Monday, May 29, 2023
- Advertisment -
- Advertisment -

የሐረር ቅዱሳን ሴቶች

በተሾመ ብርሃኑ ከማል

ሐረር ከአዲስ አበባ 517.2 ኪሎ ሜትር ያህል፣ በስተምሥራቅ 280 ኪሎ ሜትር ከቀይ ባህር በስተምዕራብ ርቃ ትገኛለች፡፡ የተቆረቆረችውም ከባህር ወለል በላይ 2,000 ሜትር ያህል ከፍ ብላ ነው፡፡ የስምጥ ሸለቆው በምሥራቅ፣ የደናኪል (አፋር) ግዛት በሰሜን፣ በስተደቡብ ጨፌያማ ሥፍራ በምሥራቅ የሐረር ተራራ ያዋስኗታል፡፡ ሐረር በምሥራቅ፣ በምዕራብ፣ በሰሜንና በደቡብ አቋርጠው ከተለያዩ አካባቢ የሚመጡ የተለያየ ባህልና ማንነት ያላቸው ብሔር ብሔረሰብ አባላት የሚገናኙባትና የንግድ ልውውጥ የሚያደርጉባት ናት፡፡

በተራራ ላይ የተመሠረተችውና ዙሪያ ምላሿ በግንብ አጥር የተከበበችው ሐረር የሐረሪዎች ባህላዊ መኖሪያ ስትሆን፣ ዋልድሮን 1974 ዓ.ም. ማለትም 40 ዓመታት በፊት ለንባብ ባበቃው የኅትመት ሥራው፣ ‹‹የአንድ ከተማ ባህል ያላት›› (ዋልድሮን 1974: 6) በማለት ገልጿታል፡፡ ‹‹የአንዲት ከተማ ባህል›› ማለትም በዚህች ከተማ ተፈጥሮ በዚህች ከተማ የሚኖር አንድ የራሱ ማንነት ያለው፣ ‹‹እኔ ሐረሪ ነኝ›› የሚል ኅብረተሰብ ነው፡፡ ሐረር አንድ ማይል በግማሽ ማይል ስፋት፣ ስድስት በሮችና የጥንት ስማቸውን ያለቀቁ ሠፈሮች ያላት ትንሽ ከተማ ናት፡፡ ሐረሪዎች የሚባሉትም በጁገል ማለትም በድንጋይ ግንብ ዙሪያ ምላሽ በታጠረችው በጥንታዊቷ ሐረር የሚኖሩት ሲሆኑ፣ የሐረር ከተማ የጥንቱና በአሁኑ ክፍለ ዘመን ከግንቡ ውጭ የተሠራው አዲሱ ከተማ ተብሎ ይታወቃል፡፡ የሐረሪዎች ባህላዊ ከተማ በአዲሲቱ ኢትዮጵያ ከሚገኙት ከአሥሩ ክልሎች አንዷ ስትሆን፣ እሷም የመጨረሻዋ አነስተኛ የክልል ዋና ከተማ ናት፡፡

ጁገል የተመሠረተችው ኢትዮጵያን ከቀይ ባህርና ከዚያ ባሻገር በሚያገናኙ የንግድ መስመሮች መካከል ነው፡፡ ሐረር 1520 እስከ 1535 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የነበረች ሲሆን፣ ሁሉን በወዳጅነትና በደግነት አቅፋ የምትኖር እንደነበረች በታሪክ የተረጋገጠ ነው፡፡

ሐረሪዎች እንደ ማኅበረሰብ ራሳቸውን እንዴት ጠብቀው እንደቆዩና ማንነታቸውንና ባህላቸውን ከትውልድ ወደ ትውልድ ሳያቋርጡ ሲያስተላልፉ እንደኖሩ፣ ራሳቸውን ከጥፋት ሲከላከሉ እንደነበሩ ጠልቀን ስናየው ጠንካሮች ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ በዚህ ጽሑፍሐረሪ ሴቶች በማኅበራዊ ኑሮ፣ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና በመንፈሳዊ ልዕልና ያላቸውናን የነበራቸውን ሚና የምንመረምር ሲሆን፣ ይህ ጽሑፍ በካሚላ ጊብስ ጥናትና ምርምር ላይ የተመሠረተ መሆኑን ጸሐፊው ለመግለጽ ይወዳል፡፡

የሐረሪ ሴቶች በፖለቲካው መስክ ያበረከቱት አስተዋጽኦ

ሐረሪዎች እንዴት እንደ አንድ ማኅበረሰብ ራሳቸውን እንዳደራጁ፣ እንደምን ለዘመናት እንደ ማኅበረሰብ  ፀንተው  እንደኖሩ፣  እንደምን ይኸው መሠረታዊ ግንዛቤ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ እንደመጣ፣ በአካባቢው ክልሎችም ሆነ በብሔራዊ ደረጃ የለውጥ ማዕበል ሲጎዳቸው እንደምን እነሱ ተቋቁመውት እንዳለፉ፣ በዚህ ረገድም ባለው ግንዛቤ ለይ ትኩረት ተደርጎ ሲመረመርሐረሪ ሴቶች በታሪክ ከፍተኛ ሥፍራ እንዳላቸው እንገነዘባለን፡፡ በእርግጥምሐረሪ ሴቶች በተለያዩ ወቅቶች አጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ በሚከት የታሪክ ዘመን ሲያልፉ፣ እንደምን በማንነታቸው ፀንተው እንደኖሩ መረዳት ከፍተኛ ምርምር የሚሻ ነው፡፡

በመሠረቱ ሐረሪዎች ማንነታቸውን የሚገልጹበት፣ ታሪካዊ ሒደቶችን የሚተረጉምበት፣ ለዘመናት ታዋቂ አድርጎ ያቆያቸውን ማንነትና ተምሳሌታዊ መገለጫዎቻቸውን እንደምን እንደሚጠቀሙባቸውና ከወቅቱ ፖለቲካዊ ሁኔታ ጋር እየተጣጣሙ እንደገና መገንባትን ስናወሳ ከሴቶች ተሳትፎ ተነጥሎ የማይታይ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ምዕራባውያን ተጓዦችን፣ የታሪክ ጸሐፊዎችን፣ የሰው ልጅ ዘርና ባህላዊ መገለጫዎችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚያጠኑ ተመራማሪዎች (Ethnographic – በሐረሪዎች ላይ ጥናት አድርገዋል፡፡

ሐረር ላለፉት ብዙ መቶ ዓመታት የጋራ መኖሪያ በመሆን ያገለገለችና በሌሎች አካባቢ ማኅበረሰቦች መካከል ልዩነት ይታይ የነበረ ሲሆን፣ ሐረር ግን ሕዝቡን  በንግድና  በእምነት በማስተሳሰር የሰመረ ግንኙነት የሰፈነባት ማኅበረሰብ ፈጥራለች፡፡ሐረሪ ሴቶችብሔረሰቦች መካከል የነበረውን ልዩነት ግለሰቦችን በመቀላቀል/በማዋሀድ፣ እንዲሁም ‹‹የከተማ ሕይወትን እንዲማሩ በማድረግ›› የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ ይልቁንም ቅዱሳኑ (ሴቶችና ወንዶች) የከተማዋን ሕዝብ ሕይወት በማኅበረሰብና በግለሰብ ደረጃ በማጠናከር ረገድ ያላቸውን ሚና ከፍተኛ ሆኖ ይገኛል፡፡

ስለቅዱሳኑና ከቅዱሳኑ ጋር በተያያዘ በየአድባራቱ የሚያከናውነው መንፈሳዊ ተግባር በኅብረተሰቡ ውስጥ የነበረውን የብሔር ብሔረሰብ፣ የኢኮኖሚና የፆታ ልዩነትን አዋውጦ በታሪክ የዘለቀው ሕዝባዊ አመለካከት፣ ዛሬም ቢሆን የፖለቲካዊ ልዩነቱን በተመሳሳይ መንገድ እየፈታው ነው የሚያሰኙ ሁኔታዎች አሉ፡፡ በአብዛኛው በአድባራት ላይ የተመሠረተው የአካባቢው ሃይማኖታዊ ልምድ በፖለቲካው መካከል ያለውን ልዩነት ለማለዘብ ጥረት ያደረገ ሲሆን፣ በዚህ ረገድ ሐረሪ ሴቶች ግንባር ቀደም ሚና አላቸው ብሎ መግለጽ ይቻላል፡፡

የሐረሪ ሴቶች በዚህ ጽሑፍ ወደፊት በዝርዝር እንደሚገለጸው ሁሉ፣ እንደ ማኅበረሰብ ራሳቸው እንዴት በልዩ የሕይወት መስኮች እንዳዋቀሩና ከወቅቱ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ተስማምተው እንዴት አዲስ ግንዛቤ እንዳዳበሩ፣ እንዴት ራሳቸውን እንደሚገልጹ፣ በብሔር ብሔረሰቦች መካከል ያለው ድንበር፣ የብሔር ብሔረሰብ ማንነታቸው ሳያግዳቸው የሚጋሩት ልምድ፣ በተምሳሌታዊ መገለጫ ባህሪያቱ ውስጥ የሚገኙ ወሰኖች የላሉ መሆናቸውን፣ እንዲሁም በሐረሪዎች መካከል በየጊዜው በሚከሰተው የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነት እየገቡ እንዴት እንዳረጋጉት በመጠኑም ቢሆን ለመዳሰስ ይሞከራል፡፡

የሐረሪ ሴቶች የጓደኝነት ቡድን

የሐረሪዎች የሰው ለሰው ግንኙነት ከሌላው ሁሉ ቀድሞ ከሴቶች፣ ማለትም ከእናቶችና ‹‹ቶያ›› ተብለው ከሚጠሩ ከጎረቤቶቻቸው፣ በትልልቅ ሴቶች ‹‹አፎቻ›› ተብለው ከሚጠሩት በሠርግም ሆነ በሐዘን ጊዜ ከሚረዳዱባቸው ዕድሮቻቸው ማኅበራዊ ተቋማት ጋር ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ወጣት ሴቶች የጓደኝነት ማኅበራት ሲኖሯቸው ይኸው የሴት ወጣቶች ማኅበር የተመሠረተው በአንድ ሠፈር ባሉ ሴቶች አማካይነት ሲሆን፣ ዋልድሮን ሴቶች ማኅበራቸውን የሚመሠርቱት እንደ ወንዶች ርቀት ካለው ቦታ መጥተው አለመሆኑና ይህ ዓይነቱን ማኅበር ዓይነተኛ የሴቶች ጓደኝነት ማኅበር አመሠራረት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ይገታዋል በማለት ባቀረበው ጥናቱ አስፍሮታል፡፡ የወጣት ሴቶቹ ማኅበር አባላት የሚሰበሰቡት ከሁሉም በዕድሜ የሚበልጡት ሲሆኑ ያገቡና ያላገቡ ሴቶችን የሚያቅፍ ነው፡፡ 

ቅዱሳን

ሐረር ውስጥ በርካታ የቅዱስ ሥፍራዎች አሉ፡፡ በሐረር ውስጥና በአካባቢው በድምሩ 365 ቅዱሳን ይገኛሉ፡፡ በሐረር ከተማ ብዙ ጊዜ ይኖር የነበረው የካቶሊክ ሚሲዮናዊው ሟቹ አባት ኢሚሌ ፋውቸር በከተማው ውስጥና አካባቢ የሚገኙ ቅዱሳንን ዝርዝር በማጠናቀር በርካታ ዓመታትን ወስዷል፡፡ እሱ የዘረዘራቸውን አጠቃላይ ድምራቸው 147 ሆኖ የተካተቱትን ቅዱሳን፣ ከእነዚህም ውስጥ 137 ወንዶችና ቀሪዎቹ አሥር ሴቶች የሆኑትን እነዚያን ቅዱሳን ናቸው (1991)፡፡ ኢዋልድ ዋግነር፣ የአባት ኢሚሊን ሥራ በመውሰድ ከአወሊያ ጋር ተያያዥነት ያለውን ሰዎች ለመግለጽና ቦታቸውን ለመለየት ሞክሯል፡፡ በድምሩ 135 ቅዱሳንን ይዘረዝራል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ 120 ወንዶች እና 15 ሴቶች ናቸው (1973)፡፡ በመጨረሻም የጌ ኡሱ ምሁር (በአዲስ አበባ የፖለቲካ ማኅበረሰቡ ተወካይ) መሐመድ አብዱራህማን ቆራም የ159 አውሊያ ሰዎችን መዝግቧል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 137 ወንዶች ሲሆኑ፣ 22 ደግሞ ሴቶች ናቸው (1984)፡፡ ከሚላ ጊብስ የተባለች አሜሪካዊት 40 ያህል ሴት አውሊያዎችን አሰባስባለች። ሴት ወልይዎች ዛሬ የወንዝ፣ የዛፍ፣ የመቃብር፣ የቁባ መታሰቢያ የተደረላቸው ሲሆን፣ ሰዎች በሰማቸው በሚጠሩት ሥፍራዎች እየተገኙ ያስታውሷቸዋል። 

ሴት ቅዱሳት ሊቃውንት

ሴት ቅዱሳት ሊቃውንት (የሐረር ቅዱሳት ሴቶች)  ኢናያችም እየተባሉ የሚጠሩ ሲሆን፣  አይ የሚል መጠሪያም አላቸው፡፡   በሐረር ውስጥ ያበረከቱት አስተዋጽኦ በዝርዝር ተጠናቅሮ ባይገኝም፣ እነሱን የሚገልጹ  የታሪክ  ቅርሶች ግን ታላቅነታቸውን  ሲመሰክሩላቸው ይገኛሉ፡፡

እዚህ ላይ መጠቀስና መታወቅ ያለበት ዓብይ ነገር ቢኖር ከቅዱስነት ደረጃ በብዙ የትምህርት ደረጃና በብዙ ውስብሰብ መንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ማለፍ  አስፈላጊ መሆኑን ነው። ስለሆነም ቅዱሳቱ በቁርዓን ዕውቀት የተካኑ፣ ተምረው የሚያስተምሩ፣ ብዙ ሊቃውንትንም ያስተምሩ የነበሩ፣ በመንፈሳዊ መንፈስ በንፅህናና በቅድስና የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት የሚሰጡ ሆነው ሲገኙ የቅዱስነት ደረጃ ይሰጣቸዋል። ለምሳሌ እንደ ዓይ ዓቢዳ ያሉ ታላላቅ ሊቃውንት በመቶዎች የሚቆጠሩ ደረሶች እንደነበራቸው ይታወቃል።

ከሐረሪ ቅዱሳት መካከልም የሚከተሉት ይታወቃሉ 

ሲቲ ለይላ፣ ሲቲ ሳራ      ፣ ሲቲ አይሻሲቲ አሻሻሲቲ አይሻ፣ ሸኻ ኹኚኝ፣ አይ  ኢመያይ፣ አይ ኢማጅ፣ አይ መረይና፣ አይ ማይሮ፣ አይ ረሐን፣ አይ ሸብረፋት፣ አይ ሸያይ፣ አይ ባይላህ፣ አይ ናስሮ፣ አይ አሚራ፣ አይ አሮሐይ፣ አይ ኢታቒላ፣ አይ ዓቢዳ (I)፣ አይ ኩሊያይአይ ኪባቢያይ፣ አይ ኹርፎ፣ አይ ዘሐቂ ኑር፣ አይ ዘናብ፣ አይ ገሲያይ፣ አይ ገዛኩሊያ፣ አይ ጣሀር ፈትሕ)፣ ኡሙ ኮዳ፣ አቢዳ (III)፣ ዩማጁ (ሲቲ፣ አይ፣ ጊስቲ)፣ ዳሀቦ (ሲቲ፣ አይና ጊስቲ)፣ ጊስቲ ኩልሱማ፣ ጊስቲ ካሚላ (ጀሚላ)፣ ፋቲሐ አሚን (ሲቲ፣ አይና ጊስቲ) እና ፋቲማ (ሲቲ፣ አይና ጊስቲ) ናቸው፡፡

መንፈሳዊ ቡራኬ

የቅዱሳንምርቃትበአዲስሕይወትየመጀመሪያጊዜያትላይአስፈላጊእንደሆነተደርጎይቆጠራል፡፡የቅዱሳንምርቃትለአዋጭበመንፈሳዊሥርዓትበሚታዘዘውዝየራአማካይነትበሴቶችዘንድአዲስየጋብቻጥምረትንናአዲስየሚወለድሕፃንንለመጠበቅአስፈላጊነውተብሎይታሰባል፡፡በቀዳሚነትበሴቶችተነሳሽነትአማካይነትበእነሱላይበተጣለውባህላዊትዕዛዝላይነውእነዚህየሕይወትዑደትሁነቶችእንደመንፈሳዊሥነሥርዓትየሚታዩት፡፡የመንፈሳዊሥርዓትሒደቱየሴቶችንተግባራዊናተምሳሌታዊአክብሮቶችጥረትይጠይቃል፡፡ከመካሃይማኖታዊጉዞመልስለሚከበሩትለሀራስጋር፣ለበለጩጋርናሀጃጅንጋርዝግጅቶችለተሳታፊዎችሁሉናእነሱዝየራሲያደርጉለቅዱሱእንደሥጦታለሚወስዱትሁሉየሚሆንምግብየሚያዘጋጁትሴቶችናቸው፡፡

ከሠርግ ሥነ ሥርዓት በፊት ቅዱስ ሥፍራዎችን መጎብኘት

ከሠርግሥነሥርዓትበፊትቅዱስሥፍራዎችንመጎብኘትሠርጉከመደረጉአንድሳምንትበፊት፣በቅዱሱየተቀደሰሥፍራእጅግአስፈላጊጉብኝትይደረጋል፡፡በዚህጊዜምየወደፊቶቹሙሽሪትናሙሽራውእናቶችከአይአቢዳስኬታማየሠርግሥነሥርዓትናለዘላቂናፍሬያማጋብቻእንዲሆንላቸውምርቃትለማግኘትሲሉወደተቀደሰሥፍራበመሄድነፃጉብኝትያደርጋሉ፡፡ይህሁሉምሴቶችሌላውቀርቶአዋጭንጎብኝተውየማያውቁትእንኳንቢሆኑዝየራንወደፊትለሚመጣውየወንድ፣ወይምየሴትልጃቸውበለጩጋርየተሳካእንዲሆንአስፈላጊነውብለውይቆጥሩታል፡፡ለዚህሁነትጠቃሚነትዕውቅናመስጠትለሁሉምማኅበረሰብበመሆኑየሠርግሥነ ሥርዓቶችንለማካሄድምመሠረትነው፡፡

በተለምዶ ሐረሪ በሌሎች ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች በእህቶቿ፣ በእናቷ ወይም በጓደኞቿ ታጅባ የምትመጣ ሲሆን በዚህ ጊዜ ሥጦታ ይይዛሉ፡፡ ይዘዋቸው የሚመጡት ሥጦታዎችም ሲሪ ቡን፣ ቋህዋህ፣ ወተት፣ ማር፣ ሙዝ፣ ጫት፣ ዕጣንና ገንዘብን ያጠቃልላሉ፡፡ የሚመጡት ቅዳሜ ቀን ነው፡፡ ምክንያቱም ቅዳሜ የአይ አቢዳ የዝየራ ቀንና የሠርጉ ሥነ ሥርዓት የመጀመርያ ይፋዊ ቀን ስለሆነ ነው፡፡

አብዛኛው የሠርጉ ሥነ ሥርዓት ተግባር የሚያተኩረው በባህላዊው ሥርዓት እንዲሟሉ ስለሚፈለጉ የምግብ ዓይነቶች፣ ሁሉም የሙሽሪትና የሙሽራው እናቶች የሴቶችን አፎቻ ጥረቶች መመዝገብ ነው፡፡

ለሙሽሪትና ሙሽራው እናቶች ሽግግሩ በሕይወት ዘመናቸው ያገቡ ልጆቻቸውን ለማየት ብዙ ጊዜያት የሚሄዱ መሆናቸው ነው፡፡ እያንዳንዱ ጋብቻ ለእነሱ ስኬት ነው፡፡ ልጆቻቸውን በስኬት ለማሳደጋቸው ማረጋገጫ፣ ለሕፃኑ ያላቸው ኃላፊነት እየቀነሰ መሄድ፣ ያላቸውን አቅም አያት ለመሆን አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ሁሉ ስኬት ነው፡፡ የዚህን የሽግግር ጊዜ አስፈላጊነት ዕውቅና በመስጠት እያንዳንዷ እናት በራሷ ግቢ ውስጥ ትቆያለች፡፡ ቢያንስ እስከ አራት ቀናት በሚደረገው የጫጉላ ቤት ወይም በአሮዝ ጋር ዝግጅት ድረስ ከግቢዋ ደፍራ አትወጣም፡፡

ከዝየራሥጦታ ጋር የሚደረጉ ጉብኝቶች

ለማኅበረሰቡ አባላት ለቅዱሱና ለቅዱስ ሥፍራው ያለው ማኅበራዊ ጠቀሜታ ይበልጥ የሚታወቀው፣ በቅዱስ ሥፍራዎች ተጨባጭ ሁኔታ በሚደረጉ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች አማካይነት የሚደረገው ምልከታና ተሳትፎ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ በቅዱስ ሥፍራው የሚደረገው ተግባር፣ የማኅበረሰቡ አባላት መስተጋብር፣ ሙሪዶችና ጃማዎችና ቅዱስ ናቸው፡፡ ቅዱሳኑ  ያሉበት ቦታ ማንነትና አስፈላጊነት (ጠቃሚነት) እንዲታወቅ የሚያደርገው የቅዱሱ ንቁ አከባበር፡፡ ቅዱሱ ሕይወት ያለውና ተፅዕኖ አሳዳሪነቱን እንዲጠብቅ የሚያደርገው፣ እናም ቀደም ሲል ያልነበረው ይህ መረጃ ነው፡፡ አሁን እየተመዘገበ ያለው፡፡

ዝየራየማኅበረሰቡአባላትቅዱሳኑንየሚቀርቡበትመንገድነው፡፡ይህየሚከናወነውምወደቅዱስሥፍራዎችየሚደረገውየጉብኝትተግባር፣ይህየሚጠይቀውተግባርምየሚሰጡሥጦታዎችበቀጥታቅዱሱሥፍራላለበትቦታወይምቅዱስሥፍራውሙሪድካለውለሙሪዱበሚሰጡ (ብዙዎቹትንንሽቅዱስሥፍራዎችሙሪድየላቸውም) አጠቃላይተሳትፎዎችነው፡፡በቅዱስሥፍራየሚደረግተግባርበተለይየሚያተኩረውሥጦታዎችንበመስጠትዙሪያ፣በቦታውላይለሚገኙትማከፋፈል፣ተገቢበሆነበትቦታምበሃይማኖታዊአከባበርወይምልምድላለውግለሰብ፣ይህምማለትበትልልቅቅዱስሥፍራዎችሙሪዱወይምበቅዱስሥፍራውየሚገኝሁሉይሆናል፡፡በዋናነትስለቅዱሱ ያለውትውስታተጠብቆየሚኖረውበዝየራአማካይነትነው፡፡

ማጠቃለያ

ኢትዮጵያ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የ2014 ዓ.ም. የዒድ በዓልን በአገራቸው እንዲያከብሩ ጠርታለች፡፡ የግብዣው መሠረታዊ ዓላማ ኢስላማዊ ቱሪዝምን ከማስፋፋት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ሐረሪ ክልልም ይህን የታሪክ አጋጣሚ ተጠቅማ ኢስላማዊ ቱሪዝምን መሠረት ያደረገ እቅስቃሴ በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችና የኢትዮጵያ ወዳጆች እጅ ለእጅ ተያይዘው በጋራ ስሜት የሚከበሩበትን በዓል በክልል ደረጃ በማስተባበር በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው፡፡ የሐረሪዎች የክልል ደረጃ እንቅስቃሴ የተቀሩት ኢትዮጵያውያን፣ የአፍሪካና በሌሎችም አኅጉሮች ያሉ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ እንቅስቃሴ አካል እንደሆነ አያጠያይቅም፡፡

ሐረሪዎች የራሳውን እምነት፣ ልምድና አስተሳሰብ ይዘው በፍቅርና በመተሳሰብ የሚኖሩባት ክልል መሆኗ ራሱ ለዕድገትና ለልማት ከፍተኛ ግብዓት መሆኑን ከግምት በማስገባት በሚቀጥለው ዒድ አልፈጥር በሐረር ውስጥ የበለጠ መቀራረብ፣ መግባባት፣ መተሳሰብ የሰፈነባትና ለተፋጠነ ልማት ተምሳሌት እንደሚያደርጓት ተስፋ ይደረጋል፡፡

የሐረር ሕዝብ የሰሜኑና የደቡቡን፣ የምሥራቁንና የምዕራቡን ኢትዮጵያ መገናኛ ድልድይ በመሆንም የእርስ በርስ ትስስሩን የበለጠ አጠናክሮታል፡፡ የጋፋት፣ የአርጎባ፣ የሐርላ፣ የዶባ፣ የበለውና የሐረሪ ሕዝቦች ከሰሜኑ የትግራይና የአማራ ሕዝብ ጋር ከምዕራብ የሐድያና የስልጤ ሕዝብ ጋር፣ ከምሥራቅ ከኦሮሞ፣ ከአፋርና ከሶማሌ ሕዝብ ጋር ያላቸው አንድነትም ለዚህ ዓይነተኛ ምስክር ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ አቅጣጫም መዳሰስ ያለባቸው የሕዝብ ማንነት መገለጫዎች የማጥናቱ ነገር በቸልታ ሊታይ አይገባውም የሚል እምነት አለኝ፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊው አንጋፋ ጋዜጠኛ፣ ደራሲ፣ የእስልምና ጉዳዮች ተመራማሪ፣ እንዲሁም የታሪክ አጥኚ ሲሆኑ፣ ጽሑፉ የእሳቸውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን፣ በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡

spot_imgspot_img
- Advertisment -

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

Related Articles