Thursday, December 7, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትለኢትዮጵያ እግር ኳስ አመራርነት የመራጮች ቁጥር በነበረው ይቀጥላል

ለኢትዮጵያ እግር ኳስ አመራርነት የመራጮች ቁጥር በነበረው ይቀጥላል

ቀን:

ትውልደ ኢትዮጵያውያንን የሚመለከተው ረቂቅ መመርያ ይሻሻላል ተብሏል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ እንዲሻሻል የቀረበለትን መተዳደሪያ ደንብና የምርጫ ማስፈጸሚያ ደንብ በማፅደቅ ተጠናቀቀ፡፡

በሌላ በኩል በፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 29 የጠቅላላ ጉባዔ ድምፅ ውክልና ለመወሰን የቀረቡ ሁለት አማራጭ ሐሳቦች በጉባዔው ውድቅ ተደርገዋል፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ግንቦት 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ በጠራው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ፣ ማሻሻያ እንዲደረግለት በቀረበው ረቂቅ መመርያ ላይ ውይይት አድርጎ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

እንዲሻሻል የሚፈለገው ረቂቅ መመርያ ለጉባዔ ከመቅረቡ በፊት በቅድሚያ ለአባላቱ ተልኮ ማስተካከያ እንደደረግባቸው በስድስት ማኅበሮች ከተጠየቀባቸው ነጥቦች ውስጥ፣ የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) በላከው ሰርኩላር መሠረት ድምፅ ሰጪ የጉባዔ አባላት ቁጥር ቀድሞ ከነበረው መቀነስ እንዳለበት የሚጠይቀው ይጠቀሳል፡፡

ሌላው ከጥምር ዜግነት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በተለይም የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በቅርቡ ለብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በላከው መመርያ፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ያለው ቢሆን፣ በፌዴሬሽኑ ለፕሬዚዳንትነትና ምክትል ፕሬዚዳንትነት እንዲሁም የጽሕፈት ቤት ኃላፊነት መመረጥ እንደማይችል ካስቀመጠው አንቀጽ ጋር የሚጣጣም ማስተካከያ መደረግ እንዳለበት የጉባዔው አቋም ሆኖ ተወስዷል፡፡

ጉባዔው በተለይ በሁለቱ ነጥቦች ላይ ጊዜ ወስዶ ከተወያየ በኋላ፣ በጉባዔ የድምፅ ሰጪ አባላት ቁጥር እንዲቀንስ የሚለው ውድቅ እንዲሆን፣ በሚኒስቴሩ የቀረበው ማለትም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የመታወቂያ ካርድ ያላቸው ቢሆኑም፣ በማናቸውም ፌዴሬሽኖች ውስጥ በዋናነት በፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሁም በጽሕፈት ቤት ኃላፊነት መመረጥ አይችሉም የሚለው አግባብነት የሌለው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በሒደት ከዚሁ መመርያ ጋር ተጣጥሞ ሊሄድ የሚችል መመርያ የሚዘጋጅ ይሆናልም ተብሏል፡፡

መንግሥት በአዋጅ ቁጥር 270/1994 የደነገገውን መሠረት በማድረግ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ላይ ገደብ የሚደረግባቸው፣ በአገራዊ ምርጫ እንዲሁም ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጨምሮ መሰል የደኅንነት መሥሪያ ቤትና የፖለቲካ ተቋማት ውስጥ በቋሚነት ተቀጥረው መሥራት የማይችሉ መሆኑ ይታወቃል፡፡     

ሌላው በረቂቁ ላይ ማሻሻያ እንዲደረግበት የቀረበው በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት በፕሬዚዳንትነት የሚመረጠው ግለሰብ የዕድሜ ጣሪያን የሚመለከተው ነበር፡፡ በመሆኑም ለቦታው ብቁ የሆነ ሰው መለኪያ ሊሆን የሚገባው አቅሙና ብቃቱ ሆኖ ሳለ፣ ‹ዕድሜ› የሚለው የዓለም አቀፉን ተቋም ጨምሮ በየትኛውም አገር የሌለ መመርያ ነው በሚል ውድቅ ተደርጓል፡፡

በፌዴሬሽኑ መተዳዳሪያ ደንብ አንቀጽ 29 መሠረት በጠቅላላ ጉባዔው ድምፅ የነበራቸው አባላት ቁጥር 144 ነበር፡፡  በቀጣይ ግን የፊፋ ሰርኩላር እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በረቂቁ የጠቅላላ ጉባዔ ድምፅና ውክልናን ለመወሰን ከቀረቡት አማራጮች በድምፅ የሚሳተፉ አባላት ቁጥር 74 አሊያም ከ79 መብለጥ የለበትም በሚል ነበር ጉባዔው ላይ ለውይይት የቀረበው፡፡

ጉባዔው በመጨረሻም በቅርቡ በሚኖረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴና የፕሬዚዳንት ምርጫ ለሚያከናውን የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን ሰይሟል፡፡ ለዚህ ኃላፊነት በዕጩነት ከቀረቡት አባላት መካከል ወ/ሮ ረሂማ አወል፣ የሕግ ባለሙያው አቶ ኃይሉ ሞላ፣ አቶ መንግሥቱ መሐሩ፣ አቶ ኢሳይያስ ደንድርና አቶ በለጠ ዘውዴ በአብላጫ ድምፅ መመረጣቸው ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...