Saturday, September 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅበእነዚህ ሆሣዕና በነዚያ ፋሲካ

በእነዚህ ሆሣዕና በነዚያ ፋሲካ

ቀን:

ዛሬ በኢትዮጵያና በምሥራቁ ዓለም የሆሣዕና በዓል እየተከበረ ነው፡፡ ‹‹ሆሣዕና›› የቃሉ መገኛ አራማይስጥ (አራማይክ) ሲሆን፣ ፍቺውም ‹‹አድነን›› ማለት ነው፡፡ በዕብራይስጥም በግእዝም ተመሳሳይ ፍች አለው፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ሐሳብ መሠረት ዓብይ ጾም ካሉት ስምንት ሳምንታት የመጨረሻውና ከፋሲካ በፊት ባለው እሑድ የሚገኘው ሆሣዕና ነው፡፡ የበዓሉ ጥንተ ነገር እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ፣ ኅብረተሰቡ ከልሂቅ እስከ ደቂቅ ‹‹ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም›› በማለት እግዚእን መቀበላቸው ነው።

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት፣ ሆሣዕና እሑድ በሁለት ነገሮች ይዘከራል፡፡ አንደኛው በቅዳሴ ጊዜ ‹‹ያለሕማምና ያለደዌ፣ ያለድካምም ለከርሞም ያድርሰን ያድርሳችሁ›› እያሉ ካህናቱ ዘንባባ የሚያድሉበት ሲሆን፣ ሁለተኛው ካህናቱና ምዕመናኑ በቤተ ክርስቲያኑ ዙርያ የሚያደርጉት ዑደት ነው፡፡ ‹‹በታወቀችው በዓላችን መለከቱን ንፉ›› እያሉ የቅዱስ ያሬድ መዝሙር እየተዘመረ፣ በአራቱም ማዕዘናት ዕለቱን በተመለከተ አራቱ ወንጌላት እየተነበቡ ይከበራል፡፡

ይህ የሆሣዕና በዓል በዓለም ክርስቲያኖች ዘንድ በየዓመቱ የሚከበር ቢሆንም፣ አብያተ ክርስቲያናቱ ከሚከተሏቸው የዘመን አቆጣጠሮች አንፃር የምሥራቅና የምዕራብ በመባባል በተለያዩ ቀናት ያከብሩታል፡፡ የጎርጎርዮሳዊውን ቀመር የሚከተሉት የውጮቹ ካቶሊኮችና የተወሰኑ ኦርቶዶክሳውያን ባለፈው እሑድ ሚያዝያ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ሲያከብሩ የራሷ ቀመር ያላት ኢትዮጵያን ጨምሮ የዩልዮስ ቀመርን የሚከተለው የኦርቶዶክሱ ምሥራቃዊ ዓለም ዛሬ እሑድ ሚያዝያ 9 ቀን እያከበረ ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት ሆሣዕናን ያከበሩት በበኩላቸው ፋሲካን እያከበሩ ናቸው፡፡ ከፎቶዎቹ ሁለቱ ባለፈው ሳምንት በኢራቅ በነነዌ አውራጃ በምትገኘው ቃራቆሽ ከተማ የሚገኙ ክርስቲያኖች ከቤይሩት የመጡት የሶርያ ካቶሊክ ፓትርያርክ ዮናን በተገኙበት ሲያከብሩ ያሳያሉ፡፡ ከተማዋ ከአምስት ዓመት በፊት ዳኢሽ ከሚባሉት የአይኤስ እስላማዊ ኃይሎች እጅ ነፃ መውጣቷ ይታወቃል፡፡ ሌሎቹ ሁለቱ ፎቶዎች ደግሞ ኢትዮጵያዊውን አከባበር ያመላክታሉ፡፡

– ሔኖክ መደብር

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...