Friday, February 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየወልዲያ ከተማ አስተዳዳር ‹‹ሰርጎ ገቦች››ን ለመለየት የነዋሪዎችን መታወቂያ ሊቀይር ነው

የወልዲያ ከተማ አስተዳዳር ‹‹ሰርጎ ገቦች››ን ለመለየት የነዋሪዎችን መታወቂያ ሊቀይር ነው

ቀን:

የወልዲያ ከተማ አስተዳደር በከተማው ውስጥ የሚገኙ ‹‹ሰርጎ ገቦችን›› ለመለየት እንዲቻል፣ የከተማዋ ነዋሪዎችን በሙሉ መታወቂያ ሊቀር እንደሆነ አስታወቀ፡፡ በከተማው ውስጥ ካለው ሁኔታ አንፃር እየተለዩ የሚታሰሩ ግለሰቦች እንዳሉ የገለጸው የከተማ አስተዳደሩ፣ አዲስ መታወቂያ የሚወስዱ ሰዎች ያላቸውን መታወቂያ ከከተማዋ ወሳኝ ኩነት መረጃ ጋር እንደሚያመሳክር ገልጿል፡፡

ለወራት በሕወሓት ቁጥጥር ሥር ከቆየች በኋላ በታኅሳስ ወር ላይ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር በሆነችው ወልዲያ፣ ‹‹ሰርጎ ገቦች›› የቀድሞውን መታወቂያ መያዛቸውን ለሪፖርተር የተናገሩት የወልድያ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ዳዊት መሰለ (ዶ/ር)፣ በዚህም ምክንያት የከተማው አስተደዳር የከተማዋን ነዋሪዎች መታወቂያ ለመቀየር ውሳኔ ማስተላለፉን ገልጸዋል፡፡

እንደ ዳዊት (ዶ/ር) ገለጻ፣ ከዚህ ቀደም መታወቂያ ሲሰጥ የነበረው መረጃዎችን በመዝገብ ላይ በመጻፍ ብቻ የነበረ ሲሆን፣ ይህም በቀበሌዎች መካከል የሚጣራበት ሁኔታ እንዳይኖር በማድረጉ የተለያዩ ቀበሌዎች ላይ ከአንድ በላይ መታወቂያ ያላቸው ሰዎች አሉ፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹ሰርጎ ገብ›› የተባሉትን ሰዎች ማንነት አብራርተው ባይገልጹም፣ የከተማዋ ነዋሪዎች መታወቂያ እንዲይዙ የሚያደርጉ የቀበሌ አመራሮች አሉ የሚል ጥርጣሬ እንዳለ አስረድተዋል፡፡ አሁን መታወቂያ የማደስ አገልግሎት እንዲቆም መደረጉን አክለዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ አሁን ላይ ያለውን ደብተር መሰል መታወቂያን በዲጂታልና የቀበሌ መለያ ባለው አዲስ መታወቂያ እንደሚቀየርም ዳዊት (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር እስካሁን የተሰጡት መታወቂያዎች በዲጂታል ሥርዓት ውስጥ ገብተው በሁሉም ቦታ መመሳከር እንዲችሉ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡

አዲሱ የመታወቂያ ዲዛይን በከተማ ውስጥ ለሚገኙት ስድስት የከተማና አራት የገጠር ቀበሌዎች መሠራጨቱን የሚያስረዱት ከንቲባው፣ በተያዘው ሳምንት ወይም ከሚቀጥለው ሳምንት አንስቶ አዲስ መታወቂያ ለመስጠት መታቀዱን ተናግረዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ከ15 ቀናት እስከ አንድ ወር ባለ ጊዜ ውስጥ በከተማ ውስጥ ላሉት 189 ሺሕ ነዋሪዎች አዲስ መታወቂያ ለመስጠት ያቀደ መሆኑን፣ ለዚህ ሥራ ብዛት ያለው የሰው ኃይል ለማሰማራት መታሰቡን ዳዊት (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ መታወቂያ ሰጥቶ ለማጠናቀቅ ጊዜ ቢቆርጥም የከተማዋ ነዋሪዎች መታወቂያ መቀየር የሚችሉበት ቀነ ገደብ እስካሁን አልተቀመጠም፡፡ ከንቲባው እንደሚያስረዱት፣ በዚህ ሳምንት መታወቂያ ሊሰጥ የታሰበው የከተማ አስተዳደሩ በፀጥታ መደፍረስና በዕርዳታ ማከፋፈል ሥራ ምክንያት ዕቅዱ በሁለት ሳምንት ከዘገየ በኋላ ነው፡፡ በዚህ ወይም በቀጣዩ ሳምንት ሥራው ከተጀመረ በኋላ ግን ቀነ ገደብ እንደሚቀመጥ ተናግረዋል፡፡

መታወቂያ የማደስ ሥራው በመቆሙም ምክንያት የከተማዋ ነዋሪዎች ሌሎች አገልግሎቶችን ለማግኘት የግድ አዲስ መታወቂያ ይወስዳሉ የሚል እምነት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር የሚያጋጥም ከሆነ ግን መታወቂያ ለመቀየር የተቀመጠው የዕቅድ ጊዜ ሊራዘም እንደሚችል አክለዋል፡፡

ከንቲባው አዲስ መታወቂያ ቢሰጥም ‹‹ሰርጎ ገቦችን›› ሙሉ ለሙሉ ማፅዳት እንደሚያዳግት ገልጸው፣ መታወቂያ መቀየሩ ያለውን ሁኔታ ለመቆጣጠር የተሻለ አማራጭ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ከተማዋ በጊዜ ሒደት ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ መግባቷን የተናገሩት ዳዊት (ዶ/ር)፣ ነጋዴዎች ከፍተኛ ኪሳራና ዘረፋ ቢደርስባቸውም እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የፀጥታ ሁኔታውን ለመቆጣጠርም የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከፖሊስና ሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ማታ ማታ ሮንድ እንደሚያደርጉ ከንቲባው ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል...

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት የፈጠሩት አምቧጓሮ

ባለፈው ቅዳሜና እሑድ በአዲስ አበባ የተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት 37ኛው...

የብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ትግበራ የፈጠራቸው አሉታዊና አዎንታዊ ጎኖች

የአገሪቱ ንግድ ባንኮች በዓመት የሚሰጡት የብድር መጠን ላይ የኢትዮጵያ...

ቱግ ቱግ!

የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ለመታደም የመጡ እንግዶችን ሸኝተን ከፒያሳ ወደ...