ቀድቼ እንዳልጠጣ፣
‹‹እንዳትጠጣ!›› አሉኝ ክፍቱን ስላደረ፤
ቆርሼ እንዳልበላ፣
‹‹እንዳትበላ!›› አሉኝ ክፍቱን ስለኖረ፤
መልበስም ፈርቼ፣
አለሁ ራቁቴን ሐሩር ቁሩን ችሎ፤
ክፍት ያደረ አትልበስ እንዳልባል ብዬ፡፡
ራስ ወዳድ ሁሉ፣
እየከፋፈቱ እየገላለቡ፣
በክፍት አማካኝተው ስንቱን ከለከሉ!!
ታዲያ እናንተ ሆዬ!
ክፍት ያደረ ሁሉ ካ’ላገለገለ፣
ተከፍቶ የሚያድር ስንት ነገር አለ፡፡
- መዝገበቃል አየለ ገላጋይ ‹‹ዶፍ አዘል ደመና›› (2013)