Sunday, February 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ያወጣው አዲስ መመርያ ተቃውሞ ገጠመው

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ያወጣው አዲስ መመርያ ተቃውሞ ገጠመው

ቀን:

የመሥሪያ ቤቱ ባለሙያዎች መመርያውን ማን እንዳዘጋጀው አያውቁም

በቅርቡ የተዋቀረው የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አገር አቀፍ የስፖርት ማኅበሮች ስለሚቋቋሙበት ሁኔታ ለመወሰን ተሻሽሎ የወጣውን መመርያ ለብሔራዊ ፌዴሬሽኖችና አሶሴሽኖች ይፋ አድርጓል፡፡ ሚኒስቴሩ ከዚሁ ጎን ለጎን የብዙዎቹን ብሔራዊ ፌዴሬሽኖችና አሶሴሽኖች ከመንግሥት ሲደረግላቸው የቆየውን የገንዘብ ድጎማ አንስቻለሁ ማለቱ ታውቋል፡፡

መመርያ ቁጥር 50/2014 ተብሎ ለብሔራዊ ፌዴሬሽኖችና አሶሴሽኖች እንዲደርስ የተደረገው ይህ መመርያ፣ በአትዮጵያ የስፖርት ልማትና ዕድገት ውስጥ የሚሳተፉ የተለያዩ የስፖርት ማኅበራትን አደረጃጀት፣ አሠራርና አመራር እንዲሁም ተግባርና ኃላፊነት በግልጽ በማስቀመጥ ሰፊ መሠረት ያለው ሕዝባዊ የስፖርት እንቅስቃሴ በማራመድ ኅብረተሰቡን በማሳተፍ ውጤታማ የሆኑ አትሌቶችን ማፍራት አስፈላጊ መሆኑን ይጠቅሳል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ሚኒስቴሩ መመርያው እንደየ ስፖርት ዓይነቱ ዝርዝር ጥናት ተደርጎበት የወጣ መሆኑን ቢገልጽም፣ በርካታ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖችና አሶሴሽኖች ግን መመርያው የዓለም አቀፍ ተቋማትን አሠራርና አካሄድ ከግምት ያላስገባ ከመሆኑ ባሻገር፣ የብሔራዊ ተቋማቱን ሕጋዊ አሠራርና የሙያ ነፃነት የሚጋፋ፣ ለስፖርቱ ዕድገት ማነቆ ነው በሚል ተቃውመውታል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ ቦውሊንግ አሶሴሽን፣ የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና ሌሎችም ተቋማት ሚኒስቴሩ እንደየ ስፖርት ዓይነትና ባህሪይ አኳያ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አንዳችም ግብዓት ሳይወስድ በራሱ ተነሳሽነት ያዘጋጀው መመርያ በመሆኑ አሠራሩን እንደገና መለስ ብሎ ማጤን ይኖርበታል በማለት ይጠይቃሉ፡፡

ይህን ተከትሎ ስፖርቱን በሚመለከት በሚኒስቴሩ የሚገኙ ባለሙያዎች፣ ማክሰኞ ግንቦት 9 ቀን 2014 ዓ.ም. በመሥሪያ ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ በመሰባሰብ፣ ‹‹መመርያው የተዘጋጀው እንዴትና በእነማን ነው?›› እና ‹‹የመሥሪያ ቤቱ የስፖርት ባለሙያዎች መሆናችን እየታወቀ እንደነዚህ የመሰሉ ትልልቅ መመርያዎች ሲዘጋጁ ግብዓት እንድንሰጥ ለምን አልተፈለገም?›› የሚል ጥያቄ ይዘው ሚኒስትሩን ቀጀላ መርዳሳን ለማነጋገር መዘጋጀታቸው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የስብሰባው ታዳሚዎች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በሚኒስትሩ ቀጀላ መርዳሳ ፊርማ ለብሔራዊ ፌዴሬሽኖችና አሶሴሽኖች እንዲደርስ በተደረገው በዚህ መመርያ አካሄድ ላይ፣ የስፖርት ዘርፉን እንዲመሩ የተሾሙት ግለሰብ በአጠቃላይ ስፖርቱን በሚመለከት በሚኒስቴሩ እየሆነ ባለው ጉዳይ ብዙም ደስተኛ አለመሆናቸውን ጭምር ነው ምንጮቹ የሚናገሩት፡፡

ይህ ሁኔታ ባለበት 21 የሚሆኑ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖችና አሶሴሽኖች እስከ ዛሬ በነበረው አሠራር፣ ስፖርቱን ለማስፋፋት ሲደረግላቸው የቆየው የገንዘብ ድጎማ መቋረጡን ጭምር የሚገልጽ ውሳኔ ከሚኒስቴሩ መደመጡን የሚናገሩት እነዚሁ ምንጮች፣ ‹‹ውሳኔው ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ሚኒስቴሩ በጉዳዩ ከሚመከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር መነጋገር ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም በእያንዳንዱ ብሔራዊ ፌዴሬሽንና አሶሴሽን ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ዕርከን ግልጋሎት ሲሰጡ የቆዩ ቁጥራቸው ወደ 300 የሚጠጉ ባለሙያዎችና ሠራተኞች ቀጣይ ዕጣ ፈንታም መታየት ስላለበት ነው፤›› በማለት የችግሩን ስፋት እንዲሁም በቀጣይ ሊያስከትል የሚችለውን ቀውስ ያመላክታሉ፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...