Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኮንፈረንስ ከኢትዮጵያ ተነጥቆ ለሩዋንዳ ተሰጠ

ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኮንፈረንስ ከኢትዮጵያ ተነጥቆ ለሩዋንዳ ተሰጠ

ቀን:

መንግሥት ለዝግጅቱ ያወጣውን ወጪ ከድርጅቱ ሊጠይቅ መሆኑ ተሰምቷል

በቀጣዩ ሰኔ 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ታስቦ የነበረው ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ልማት ኮንፈረንስ፣ ከኢትዮጵያ ተነጥቆ ለሩዋንዳ መተላለፉ ተሰማ፡፡

በአፍሪካ ለመጀመርያ ጊዜ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ይጠበቅ የነበረው ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ልማት ኮንፈረንስ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ኤጀንሲ በሆነው የዓለም የቴሌኮም ኅብረት በየአራት ዓመቱ የሚዘጋጅ ነው፡፡

ይህንን ዓለም አቀፍ ጉባዔ ኢትዮጵያ እንደምታዘጋጅ ቀድሞ ቀን ተቆርጦለት የነበረ ቢሆንም፣ ድርጅቱ በአገሪቱ ባለው የፖለቲካና የሰላም ሁኔታ ላይ መተማመን ባለመቻሉ ቦታውን ለውጫለሁ ማለቱ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ኮንፈረንሱን በጥቅምት እ.ኤ.አ. 2021 ዓ.ም. ለማካሄድ  በ2019 ከድርጅቱ ተቀብሎ ዝግጅት እያደረገ ቢቆይም፣ ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር በተገናኘ ታውጆ በነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያትና እየተካሄደ በነበረው ጦርነት ኮንፈረንሱን እ.ኤ.አ. ወደ ግንቦት 2022 ዓ.ም. ማዘዋወሩ ይታወሳል፡፡

በዚህ ሁሉ ሒደት ኮንፈረንሱ በአዲስ አበባ እንዳይካሄድ ጦርነቱን ሰበብ በማድረግ በዓለም ለስምንተኛ ጊዜና በአፍሪካ ለመጀመርያ ጊዜ በኢትዮጵያ እንዲዘጋጅ ቢታሰብም፣ አገሪቱ ዕድሉን እንዳታገኝ ሲሯሯጡ የነበሩ በርካታ አካላት መኖራቸውን መንግሥት በተደጋጋሚ ሲጠቅስ ይሰማ ነበር፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ደኤታ ወ/ሮ ሁሪያ ዓሊ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ጉባዔውን ለማካሄድ የሚያግዙ ማናቸውም ዓይነት ቅድመ ዝግጅቶች የተጠናቀቁ ቢሆንም ድርጅቱ በአዲስ አበባ መካሄድ የነበረበትን ኮንፈረንስ ወደ ሩዋንዳ ወስዶታል፡፡

በመንግሥት በኩል ማናቸውም ጉዳዮች በከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች ጭምር ቢከናወኑም አለመሳካቱን በመግለጽ፣ ‹‹አስገድዶ እንዲከሄድ ማድረግ ስለማይቻል አሁን በአገር ቤት ያሉትን ሥራዎች በማስተካከል በቀጣይ መሰል ኮንፈረንስ ለማካሄድ መዘጋጀቱ ይበጃል፤›› ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካና የሰላም ሁኔታ በተወሰኑ ሚዲያዎች እንደሚባለው አለመሆኑን በአካል መጥተው እንዲያረጋግጡ፣ እውነታውን እንዲውቁና ኮንፈረንሱም በተያዘለት ጊዜ እንዲከናወን ቢጠየቅም፣ ‹‹አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም›› እንደሚባለው ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ተናግረዋል፡፡

የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ የዓለም የቴሌኮም ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶሮን በግደን ማርቲንን ተቀብለው ስለኮንፈረንሱ መወያየታቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በውይይታቸው ወቅት ጉባዔውን በሩዋንዳ ኪጋሊ ከግንቦት 2014 ዓ.ም. መጨረሻ ጀምሮ ለተከታታይ አሥር ቀናት እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሮ ሁሪያ እንደሚሉት፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የሩዋንዳ ከፍተኛ ኃላፈ እንዳናገሯቸውና እኝህ ስማቸው ያልተጠቀሱ  ባለሥልጣን፣ ከኮንፈረንሱ ይልቅ፣ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ግንኙነት እንደሚበልጥባቸው እንደነገሯቸው አስታውሰዋል፡፡

ይሁን እንጂ ኮንፈረንሱ በሩዋንዳ ከመካሄድ ባለፈ የዓለም የቴሌኮሙዩኒኬሽን ምክር ቤት ውስጥ ካሉ 40 አገሮች መካከል፣ አፍሪካን የሚወክሉ 13 አገሮች ጭምር፣ በኢትዮጵያ እንዳይካሄድ የሚለውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ መደገፋቸውን ተናግረዋል፡፡

አሁን የኢትዮጵያ ሰላም መመለሱን፣ በአገሪቱ ታውጆ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጭምር ከመነሳቱ በተጨማሪ በጥር 2014 ዓ.ም. የተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ የሰላም ማሳያ ሊሆን ቢችልም፣ ሁኔታውን እያወቁ የወሰኑት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እንደ ሚኒስትር ደኤታዋ ገለጻ በቀጣይ አገሪቱ ኮንፈረንሱን ለማዘጋጀት ያወጣችውን ገንዘብ በድርጅቱ አሠራር መሠረት እንዲመለስ ይጠየቃል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...