Friday, December 9, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትየኢትዮጵያ ቦውሊንግ ባለውለታውንና ተሟጋቹን አጣ

  የኢትዮጵያ ቦውሊንግ ባለውለታውንና ተሟጋቹን አጣ

  ቀን:

  ለዘጠኝ አሠርታት ግድም በኢትዮጵያ ሲዘወተር የቆየው ቦውሊንግ ባለውለታውን አጣ፡፡ ቦውሊንግ በኢትዮጵያ ቀደምት ተብለው ከሚጠቀሱ ስፖርቶች አንዱ ቢሆንም፣ ጊዜውን በሚመጥን መልኩ ስፖርቱን በመላ ኢትዮጵያ ማስፋፋት ይቻል ዘንድ የማዘውተሪያና የመለዋወጫ ችግሮችን ለሚመለከተው አካል በማድረስ፣ በመሟገት በቀዳሚነት የሚታወቁት ባለውለታውን አቶ ደጀኔ ኃይለ ማርያምን በሞት አጥቷል፡፡

  በ74 ዓመታቸው ያረፉትን የአቶ ደጀኔ ኃይለማርያምን ድንገተኛ ሕልፈት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ቦውሊንግ አሶሴሽን ባወጣው መግለጫ፣ ‹‹አቶ ደጀኔ ለ50 ዓመታት ያህል በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴና በፕሬዚዳንትነት ከማገልገላቸውም በላይ፣ በኢትዮጵያ ቦውሊንግ በተጫዋችነት እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ በተደረጉ ውድድሮች ኢትዮጵያን በመወከል ከስድስት ጊዜ በላይ ተሳትፎ የነበራቸው ናቸው፤›› ብሏል፡፡

  የኢትዮጵያ ቦውሊንግ ከመንግሥት የሚደረግለት ድጎማ 400 ሺሕ ብር መሆኑን የሚያስረዳው መግለጫው፣ የስፖርቱ ዓመታዊ በጀት ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ እንደሆነና ይህም የሚሸፈነው በተወዳዳሪዎችና በቤተሰቦቻቸው መልካም ፈቃደኝነት የነበረ መሆኑን ያስረዳል፡፡ ለዚህ ትልቅ ድርሻ ከነበራቸው በጎ ፈቃደኛ ኢትዮጵያውያን መካከል ደግሞ አቶ ደጀኔ አንዱ ነበሩ ብሏል፡፡

  የኢትዮጵያ ቦውሊንግ በቀደሙት ዓመታት አስመራን ጨምሮ በአዲስ አበባ በተለያዩ ቦታዎች ከነበሩት አራት ማዘውተሪያዎች ውስጥ፣ በአሁኑ ወቅት ሁለት ማለትም በገነት ሆቴልና ብሥራተ ገብርኤል አካባቢ የሚገኘው ላፍቶ ሞል ያሉት ብቻ መሆናቸው፣ እነዚህም ቢሆኑ ከፍተኛ የመለዋወጫ ችግር እየገጠማቸው ሙሉ አገልግሎት እንደማይሰጡ ጭምር በመግለጫው ተካቷል፡፡

  በተለይም የኢትዮጵያ ቦውሊንግ ከማዘውተሪያ ዕጦት ባሻገር፣ ስፖርቱ የሚዘወተርባቸው ማሠሪያዎች ከፍተኛ የሆነ የመለዋወጫ ችግር እየገጠማቸው በመሆኑ መንግሥትና የሚመለከተው አካል ትኩረት እንዲሰጡት ጠይቋል፡፡

  በመሆኑም ቦውሊንግ እንደሚነገረው የቅንጦት ሳይሆን፣ እንደ አንድ የልማት ዘርፍ ጤናማ ትውልድ የሚቀረፅበት ዓይነተኛ መንገድ መሆኑ ከግምት በማስገባት ድጋፍና ክትትል እንዲደረግለት ጥሪውን አቅርቧል፡፡      

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ጭፍጨፋና ሥጋቱ

  ኦሮሚያ ክልል ከቀውስ አዙሪት መላቀቅ ያቃተው ይመስላል፡፡ ከ200 በላይ...

  እናት ባንክ ካፒታሉን ወደ አምስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰነ

  መጠባበቂያን ሳይጨምር የባንኩ የተጣራ ትረፍ 182 ሚሊዮን ብር ሆኗል እናት...

  ቡና ባንክ ዓመታዊ ትርፉን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ማሻገር ቻለ

  ቡና ባንክ በ2014 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔውን ለመጀመርያ...