ፣ ሐውልት ተከለ፡፡ ኦሮሞ የራሱን ሐውልት፣ ትግሬም፣ ሲዳማም የየራሳቸውን ሐውልት እንዲያቆሙ ተደረገ፡፡ ጥበብ በዚህ መሀል ራሱን ነፃ አላወጣም፡፡ የብአዴንን በባህር ዳር የቆመ መሣሪያ ወደ መሬት ያዘቀዘቀ ሐውልት ስታይ፣ አማራን አንገቱን አስደፋነው ለማለት የተፈለገ ይመስላል፡፡ መቀሌ አደባባይ ላይ ስትሄድ ደግሞ በመስዋዕትነት አሸንፈን፣ ጨቋኝ ሥርዓትን ገርስሰን አገር መምራት ችለናል የሚል መልዕክት ያለው የሚመስል ሐውልት ቆሟል፡፡ ኦሮሚያ ስትመጣ ደግሞ አኖሌ ላይ የተቆረጠ ጡት ሐውልት ተሠርቶለት ታገኛለህ፡፡ አዳማ ላይ ደግሞ የሰው አጥንት ቅሪትን ታገኛለህ፡፡ ተጨቁነናል የሚለውን ታሪክ ለማስተጋባት ታስበው የተሠሩ የጥበብ ውጤቶች ተገንብተዋል፡፡ በሐዋሳና በሌሎች አካባቢዎች የተሠሩ ሐውልቶችም ሆኑ ሌሎች የሥነ ጥበብ ውጤቶች የፖለቲካው ዋና መሣሪያ ሆነው አገልግለዋል፡፡
ሪፖርተር፡– ሌሎች የዓለም ከተሞችን ዓይተሃል፡፡ የሥነ ጥበብ ታሪክን አጥንተሃል፡፡ በሥነ ጥበብ ሥራም ለረዥም ጊዜ ቆይተሃል፡፡ የኢትዮጵያውያንን አኗኗርን፣ ከተሞች፣ ባህሎች፣ ማጌጫዎች፣ ገበያዎችን ወይም ሌሎች እንቅስቃሴዎችን ጥበባዊ ለዛ ያላቸው ናቸው ትላለህ፡፡ ለምሳሌ አዲስ አበባ ከአለባበስ ጀምሮ የሚታየው እንቅስቃሴ፣ የሕንፃዎች አሠራር፣ የቀለም ቅባቸውና የመሠረተ ልማቶች አገነባብ ለውበት ብቻ ሳይሆን ለአኗኗር ምቹነት በመጨነቅ የሚሠሩ ናቸውን?
አቶ ወንድወሰን፡-ቅድምእንዳልኩትበሥነጥበብረገድአገራችንፖሊሲአልባናት፡፡የሥዕልናየፎቶግራፍመሣሪያዎችቅንጦትናቸውተብሎ ከፍተኛ ቀረጥተጥሎባቸዋል፡፡አውሮፓውያንዘርፉለትውልድግንባታወሳኝመሆኑንበመገንዘብበጥንቃቄሲይዙትታያለህ፡፡እኛዘንድይህንዓይነትነገርየለም፡፡አለንሊሉቢችሉምእኛአርክቴክቸራልፖሊሲየለንም፡፡ያደጉአገሮችለሥነ ጥበቡከፍተኛድጋፍስለሚያደርጉከዘርፉብዙአትርፈዋል፡፡ፈረንሣይለምሳሌከ12 ሺሕያላነሱሙዚየሞችናቸው ያሏት፡፡እነዚህሙዚየሞችከአሥረኛውክፍለዘመንጀምሮየተገነቡበቅብብሎሽእየዘመኑለዚህትውልድየደረሱናቸው፡፡ዋናዋናሙዚየሞቻቸውልትጎበኝስትገባኢትዮጵያንጨምሮከመላውዓለምየዘረፉትንየጥበብውጤትእያስጎበኙገንዘብሲሠሩባቸውታያለህ፡፡እነዚህንቅርሶችያስቀመጡባቸውንሙዚየሞችየሚያደርጉላቸውእንክብካቤቀላልአይደለም፡፡ለመስረቅና ለማበላሸትቀርቶቀርበህመንካትአትችልም፡፡በዲጂታልቴክኖሎጂይከታተሉታል፡፡ጥንታዊሙዚየሞቻቸውዋይፋይተገጥሞላቸዋል፣ሊፍትተሠርቶላቸዋል፣ለጎብኚዎችአመቺመሠረተልማትተሟልቶላቸዋል፡፡ሥነ ጥበብሁልጊዜከተበደሉጎንነውየምትቆመው፡፡በጨቋኝተጨቋኝትርክትብቻበደመነፍስያለፉትንየጥበብቅርሶችአበጥረንሳናይእናጥፋብለንእንነሳለንእንጂ፣ሥነ ጥበብግንየነበረውንታሪክበሀቅሰንዶነውለትውልድየሚያስተላልፈው፡፡
ሠዓሊአገኘሁእንግዳለምሳሌ 12 አህዮችገዝተውበከተማው ውስጥመንዳትጀመሩ፡፡ባለሥልጣናትተደናግጠውየተከበሩትየጥበብሰውያበዱመስሏቸውጠየቁ፡፡ምንድነውሲባሉግንጉዳይልጭንበትነውብለውበአሽሙርመንግሥቱንናየወቅቱንተሿሚ 12 ሚኒስትሮችተቹ፡፡ሰውየውፈረንሣይተምረውየመጡናየንጉሡንታላላቅሥዕሎችየሚሠሩቢሆኑም፣ጥበብግንኢፍትሐዊነትንበተለየመንገድእንዲቃወሙአደረጋቸው፡፡የጥበብሥራናየጥበብሰዎችሁልጊዜለፍትሕእንደ ወገኑነው፡፡የጥበብሰውስትሆንጠያቂናአገናዛቢብቻሳትሆን፣ፍልስፍናበተሞላውረቂቃዊመንገድሐሳብህንመግለጽምትችላለህ፡፡እኛፖለቲካላይብቻተንጠልጥለን የቀደሙየጥበብሥራዎችንናጠቢባንንየምናወድምከሆነየምናጣውብዙየአገርዕውቀትምጭምርነው፡፡ይህንየተረዱትአገዛዞቻችንጥበብንበእጅጉጨምድደውበመዳፋቸውሥርማፈንነውየመረጡት፡፡የከተማልማትምሆነየአርክቴክቸር፣እንዲሁምየሥነጥበብፖሊሲውእኛ ጋምንነቱአይታወቅም፡፡አሁንየምናያቸውየኢትዮጵያከተሞችኢትዮጵያንይመስላሉወይ? የሚለውበእጅጉያነጋግራል፡፡አዲስአበባለምሳሌየሚኖርባትንሕዝብማንነትታንፀባርቃለችወይ? ታሪኳንየምትገልጽከተማናትወይ? ወይምአዲስአበባ ራሷ አዲስአበባንትመስላለችወይብለንብንጠይቅብዙችግሮችንእንመዘግባለን፡፡ብዙከተሞችየሚስፋፉባቸውአካባቢዎችአሏቸው፡፡በዚያውልክደግሞአሻራቸውተጠብቆከእነ ማንነታቸውእንዲቆዩየሚደረጉየማይነኩቦታዎችምአሏቸው፡፡አዲስአበባለዚህአልታደለችም፡፡በየቦታውበመልሶግንባታናበልማትስምአውዳሚሥራዎችየሚታይባትከተማናት፡፡
አዲስአበባበዓለማችንብልጭልጭናወዲያውተሠርተውለዕይታየሚበቁመሠረተልማቶችከሚስፋፋባቸው (ቪካሪየስኧርባንዴቨሎፕመንት) ከሚስተዋልባቸውከተሞችአንዷናት፡፡ኢትዮጵያአራቱም የአየርንብረቶችያሏት፣አዲስአበባምያለኤሲየሚኖርባትየማትሞቅናየማትበርድከተማነበረች፡፡አሁንግንእየተገነቡያሉየአልሙኒየምግጥግጥሕንፃዎችየፀሐይንነፀብራቅየሚጨምሩናወበቅየሚፈጥሩናቸው፡፡በብዙአገሮችየእኛንሥነ ጥበብይዤሄጃለሁ፡፡ብዙየውጭሰዎችበእኛቀለምአቀባብና የአሣሣልውቅርሲደመሙ ዓይቻለሁ፡፡እኛቅኝባለመገዛታችንየራሳችንማንነትበብዙሥነ ጥበባችንመንፀባረቁእንዲወደድአድርጎታል፡፡ነገርግንአዲስአበባከተማንብታያትአገነባባችንብቻሳይሆን፣ቀለምአቀባቡናምልክትአጣጣሉሁሉእኛነታችንንየሚያንፀባርቅነገርየለውም፡፡እኛየምናማትረውየዕለትኑሮላይነው፡፡ያለፈውንጠብቆማቆየትምሆነየመጪውንጊዜአስበንየምንሠራውነገርብዙምየለም፡፡ቀድሞየተሠራነገርታሪክነውቢቆይይጠቅመናልስትለው፣ሳትበላናሳትጠጣየምንታሪክነውይፍረስይልሃል፡፡ያንንምይህንንምሲያጥሩታያቸዋለህ፡፡ወጥነትያለውበትውልዶችቅብብሎሽየሚሻገርሥራየለም፡፡ሥነጥበባችንድጋፍምሆነዕገዛከፖሊሲጀምሮየሌለውመሆኑበብዙመንገዶችጎድቶናል፡፡ዛሬበአኗኗራችንየምናየውየሚረብሽናዝብርዝርቅያለግንባታናአሠፋፈርየዚህውጤትነውእላለሁ፡፡
ሥነጥበባችንብዙድጋፍጎድሎትምባለውየማያበረታታሁኔታእየተሠራ፣ለብዙሰዎችየሥራዕድልመፍጠርየቻለናየራሱንገቢእያስገኘያለዘርፍሆኗል፡፡ሥነጥበባችንበሚገባውልክቢደገፍደግሞወደውጭአገርገበያመውጣትናለአገርኢኮኖሚየሚጠቅምየምንዛሪገቢማምጣትየሚችልነውብዬአምናለሁ፡፡ብዙየተማረናሥራያጣሕዝብባለበትአገር፣ብዙምምርታማያልሆነየዕውቀትምሆነክህሎትዝግጅትየሌለውሰውንበሥራፈጠራስምእየሰበሰቡብርማፍሰስየእኛአገርየሥራፈጠራፈሊጥሆኗል፡፡የፖለቲካጫናይፈጥራልበሚልዕሳቤብቻአሰሱንምገሰሱንምእየሰበሰቡውድየአገርሀብትንማፍሰስየትእንዳደረሰንመገምገምይኖርብናል፡፡የተማረውን፣ዕውቀትናክህሎትየጨበጠውንበጉልበትብቻሊያግዝከሚችለውሰውጋርማቀናጀትናድጋፍማድረግአንዱአዋጭመንገድይመስለኛል፡፡በሌላበኩልደግሞአገርንሊያሳድጉናከፍተኛገቢሊያስገኙበሚችሉ፣ሥነጥበብንጨምሮእንደአርትባሉኢንዱስትሪዎችላይኢንቨስትርማድረግምአዋጭመንገድሆኖይታየኛል፡፡
ሪፖርተር፡– አርቱ (ሥነ ጥበቡ) ኢኮኖሚን እንዴት ይደግፋል የሚለውን በተለያዩ ማሳያዎች ማቅረብ ይቻላል?
አቶ ወንድወሰን፡- በጣምጥሩነው፡፡ለምሳሌ እስራኤልአገር ብትሄድብዙኃኑሕዝብአይሁዳዊነው፡፡ስለኢየሱስክርስቶስታሪክምሆነስለአዲስኪዳንብዙምጉዳያቸውአይደለም፡፡ነገርግንየሃይማኖትሥነጥበብንበፋብሪካደረጃአደራጅተውነውየሚሠሩበት፡፡እስራኤልየገባቱሪስትናየእምነትተጓዥበሙሉበኢየሱስክርስቶስምሆነበሌሎችእምነቶችታሪክላይየተሠሩየጥበብሥራዎችንናምልክቶችንእንዲሸምትያደርጉታል፡፡ይህዘርፍየእስራኤልንጥቅልኢኮኖሚበእጅጉየሚደግፍትልቅመስክሆኗል፡፡እኛንተመልከተን፣በሁሉምሃይማኖቶችታሪክከእስራኤልምሆነከሌሎችአገሮችብዙአንርቅም፡፡የእምነትተቋሞቻችንብዙየሥነጥበብሀብትያላቸውናቸው፡፡ባህልናቱሪዝምሲባልየዘርፉሀብትብዙውበሥነጥበብውጤቶችየሚገለጽእኮነው፡፡ሥነጥበብያፈራውየቱሪዝምሀብታችንበኢትዮጵያበእጅጉብዙነው፡፡ ይህንትልቅየአገርሀብትከማውደምይልቅለምንአናዘምነውም?ለአገርኢኮኖሚገቢማግኛነትለምንአናውለውም?ነውየእኔጥያቄ፡፡አብያተ ክርስቲያናቱ፣መስጊዶቹ፣ጽላቱ፣ሥዕሎቹ፣መጻሕፍቱናሌላውምበሙሉየሥነጥበብሰዎችየቀረፁት፣የሣሉትወይምየገነቡትሀብትነው፡፡ሥነጥበብከሁሉምነገራችንጋርይተሳሰራል፡፡ከባህልአልባሳቶቻችንጀምሮበየዕለትአኗኗራችን የምንገለገልባቸውጀበና፣ድስትናሌላምበርካታቁሳቁስጭምርየሥነጥበብአሻራያረፈባቸውናቸው፡፡ይህንተረድቶናዘርፉንአዘምኖከገበያጋርለማስተሳሰርብዙአይሠራም፡፡
ከተሞቻችን በሙሉ የከተማ ሥነ ውበትና ለመኖሪያ አመቺነታቸውን ታስበው በኪነ ሕንፃ ዕውቀት ተደግፈው የሚሠሩ አይመስሉም፡፡ የተሠራውም ደግሞ ቴሌ፣ መብራት፣ ውኃና መንገድ እየተባለ ወዲያው ሲፈርስ ታያለህ፡፡ በከተሞቻችን መኖር ዕይታን የሚረብሽ ብቻ ሳይሆን የአዕምሮ ሰላምንም የሚያደፈርስ ጭምር ነው አንዳንዴ፡፡ አገራችን እጅግ ከፍተኛ የድንጋይ ሀብት ያላትና ጥንታዊ የድንጋይ አገነባብ ሥልጣኔም የፈነጠቀባት ሆና ሳለ፣ የሚገነቡ ሕንፃዎች ግን በመስታወትና በአልሙኒየም የተለበጡ ናቸው፡፡ ዕይታን የሚረብሹና ሙቀት የሚጨምር ጨረር የሚፈነጥቁ ሕንፃዎችን ታያለህ፡፡ በጎን ደግሞ አረንጓዴ ልማት እያሉ ሲሰብኩ ታያለህ፡፡ ይህ ሁሉ የድንጋይ ሀብት ያላት አገር ውድ የሰሊጥና የቡና ምርት ወደ ውጭ እየላከች፣ ከውጭ አገር አልሙኒየምና መስታወት ማስገባቷ የፖሊሲ መጣረስ ነው፡፡ አዲግራት ልዩ ድንጋይ አለ፣ አምቦም የተለየ የድንጋይ ውበት አለ፣ ኮንሶና ሌላም አካባቢ ልዩ የድንጋይ ውበት አለ፡፡ ይህን ሀብት በራሳችን አገነባብ ለምን አናበለፅገውም?
ሪፖርተር፡– በዘርፉ ያሉትን ሀብቶች በመንከባከብና ጠብቆ በማቆየት ረገድስ እንደ አገር ምን ያህል የተዋጣ ነው የሚለውን ብታብራራልን?
አቶ ወንድወሰን፡- ይህጥያቄምወደፖሊሲጉድለትናወደፖለቲካዊትርክቶቻችንችግርይወስደናል፡፡አገሪቱየቅርስጥበቃናክብካቤፖሊሲበቅጡየላትም፡፡ቢኖራትምበተጨባጭመሬትላይወርዶየሚተገበርነገርየለም፡፡ሌላውየፖለቲካትርክታችንመራዥናቅርስጠልነው፡፡በግለሰቦችትግልናጥረትእንጂብዙውየኢትዮጵያየቅርስሀብትተጠብቆየመቆየትዕድሉየመነመነነው፡፡
ሪፖርተር፡– በመንግሥት ብቻ ሳይሆን በማኅበረሰቡ ውስጥም ሆነ በሚዲያ አካላት አካባቢ ለቅርሶች መጠበቅ አስተዋጽኦው ደካማ ስለመሆኑ መተቸት ይቻላል?
አቶ ወንድወሰን፡- እኔ በሁሉም እርከኖች ችግሮች ካሉ ለመናገር አልፈራም፡፡ ዋናው ችግር ከዕውቀት የሚጀምር ነው፡፡ አገሪቱ በቅርስ ጥገናም ሆነ ጥበቃና እንክብካቤ ይህ ነው የሚባል በቂ ዕውቀት ያለው ባለሙያ የላትም፡፡ ቅርስን መንከባከብ፣ መጠበቅም ሆነ መልሶ መጠገንና ማዘመን እጅግ የዘመነ ቴክኖሎጂ የሚጠይቅ ነው፡፡ በእነዚህ በሁለቱ ላይ ትልቅ ክፍተቶች አሉብን፡፡
ሪፖርተር፡– የዓለም ዋና ዋና ቱሪስት ሳቢ አገሮች ግን ይህን ክፍተት በተለያዩ መንገዶች ሞልተውታል፡፡ እዚህ ለምንድነው መንግሥት ሁሉንም ነገር ካላደረገ የሚባለው? በአንዳንድ አገሮች የቱሪስት መስህብ የሆኑ የቅርስ ሀብቶች ጥበቃም ሆነ አያያዝና ጥገና ለግሉ ዘርፍ በልዩ ኮንትራት ይሰጣል፡፡ ከኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ብዙ ያልተሻሉ አገሮች የረቀቀ ቴክኖሎጂና ዕውቀት ክፍተቶችን በዚህ መንገድ ሲሸፍኑ እየታየ እዚህ ለምን ሁሌም መንግሥት ይባላል?
አቶ ወንድወሰን፡- ጥሩአመጣህልኝ፡፡ውይይታችንንስንጀምርጀምሮፖሊሲእያልኩስደጋግምየነበረውለዚህነው፡፡ፖሊሲዎቻችን፣አሠራሮቻችንወይምሕጎቻችንየግሉንዘርፍየሚጋብዙአይደሉም፡፡የሰይጣንቤትጉዳይንለምሳሌተመልከተው፡፡የአዲስአበባከተማአስተዳደር፣የአዲስአበባባህልናቱሪዝም ቢሮ፣የመንግሥት ቤቶችኮርፖሬሽን፣የቅርስባለአደራቦርድ፣የቅርስጥበቃባለሥልጣን፣እንዲሁምሕዝቡበተለያየፍላጎትየተሠለፉበትጉዳይነው፡፡ይህየመጀመርያውየአፍሪካሲኒማቤትሊባልየሚችልየቅርስሀብትማንበምንሁኔታእንደሚያስተዳድረውሕጉበግልጽአያስቀምጥም፡፡የአዲስአበባባህልናቱሪዝም ቢሮቅርሱይጠበቅእንዳይፈርስብሎ የመንግሥት ቤቶችኮርፖሬሽንንከሷል፡፡የቅርስጥበቃባለሥልጣን በቅርሱላይምንም ዓይነትባለቤትነትየለውም፡፡ቢኖረውምከመፍረስሊያድነውመቻሉንእጠራጠራለሁ፡፡ እኛአገርሥልጣንእንጂየማስፈጸምአቅምየመስጠትችግርአለ፡፡የቅርስባለሥልጣንሰዎችባሉበትእኮብዙቅርሶችየፈረሱባትከተማናትአዲስአበባችን፡፡ብዙቅርሶቻችንበኃይልሲወድሙማንምማስቆምአልቻለም፡፡ፈረንሣይበአካልየማውቀውየሮተርዳምካቴድራልሲቃጠልቅርሱንለማዳንእንደተረባረቡትሁሉ፣ለመጠገንምያሳዩትትብብርየሚገርምነው፡፡ከዩኔስኮጀምሮመላውዓለምናመላውአውሮፓጭምርከፈረንሣይጎንቆመውነበር፡፡እኛአገርውድሀብትየሆኑቅርሶችእየወደሙ፣አንዳንዱበፖለቲካብቻአዕምሮውንመርዞበለው፣ደግአደረገ፣ይፍረስሲልታያለህ፡፡የራስካሳንኢትዮጵያዊምልክቶችንበአርሜኒያናበህንድአርክቴክቸር ተቀምሮየተገነባቤትባለሥልጣናትተውእያሉበአካልቆመውበግሬደርአፍርሰውካልጠፋቦታለኦሮሚያፖሊስኮሚሽንካምፕነትአዋሉት፡፡የሻቃ በቀለወያመኖሪያምተመሳሳይዕጣነውየገጠመው፡፡ብዙሕዝብአይነኩእያለ፣እንዳይፈርስየሚጠይቅየመንግሥትአካልምተቀምጦከሁሉበላይነንየሚሉመንግሥታትግንቅርስንእያፈረሱነው፡፡ለዚህደግሞየገጠማቸውአንዳችምተጠያቂነትየለም፡፡ በሌላአገርቅርሶችላይእንዳሻውየሚፈነጭመንግሥትመኖሩንእጠራጠራለሁ፡፡ከመቶዓመታትበላይያስቆጠረውቡፌደላጋርንመንግሥትነውያፈረሰው፡፡በአዲስአበባችን 70 እና 80 ዓመታትያስቆጠሩቤቶችናቸውየሚወድሙት፡፡ በሌላአገርለወሳኝግንባታእንኳቢፈለግቅርሱንወደ ሌላቦታአስጠግተውይተውታልእንጂ፣አፍርሰውሌላነገርእንገንባአይሉም፡፡በሰፊዋአዲስአበባ 300 የማይሞሉቤቶችናቸውእኮቅርስተብለውየተመዘገቡት፡፡ 300 ቤቶችምንያህልቦታፈጅተውነውካላወደምናቸውበሚልጭፍንየፖለቲካጥላቻየምንነዳው?
ኢትዮጵያየብዙሺሕዓመታትታሪክያላትአገርናት፡፡በመላውአገሪቱያሉቅርሶችንሰብስበንበሙዚየሞችውስጥእናስቀምጥብንል፣እንደፈረንሣይሉቭ ሙዚየምዓይነት 40 ሺሕግዙፍሙዚየሞችንብንገነባምቅርሶቹንከተንአንጨርሳቸውም፡፡ቅርሶቻችንበየግለሰቦችእጅ፣በየመንግሥትተቋማትናበየንግድድርጅቱእጅነውያሉት፡፡እነዚህንሁሉቅርሶቻችንንወጥበሆነሕግናፖሊሲእንዲጠበቁካላደረግንበስተቀር ወደፊት የታሪክምሆነየቱሪዝምሀብትአይኖረንም፡፡እንጦጦሙዚየምሂድ፣በወርቅየተለበጠውንየንጉሡንካባብልሲበላውታያለህ፡፡አዲስአበባሙዚየምሂድናተመልከት፡፡የታላላቆቹሠዓሊያንአገኘሁእንግዳናዕማዕላፍህሩይ 70 ዓመታትያስቆጠሩሥዕሎችከሙዚየምጀርባመሬትላይበጅምላተቀምጠውፀሐይናአቧዋራሲጠጡታገኛቸዋለህ፡፡እነዚህሀብቶችእንደቅርስስላልታሰቡማስቀመጫሙዚየምአጥተውነውለአደጋየተዳረጉት፡፡ይህካቃተታዲያቅርሶቹበየሜዳውከሚወድሙመንግሥትቢያንስጨረታአውጥቶሀብቶቹተሸጠውአገሪቱገቢለምንአታገኝባቸውምያሰኛል፡፡ይህሁሉየሚሆነውደግሞከዕውቀትበተጨማሪፖሊሲናአሠራራችንክፍተትስላለውነው፡፡ቤተመንግሥቱውስጥያለውንጥንታዊውንታአካነገሥትቤተ ክርስቲያንጠቅላይሚኒስትርዓብይአህመድ (ዶ/ር) በ50 ሚሊዮንዶላርበጀትእንዳሳደሱትሰምቻለሁ፡፡ግሪኮችናአርመኖችመጥተውነውያደሱት፣ይህትልቅነገርነው፡፡ማንነቱንሳይለቅለማደስሲባልነውአገሪቱበዘርፉየተማረሰውስለሌላትየውጭባለሙያዎችመጥተውየሠሩት፡፡ለምሳሌእኔቻይናተልኬ ‹‹ካልቸራልፕሪዘርቬሽንኤንድሪስቶሬሽን››የሚባልየአጭርወራትትምህርትተምሬያለሁ፡፡አገሪቱልክእንደዚህወደ ውጭልካያሠለጠነቻቸውባለሙያዎችበቂአለመሆናቸውብቻሳይሆን፣ሸምተውየመጡትንዕውቀትለብዙዎችበማሸጋገርምበኩልሰፊክፍተትአለባት፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለት ቢሊዮን ብር ወጪ አድርገን ቢሮ አሳደስን ይላል፡፡ ሥራው ሲጀመር እኔ በግሌ ፕሮፖዛል ጽፌ የኢትዮጵያ ልጆች በሥራው ላይ ይሳተፉ ብዬ ጠይቄያለሁ፡፡ የዕውቀት ሽግግር ልናገኝበት የምንችልበት አጋጣሚ ነበር፡፡ ህንዶች፣ አርመኖችና ቱርኮች መጥተው ነው የሠሩት፡፡ ሥራው የወጣበት ወጪ ይገባዋል የሚያሰኝ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ሁሉ የአገር ሀብት ፈሶበት ለአገር ልጆች የሥራ ላይ የዕውቀት ሽግግር መሸመቻ መሆን አለመቻሉ ያሳዝናል፡፡ በየመንግሥት ቢሮዎች ተመሳሳይ ብዙ ወጪ የወጣባቸው ዕድሳቶች እየተደረጉ ነው፡፡ የቱሪዝም መስህብ ሊሆኑ የሚችሉ መናፈሻዎችና መዝናኛዎችም እየተሠሩ ነው፡፡ ከእነዚህ ሁሉ የኢትዮጵያ የጥበብ ሰዎች፣ መሐንዲሶችና አርክቴክቶች ተገቢውን የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲያገኙ ካላደረግን ከስረናል ነው የምለው፡፡ ከመቶ ዓመታት በላይ ያስቆጠረውን የሰይጣን ቤት እኔ የምመራው የሠዓሊያን ማኅበር ማንነቱን ሳይለቅ አድሶ ለመጠቀም፣ የሥነ ጥበብ ማሳያ ቦታ ለማድረግ ጥረት ጀመረ፡፡ ነገር ግን ቦታውን ለንግድ ለማዋል ያሰፈሰፉ አካላት ዕቅዱን ወደ ጎን በማለት አሁን ለሱቅ እየሸነሸኑት ነው፡፡ የአፍሪካ ዲፕሎማሲ መዲና በምትባል ከተማ ይህን ጥንታዊ የሲኒማ ማሳያ ለሥነ ጥበብ ማሳያነትና መሸጫነት ብታውል ከዘርፉ ብዙ ልትጠቀም እንደምትችል ቢታወቅም፣ ነገር ግን ዕቅዱን በበጎ ተመልክቶ ለማስፈጸም ብዙ ችግር ነው የገጠመን፡፡ ሌላ ሌላውን ትተን ዲፕሎማቶች ለስብሰባ ሲመጡ ከዚህ ቦታ ሥዕል እንዲገዙ ብናደርግ የሚገኘው ዶላር ቀላል አልነበረም፡፡ ይህ ዓይነቱ ሐሳብ ዕውን እንዲሆን የብዙ ቀና ልቦችን ድጋፍ ይፈልጋል፡፡