‹‹ልዩነታችንን ተቀብለን አገራችን ማፅናት አለብን››
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ በአገራዊ
ጉዳይ ላይ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም. በጅግጅጋ ከተማ በተዘጋጀው መድረክ ላይ
ከተናገሩት የተወሰደ፡፡ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ባዘጋጀው ፓናል ውይይት ላይ
በአገር አቀፍ ደረጃ ሕዝቡን በአገራዊ ጉዳዮች የሚያወያዩ ሌሎች መድረኮች በዋና ዋና ከተሞች እንደሚዘጋጁም አፈ ጉባዔው አስታውቀዋል። ረጅም ታሪክ ያላት አገርና ሕዝብ መሆኗን ለዓለም ለማሳየት ስለ ኢትዮጵያ ያገባኛል የሚሉ አካላት በእነዚህ መድረኮች ተገኝተው ለአገር የሚጠቅሙ አሳቦች እንዲያካፍሉም ጥሪ ቀርቧል።