Thursday, June 20, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በውጭ ገንዘቦች ለሚደረጉ ግብይቶች ግብር የሚከፈለው በወቅቱ በሚኖረው የምንዛሪ መጠን እንዲሆን ተወሰነ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

በውጭ ገንዘቦች ለሚደረጉ ግብይቶች ክፍያ በተፈጸመበት ወቅት በሚኖረው የምንዛሪ መጠን ግብር እንዲከፈል መወሰኑን፣ የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

የገቢዎች ሚኒስቴር የሒሳብ መዝገብ አያያዝ መመርያ ቁጥር 152/2011 በማሻሻል በአዲስ መመርያ ተተክቷል። አዲሱ የሒሳብ አያያዝ መመርያ 176/2014 ሲሆን በብድር አሰጣጥ፣ በካፒታል ማሳደግ ምዝገባና ሌሎችም ሒደቶች ላይ እየተፈጠሩ ያሉ ቅሬታዎችን ለመፍታት እንደሚያስችል፣ በገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ኦዲት ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አበበ ገልጸዋል።

ግብር ከፋዮች ቅሬታ ሲያሰሙባቸው ከቆዩ ጉዳዮች መካከል በውጭ ገንዘቦች የሚደረጉ ግብይቶችን የተመለከቱ መኖራቸውን ገልጸው፣ በተለይም የብር መጠን ከሌሎች አገሮች ገንዘቦች አንፃር መቀነሱ ውል ከተፈጸመበት ጊዜ ጋር ልዩነት የሚፈጥርና ግልጽነት ያልነበረው ነው ብለዋል። 

በመሆኑም በአዲሱ መመርያ ግብር ከፋዮች በውጭ አገሮች ለተደረጉ ግብይቶች የሚጠየቀው ግብር መሠረት የሚያደርገው፣ ክፍያው የተፈጸመበትን ወቅት እንዲሆን መወሰኑን አቶ ብርሃኑ ገልጸዋል።

ከ2011 ዓ.ም. በፊት የወጣው የሒሳብ አያያዝ መመርያ በሥራ ላይ ከዋለ ጊዜ ጀምሮ ከውልና ማስረጃ፣ እንዲሁም ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር ያለው አሠራር የተቃረነ እንደነበር አቶ ብርሃኑ አስረድተዋል።

ከሚያዚያ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ሥራ የገባው አዲሱ መመርያ ከታክስ አስተዳደር ሥርዓት ጋር የሚጣረሱና ወቅቱ ከሚፈልገው የቢዝነስ ተለዋጭነት ጋር የሚጋጩ አሠራሮችን ያስቀረ፣ በብድርና ካፒታል ማሳደግ ምዝገባ ሒደት ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በቀላሉ ለመፍታት የሚያስችል መሆኑን አክለዋል።

በተጨማሪም የክሲዮን ማኅበራት ካፒታል ሲያሳድጉ ምዝገባ ለማድረግ የሚሰጠው ጊዜ በቂ ሳይሆን ሲቀር በግብር ከፋዮች ላይ ጫና የሚያሳድሩ ሆነው በመገኘታቸው ከጠቅላላ ጉባዔውና ከሰነዶች ማረጋገጫ መረጃዎችን በመውሰድ ጊዜ እንዲሰጣቸውና በግብር ውስጥ እንዳይካተትባቸው መወሰኑን አቶ ብርሃኑ አስታውቀዋል።

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች