Wednesday, February 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህል‹‹ያጣነው››

‹‹ያጣነው››

ቀን:

‹‹እየሆነ ያለው መሆን ከሚገባው ጋር አልዛመድ እያለ ነው፡፡ ብዙ የጥፋት ድርጊቶችን እየተመለከትን ነው፡፡ በየሰፈሩ እያየነው የሚገኘው የክፋት ሥራ ቁጥሩ እየበዛ ነው፡፡ ይለወጣሉ፣ ይሻሻላሉ፣ ሲረጋጉ ሊያዩን ይችላሉ በማለት ከልብ ታገስናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ቸልተኝነታቸው ራስ ወዳድ አድርጎ በስግብግብነት እየመራቸው ነው፡፡ ትዕግሥታችን ከሞኝነት ቆጠሩት፡፡ ያጣነው በጨካኝ ወንዶቻችንና እህቶቻችን ተገፍተን ነው፡፡ ጎዶሏችን የበዛው በሰዎች ጭካኔ ነው! እያሉም ለማጣታቸው የሚያሳስብ የመሟገቻ ምክንያት ያቀርባሉ፡፡

‹‹አንዳንድ የመንግሥት አካላት ከቀደመው ዘመን አንስቶ ከሕዝቡ የወጡ እንጂ ለሕዝቡ የመጡ አይደሉም፡፡ ይህ በመሆኑም የሚቀሙንና የሚወሰድብን እልፍ ነው፡፡ የሚሰጠን ያነሰ ነው፡፡ መንግሥት መሻሻል ይጠበቅበታል እያሉ ሲወያዩ ይደመጣል፡፡ የሚቀነስብን እንጂ የሚጨመርልን አንሷል፡፡ የሚያኖረን ጠፍቶ መኖሪያ እያጣን ነው፡፡ መከራችን በዝቷል እያሉም ያሳጣቸውን ይከሳሉ፡፡ ኑሯቸውን ያመረረባቸውን አካል ይኮንናሉ፡፡ መቸገራቸውን ከሚወዱት የፍቅር ዘፈን በላይ እያዘኑ ከልብ ያዜሙለታል፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት እንባ የማይበግራቸውና ልብን የሚያደክሙ የሐዘን መገለጫዎችን ሳልሰማ ውዬ አላውቅም፡፡››

ይህ ኃይለ ቃል የተገኘው መሰንበቻውን የኅትመት ብርሃን ካገኘው የመቅድም ገረመው ‹‹ያጣነው›› መጽሐፍ ላይ ነው፡፡

ደራሲው ይቀጥላል፣ እንዲህም ይላል፡- ‹‹ኅብረተሰባችን የአንድነት ዋጋ ያልተረዳ ይመስላል፡፡ መከባበርና መደጋገፍ እየተሳነው ነው፡፡ ፍትሕ፣ ሰላምና የነፍስ እርካታ እያጣ ነው፡፡ ይህ በመሆኑ አብዛኛዎችን በባሰ ሐዘንና ተስፋ በመቁረጥ እየተጎዳን ነው፡፡ ሕዝብ በመተሳሰብ ለማደግ ቢሞርክም የሚረብሸውና የሚያውከው ብዙ ነው፡፡ መንግሥትም ማኅበረሰቡን እየዘጋ ነው፡፡ እኛም የምንኖረው ለመኖር እንጂ ያለን የሚያኖር አይደለም ይላሉ፡፡ መቸገራችን በላይ ሆኖ ከብዶናል፡፡ ሰውነታችን ማረፍያ አጥቶ በእጅጉ ግራ እየተጋባን ነው፡፡ አልፎም በምናውቀው ቀያችን ኑሯችን ተጎሳቁሏል በማለት ለራሳቸው ከንፈራቸውን ይመጣሉ፡፡››

ደራሲው ‹‹የዚህ መጽሐፍ ሐሳብ ከነፍሴ የተፀነሰው፣ በእነዚህ ሁሉ ጩኸቶች መካከል እየማሰንኩ ባለሁበት ወቅት ነው፤ በተገኘሁበት ቦታ ሁሉ መንፈሴ በብዙ ጥያቄ ያፋጥጠኝ ጀመር፡፡ ለህሊናዬም ምንድነው የጎደለን? ማነው የነበረንና የያዝነውን የቀማን? ለመሆኑ በትክክል ያጣነው ምንድነው? ያጣነውም ላይገኝ ድብን ብሎ የጠፋብን በምን ምክንያት ነው? እያልኩ አዕምሮዬን ከልቤ ማስጨነቁን ተያያዝኩት፡፡ ቀልቤን በንቃት ሰብሰብ አድርጌ፣ ሁለንተናዬን ይዤ ከነፍሴ በተጠየቅኩት ጥያቄ ተመሰጥኩ፡፡ ብቻዬን ለአንድ መቶ ሃያ ሚሊዮን ሕዝብ የሚበቃ መጠይቅ ተሸክሜ ትንlን አንደበቴን ሳልንቃት ሙግቴን አከረርኩት፤›› ሲሉ በመቅድሙ አመልክቷል፡፡

መጽሐፉ በሰባት ምዕራፎች የተከፈለ ሲሆን የሽፋን ዋጋው 200 ብር መሆኑ ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...

ይኼ አመላችን የት ያደርሰን ይሆን?

እነሆ ከፒያሳ ወደ ካዛንቺስ። ‹‹አዳም ሆይ በግንባር ወዝ ትበላለህ››...