Sunday, June 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልጓደኝነት በ‹‹ሂሪዮሌ›› ሙዚቃ

ጓደኝነት በ‹‹ሂሪዮሌ›› ሙዚቃ

ቀን:

የኦሮሚያ ክልልና አካባቢዋ ብዙ ዓይነት ባህላዊና ማኅበራዊ ክንውኖች አሏቸው፡፡ ባህላዊ ሠርግ ሥነ ሥርዓት ደግሞ አንደኛው ማኅበረሰባዊ መስተጋብር ነው፡፡ የቦረና፣ የጉጂ፣ የወለጋ፣ የሐረርጌ፣ የሸዋ፣ የጅማ ልዩ የሠርግ ሥነ ሥርዓቶችና የሙዚቃ ሥልቶች እንዳሏቸው፣ አዚያዜማቸውም የተለያዩ መሆናቸውም ይታወቃል፡፡

በእነዚህ አካባቢዎች ለሠርግ ሥርዓት የሚዜሙ ዘፈኖችና ጭፍራዎቻቸው የተለያዩ ቢሆንም ወደ ሌሎች ክልሎች ጎልተው እንዳልወጡ ይነገራል፡፡ ለዚህም ይመስላል ሰባት የአፋን ኦሮሞ ዘፋኞች የየአካባቢያቸውን የሠርግ ሙዚቃ ለአድማጭ ይዘው ብቅ ያሉት፡፡ አርቲስቶቹ ሚያዝያ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. በግዮን ሆቴል በጋራ የሠሩትን አልበም አስመርቀዋል፡፡

ከሙዚቀኞቹ አንዷ የሆነችው አርቲስት ቲያ ማሞ ናት፡፡ አርቲስት ቲያ እንደተናገረችው በአልበሙ የተካተቱት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኙ ባህላዊ የሠርግ ሥርዓት ጊዜ የሚዘፍኑ ናቸው፡፡

ወደ ወለጋ አካባቢ በሠርግ ጊዜ የሚዘፈን ሙዚቃ የሠራችው አርቲስት ቲያ፣ ይዘቱን የጠበቀ የባህል ዘፈን መሆኑን ትናገራለች፡፡

‹‹ሂሪዮሌ›› የተሰኘው የኦሮሞ የሠርግ ዘፈን ባህልን፣ ፍቅርና መተሳሰብን የሚያሳይ መሆኑንም ተናግራለች፡፡

በሂሪዮሌ (Hiryyooloo) የሙዚቃ አልበም የተሳተፉት ቲያ ማሞን ጨምሮ፣ ኤልሳ ንጉሤ፣ አበራ እንዳለ፣ ብርሃኑ ዜና፣ ታደሰ ቀቤሳና ሲዮ መኮንን ናቸው፡፡

የሙዚቃ አልበሙ ለመሥራት የወሰደባቸው ጊዜ ከስድስት ወራት በላይ ሲሆን አሥራ አንድ ዘፈኖችን በውስጡ የያዘ ነው፡፡

በአፋን ኦሮሞ የተሠሩ የሠርግ ዘፈኖች አርቲስት ታደለ ገመቹን ጨምሮ ሌሎች አቀንቃኞች መዝፈናቸውን፣ ነገር ግን በኅብረት የሠርግ ሙዚቃ አልበም ሲሠራ የመጀመርያ መሆኑን ድምፃዊቷ አስረድታለች፡፡

የአልበም ምርቃቱ በተለያዩ ሁነቶች የታጀበ መሆኑን፣ በዚህም አሥራ ሁለት ጥንዶች የተሞሸሩበት ነው፡፡ ጥንዶች ሠርግ የመደገስ አቅም የሌላቸው ሲሆኑ፣ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ አማካይነት ዕድሉን ያገኙ መሆናቸውንም ተገልጿል፡፡

ከጥንዶቹ መካከል አቶ ታደሰና ወ/ሮ አበባ ጀንበሩ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ፣ የመሠረግ አቅሙ ስሌላቸው ይህን ዕድል እንደተጠቀሙ ይገልጻሉ፡፡ ከፎቶ፣ የሴቶቹ ሜካፕ፣ የፀጉር ፋሽንን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ ነፃ በመሆኑ ትልቅ ዕድል መሆኑን ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

የበሻቱ ቶለማርያም መልቲ ሚዲያ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ በሻቱ ቶለማርያም እንደተናገሩት፣ ሂሪዮሌ የተሰኘ የሙዚቃ አልበም ምርቃት የተለየና የማይረሳ አጋጣሚ ይዞ የመጣ ዝግጅት ነው፡፡

አልበሙ በውስጡ ከሐረር፣ ሸዋ፣ ወለጋ፣ ጉጂና ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ አሥራ አንድ ሙዚቃዎች ሲኖሩት፣ ሁለቱ የምርቃት፣ አንዱ የልደት፣ ስምንቱ ደግሞ የሠርግ ሙዚቃዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በአልበም ምርቃት ምግብና መጠጥ ሌሎችም ነገሮች ተሟልተው አዲስ ለሚጋቡ ጥንዶች ዕድሉ ቢመቻችላቸው በማለት ወደ ዝግጅቱ እንደገቡ ሥራ አስኪያጇ ያስረዳሉ፡፡

በኑሮ ውድነትና በተለያዩ ችግሮች ምክንያት የሠርግ ዝግጅት ማድረግ ያልቻሉ ጥንዶች በሶሻል ሚዲያ በሬዲዮ ማስታወቂያ ማስነገራቸውን አስታውሰዋል፡፡

ወ/ሮ በሻቱ እንደገለጹት፣ ዋናው ዓላማው አልበሙን ማስመረቅና በዚያውም ደግሞ ጥንዶቹን ሙሉ ወጪያቸውን በመሸፈን ቤተሰቦቻቸውን በተገኙበት መዳር ነው፡፡ ወዳጅ ዘመዶቻቸውን በመጋበዝ የተለያዩ ወጪዎቻቸውን በመሸፈን፣ 12 ጥንዶችን እንዲጋቡ ዕድል ማመቻቸታቸውን ገልጸዋል፡፡

አልበሙ ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ ለአሁኑ ዘመን ማኅበረሰብ የሚመጥን ተደርጎ የተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...