Wednesday, June 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዓለምየኢማኑኤል ማክሮን ዳግም የፈረንሣይ ፕሬዚዳንት መሆን ለአውሮፓ ኅብረት ምኑ ነው?

የኢማኑኤል ማክሮን ዳግም የፈረንሣይ ፕሬዚዳንት መሆን ለአውሮፓ ኅብረት ምኑ ነው?

ቀን:

የፈረንሣይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለሁለተኛ ጊዜ የፈረንሣይ ፕሬዚዳንት ሆነው ቀጣዮቹን አምስት ዓመታት እንዲያገለግሉ፣ እሑድ ሚያዝያ 16 ቀን 2014 ዓ.ም. በተከናወነ ምርጫ ተመርጠዋል፡፡

እ.ኤ.አ. ከ2002 ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ዳግም ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲመሩ የተመረጡት ማክሮን፣ ከመራጩ ሕዝብ 58.5 በመቶ ድምፅ ሲያገኙ፣ የቀኝ ዘመም ተቀናቃኛቸው ማሪን ላ ፔን 41.5 በመቶ አግኝተዋል፡፡

‹‹ሩሲያን ማግለል የለብንም፣ ወደ አውሮፓ መሳብ አለብን›› በሚል አቋማቸው የሚታወቁት ላ ፔን፣ የፕሬዚዳንትነቱን ወንበር አለመጨበጣቸው ደግሞ መቀመጫቸውን ብራስልስ ላደረጉት የአውሮፓ ኅብረትና የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) እፎይታን ሰጥቷል፡፡

- Advertisement -

ምዕራባውያን አገሮች ማክሮን እንዲመረጡ አብዝተው ይፈልጉ የነበረ ሲሆን፣ ይህ ተሳክቶላቸዋል፡፡ ሆኖም የመራጩን 41.5 በመቶ ድምፅ ያገኙት ላ ፔን እና ደጋፊዎቻቸው ለማክሮን ቀጣይ የአምስት ዓመታት ጉዞ ፈታኝ ይሆናሉ ሲል ሲኤንኤን አስፍሯል፡፡

ማክሮን በዩክሬንና ሩሲያ ጦርነት ዙሪያ ምዕራባውያኑ የሚያደርጉትን ጣልቃገብነት በመደገፍ የኔቶ እና የአውሮፓ ኅብረት ትብብር እንዲቀጥል የበኩላቸውን ሚና የተጫወቱ ናቸው፡፡ ለሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ስልክ በመደወል ችግሩ በውይይት እንዲፈታ ማድረጋቸውም ይታወሳል፡፡

ነገር ግን ላ ፔን የተለየ ሐሳብ ያንፀባርቃሉ፡፡ ሩሲያ ዩክሬንን መውረሯን ባይደግፉም፣ ሩሲያን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ወደ አውሮፓ መሳብና ከቻይና ጋር ያላትን ጥምረት ማክሸፍ በሚለው ሐሳባቸው ግንባር ቀደም ሆነው የሚታወቁ ናቸው፡፡

‹‹የሩሲያንና ዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም ዲፕሎማሲያዊ አካሄድ ያዋጣል›› የሚሉት ላ ፔን ሐሳብ ደግሞ፣ መሣሪያ ለዩክሬን በመላክ ከተጠመዱት የአውሮፓ ኅብረት አገሮችና አሜሪካ ብሎም ለኔቶ አባል አገሮች የሚዋጥ አልነበረም፡፡

ይህም ላ ፔን ቢመረጡ፣ የአውሮፓ ኅብረትን፣ የአሜሪካንና የኔቶን አንድነት ሊነቀንቁት ይችሉ ነበር የሚሉ አስተያየቶች ይሰጣሉ፡፡

የላ ፔን አለመመረጥ ለምዕራባውያኑ ዕፎይታን ይስጥ እንጂ፣ ለማክሮን ፈተና ሊሆን  እንደሚችል ተሠግቷል፡፡ በሰኔ ለሚደረገው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ምረጡን በማለትም ደጋፊዎቻቸውን መጠየቃቸውና በቀጣይም ሐሳባቸውን ለማሳካት በፖለቲካው ዓለም የሚሳተፉ መሆናቸው  ማክሮንንም ሆነ ምዕራባውያኑን የሚያሳስብ ጉዳይ ሆኗል፡፡

በፈረንሣይ ምርጫ ማክሮን 58.5 በመቶ ላ ፔን 41.5 በመቶ ድምፅ ቢያገኙም፣ አጠቃላይ ለመምረጥ ከተመዘገበው ሕዝብ 28.2 በመቶ በምርጫው አለመሳተፉ ሁለቱንም የማይፈልጉ ትልቅ ቁጥር ያላቸው ሕዝቦች መኖራቸውንና ይህ እ.ኤ.አ. ከ1969 ወዲህ ታይቶ አለመታወቁ ለማክሮን ቀጣይ አምስት ዓመታት ተጨማሪ ፈተና ነው ሲሉ የፈረንሣይ ሚዲያዎች አስፍረዋል፡፡

ታይም የፖለቲካ ታሪክ ፕሮፌሰር ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ማክሮን ሁሉንም የፈረንሣይ ዜጎች ማናገር ይጠበቅባቸዋል፡፡ በመረጧቸው፣ ላ ፔንን በመረጡትና ባልመረጧቸው ዜጎች መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብም አለባቸው፡፡

ፈረንሣይ የአውሮፓ ኅብረት፣ የኔቶና የቡድን ሰባት አገሮች አባልት ናት፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ አላት፡፡ ምንም እንኳን ከምዕራባውኑ ጋር በነዚህ ተቋማት አብራ ብትሠራም፣ የራሷ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ባለቤት ናት፡፡

ይህም አሜሪካ መር በሆነው የምዕራባውያኑ ዕዝ እና በኢራን፣ ቻይናና ሩሲያ መካከል እንደ ደላላ ሆና እንድታገለግል አስችሏታል፡፡ ማክሮን ይህንን ኃላፊነት እየተወጡ ያለፉትን አምስት ዓመታት መርተዋል፡፡ ላ ፔን እንዲያ ያለውን አካሄድ የሚቀበሉ አይደሉም፡፡ ይልቁንም ‹‹መጀመርያ ለፈረንሣያውያንና ፈረንሣይ›› በሚል አቋማቸው ይታወቃሉ፡፡ ይህ የአውሮፓ ኅብረትን አንድነት ሥጋት ላይ የሚጥል ነው፡፡

ላ ፔን ከሩሲያ ጋር ያላቸው ግንኙነት፣ ለኔቶ ያላቸው ምዕራባውያኑን የማያስደስት ዕይታ እንዲሁም የአውሮፓ ኅብረት ላይ ያላቸው ‹‹ትክክል አይደላችሁም›› አመለካከት ምዕራባውያኑ ዓለምን ያስተሳሰሩበትን ገመድ ሊበጣጥስ የሚችል ነው፡፡

እሳቸው፣ ባይመረጡም የእሳቸውን ሐሳብ የሚደግፉ 41.5 በመቶ መራጮች ድምፅ መስጠታቸው የኔቶ፣ የአውሮፓ ኅብረትንና የምዕራባውያኑ አካሄድ ፈተና እንዲገጥመው ሊያደርግ የሚችል ነው፡፡

 በአውሮፓ ኅብረት ጠንካራ አቅም ያላት ፈረንሣይ ውስጥ ፀረ ምዕራባውያንና አውሮፓ ኅብረት አመለካከት የመንሰራፋት ምልክትም ነው፡፡ የማክሮን መመረጥ ጥምረት የተፈጠረባቸውን ተቋማት ከሥጋት ነፃ አደረገ እንጂ፣ ማክሮንን ከፈተና አያወጣቸውም፡፡ በተለይ በሕዝብ ተወካዮች ምርጫ የቀኝ ዘመም ፖለቲካኞች እመርታ እያገኙ ከሄዱ፣ ከአሁን ጀምሮ ቀጣዩ አምስት ዓመታት የአውሮፓ ኅብረትና የኔቶ አባል አገሮች እንደሚፈልጉት ሳይሆን የተለየ ውጤት ይዞ የሚጓዝ ሊሆን እንደሚል ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡

‹‹ፈረንሣይን ወይም ማክሮንን ምረጡ›› በሚል ቅስቀሳቸው የሚታወቁት ላ ፔን  የሥራ፣ የቤትና ሌሎች ዕድሎች ቅድሚያ ለፈረንሣያውያን የሚሉና ከአውሮፓ ኅብረት አባል አገሮች አሠራር የሚቃወሙ ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...