ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኰንን፣
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን የዘጠኝ ወራት የሥራ ክንውን ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ.ም. ሲገመግም ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ላይ
የተናገሩት። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አክለውም፣በቀይ ባሕር ጉዳይ ላይ ኢትዮጵያን ያላሳተፈ አደረጃጀት ተቀባይነት እንደሌለውም አውስተዋል፡፡ በኬንያ፣ በሶማሊላንድና በኤርትራ በመተማመን ላይ የተመሠረተ የወደብ አማራጮችን ለማስፋት እየተሠራ መሆኑንና ይሀንኑ ለማስቻልም በአፍሪካ ቀንድና በቀይ ባሕር የጂኦ-ፖለቲካ ስትራቴጂ ተቀርፆ በልዩ ትኩረት እየተሠራ መሆኑም ሳይጠቅሱ አላለፉም።