Saturday, June 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊማኅበረሰቡ ያልተገነዘበው የፓርኪንሰን ሕመም

ማኅበረሰቡ ያልተገነዘበው የፓርኪንሰን ሕመም

ቀን:

ትናንት ሲቦርቁ፣ ቁልቁለት ሲወርዱና አቀበት ሲወጡ ደከመኝ ሰለቸኝ ያላሉ እግሮች ሲዝሉ፣ እርፍ ጨብጠው ያርሱ፣ ይኮተኮቱ፣ ጠመኔ ይዘው የዕውቀትን አዝመራ ሲዘሩ፣ በሞቴ ብለው ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ሲያጎርሱ የነበሩ እጆች መሥራት ሲሳናቸው፣ ርቱዕ አንደበታቸው ጨዋታን አድምቆ ሲቃን የፈጠረ፣ የተጣላን መክሮና ገስጾ ያስትረቀ ያዜመና የዘመረ፣ አዛን ያሉ፣ ዱዓ ያደረጉ ዛሬ ሐሳብን ማውጣት ሲሳናቸውና ሲተሳሰሩ ማየት እየተለመደ መጥቷል፡፡

ለእንዲህ ዓይነት ጉስቁልና የሚዳርገው፣ የሚያንቀጠቅጠው፣ ዘገምተኛ የሚያደርገው፣ የሰውነት መግረርና ሚዛን የሚያስተው፣ ከእንቅስቃሴ ጋር ያልተገናኙ ድብርት፣ እንቅልፍ ማጣት፣ ለመጻፍና ለመናገር መቸገር፣ የምራቅ መዝረብረብ፣ የሆድ ድርቀትና የማሽተት ችሎታ የሚቀንሰው የጤና ችግር ፓርኪንሰን ነው፡፡

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ ኒውሮሎጂስት ህሊና ዳኛቸው (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ የፓርኪንሰን ሕመም ‹‹ዶፓሚን›› የሚባለውን ንጥረ ነገር በሚያመነጩ ሴሎች ላይ በሚደርስ ጉዳት የሚመጣ የእንቅስቃሴ መቀነስና ተመሳሳይ የሆኑ ችግሮች ሕመም ነው፡፡

- Advertisement -

በዓለም ላይ በፓርኪንሰን ሕመም በአንድ ዓመት ውስጥ ከ100 ሰዎች መካከል 18 ሰዎች እንደሚሞቱ፣ ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ ከሆኑ ከ100,000 ሰዎች ውስጥ 160 ሰዎች ከፓርኪንሰን ሕመም ጋር አብረው እንደሚኖሩ፣ በአሁኑ ጊዜ በዓለም ውስጥ አሥር ሚሊዮን የሚጠጉ የፓርኪንሰን ሕሙማን እንዳሉና፣ ይህም ቁጥር በ2022 በእጥፍ እንደሚጨምር ተናግረዋል፡፡

ወጣቶች በፓርኪንሰን ሕመም የመያዝ ዕድላቸው በጣም አነስተኛ መሆኑን ገልጸው፣ ከ55 ዓመት ዕድሜ በላይ ወይም ዕድሜ 60 ዓመት ከሞላ በኋላ በፓርኪንሰን የመጠቃቱ አጋጣሚ ከፍ እያለ እንደሚሄድ አስረድተዋል፡፡

የፓርኪንሰን ፔሸንትስ ሰፖርት ኦርጋናይዜሽን ኢትዮጵያ ያዘጋጀውና ‹‹ከፓርኪንሰን ሕመም በላይ ጠንካራ ነኝ›› በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የፓርኪንሰን ቀን ሚያዝያ 6 ቀን 2014 ዓ.ም. ታስቦ በዋለው ሥነ ሥርዓት ላይ ህሊና (ዶ/ር) እንዳመለከቱት፣ የፓርኪንሰን ሕመም ምልክቶች በአካል ገጽታ ላይ የሚታዩና ከእንቅስቃሴ ጋር የሚገናኙ ናቸው፡፡

ከእንቅስቃሴ ጋር ከተያያዙ ምልክቶች አንዱ መንቀጥቀጥ መሆኑን ገልጸው፣ ይህንንም 90 ከመቶ ያህሉ የፓርኪንሰን ሕሙማን ላይ እንደሚታይ ተናግረዋል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ግትርነት ነው፡፡ ይህ የመንቀሳቀስ ፍጥነትን በጣም ይገድባል፡፡

የሰውነት አቋምና ሚዛንን ማጣት ሌላ ምልክት ሲሆን፣ ሕሙማኑ የሚወስዷቸው መድኃኒቶች ጥሩ ለውጥ ቢያመጡም፣ የሚዛንን ችግር የመቋቋም አቅም ውስን ነው፡፡

ድብርት ወይም ጭንቀት፣ ግንዛቤን ማጣት፣ በተለይ የሰገራ ድርቀት፣ ማታ ላይ ሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት፣ የእንቅስቃሴ ምልክት በማያሳዩት ላይ የሚከሰቱ ችግሮች ናቸው፡፡

በቂ የሆነ ሕክምና፣ የፊዚዮ ቴራፒ አገልግሎትና ድጋፎች ማግኘት ለፓርኪንሰን ሕሙማን በእጅጉ ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፣ ሕክምናውን በተለያዩ ቦታዎች ማግኘት እንደሚቻል፣ የደም ምርመራና ኤምአርአይ የመሳሰሉ ሕክምናዎች ሕመሞችን ለመለየት እንደሚያስችሉ አስረድተዋል፡፡

የፓርኪንሰን ፔሸንትስ ሰፖርት ኦርጋናይዜሽን ኢትዮጵያ የሥራ አመራር ቦርድ ሊቀመንበር ታሊሞስ ዳታ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ የፓርኪንሰን ሕመም በሁሉም የዓለም ክፍል በእኩል ደረጃ የሚያጠቃ ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ግን በፓርኪንሰን ከሚከሰተው ሕመም በተጨማሪ ስለፓርኪንሰን ሕመም ግንዛቤ ባለመኖሩ በሌላ አገር ከሚኖሩ ሕሙማን በባሰ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

‹ይህም ቢሆን የመረጃ ችግር በመጠኑ በመቅረፉ፣ በአሁኑ ጊዜ በተሻለ ያወቁ የፓርኪንሰን ሕሙማን መኖራቸውን፣ ይህም ሊሆን የቻለው ድርጅቱ ላለፉት አሥር ዓመታት ያህል የፓርኪንሰን ሕመምን በማስተዋወቅና የፓርኪንሰን ሕሙማን የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ በማድረጉ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የድርጅቱ ተደራሽነት አዲስ አበባ ለሚኖሩ ሕሙማን እንደሆነና ከአዲስ አበባ ውጪ የሚኖሩ ሕሙማን በከፋ ሁኔታ ውስጥ እንደሚኖሩም አክለዋል፡፡

ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮና ከከነማ መድኃኒቶች አስተዳደር ጋር በተፈጸመው ስምምነት መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ ከተመረጡ አምስት የከነማ መድኃኒት ቤቶች ጋር በመተባበር ከ400 በላይ ለሚሆኑ የፓርኪንሰን ሕሙማን በነፃ መድኃኒት የሚያገኙበት ዕድል እንደተመቻቸ ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...