Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበጂንካና ዙሪያዋ በተፈጠረው ሁከት የፀጥታ ኃይሎችን ጨምሮ ከ900 በላይ ሰዎች ታስረዋል

በጂንካና ዙሪያዋ በተፈጠረው ሁከት የፀጥታ ኃይሎችን ጨምሮ ከ900 በላይ ሰዎች ታስረዋል

ቀን:

በደቡብ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን በጂንካ ከተማና በዙሪያዋ በሚገኙ አካባቢዎች በመጋቢት ወር መጨረሻ አንስቶ ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ 12 የፀጥታ አካላትን ጨምሮ፣ 904 ሰዎችን በቁጥጥር ሥራ አውሎ ምርመራ እያደረገ መሆኑን የምዕራብ ኦሞ ዞን አስተዳደር አስታወቀ፡፡ ከተጠርጣሪዎቹ መካከል የመንግሥት አመራሮችና መምህራን እንዳሉበትና ሌሎች ተጠርጣሪዎችንም ለመያዝ እየሠራ መሆኑን ገልጿል፡፡

ከዞን መዋቅር ጋር ተያይዞ የተነሳ ጥያቄን ተከትሎ በደቡብ ምዕራብ ዞን በጂንካ ከተማና የደቡብ አሪ አካባቢዎች በተነሳው ግጭት 150 ቤቶችና አንድ መስጊድ የተቃጠሉ ሲሆን፣ ከ1,500 በላይ የቤተሰብ አባላት ተፈናቅለዋል፡፡ የዞን አስተዳደሩ የደረሰውን ውድመት ሼኬንና ሶያ የተባሉ ‹‹ኢመደበኛ አደረጃጀቶች›› አድርሰውታል የሚል ክስ ያቀረበ ሲሆን፣ ተጠርጣሪቹ በፍርድ ቤት የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የሰላምና ፀጥታ መምርያ ኃላፊ አቶ ደሞ በዛብህ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ዞኑ የመልሶ ማቋቋም ሀብት አሰባሳቢ ኮሜቴ ማቋቋሙን የገለጹት ኃላፊው፣ ለአንድ ሳምንት ገደማ በቆየውና የመከላከያ ሠራዊት ገብቶ ባበረደው ግጭት የደረሰውን ውድመት ለመመለስ 82 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል፡፡ እንደ አቶ ደሞ ገለጻ፣ የደቡብ ክልል ከቤታቸው ለተፈናቀሉና ቤታቸው ለወደመባቸው ሰዎች የሚሆን ዕለታዊ የምግብ ዕርዳታ በመላክ ላይ ሲሆን የዞን አስተዳደሩ የወደሙ ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የእንጨት ማሰባሰብ ሥራ ላይ ነው፡፡

በዞኑ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በተለይ ደቡብ አሪ ወረዳ መደበኛ የመንግሥት እንቅስቃሴዎች ተገትተው የቆዩ ሲሆን፣ የዞኑ አስተዳደር ከሰኞ ሚያዝያ 17 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛና አመራር በመደበኛ የሥራ ገበታው ላይ እንዲገኝ ካሳሰበ በኋላ ሁኔታዎች እየተሻሻሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አሁን የፀጥታ ችግር አለመኖሩን የተናገሩት አቶ ደሞ፣ ይሁንና ግጭቱ ውስጥ ተሳትፈው በቁጥጥር ሥር ያልዋሉና በሕዝቡ ውስጥ የተሸሸጉ ግለሰቦች መኖራቸው እንደ ሥጋት ሊነሳ እንደሚችል አስረድተዋል፡፡ ግጭቱ የተነሳው  በዞንነት ለመደራጀት ጥያቄ ያቀረቡ አራት የአሪ ሕዝብ ወረዳዎች ጉዳያቸው በዞኑ ምክር ቤት አለመታየቱ መሆኑን ከዚህ ቀደም ቢገለጽም፣ የሰላምና የፀጥታ መምርያ ኃላፊው፣ ‹‹ይኼ ጉዳይ ሰበብ ተደረገ እንጂ የጥፋቱ ዋነኛ ምክንያት አይደለም፤›› ብለዋል፡፡

በጂንካና አካባቢዋ በተለይ ከሚያዝያ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ የተከሰተው ግጭት ከጂንካ ከተማ ሁለት የገበያ ቦታዎች ላይ ረብሻ ተነስቶ ገበያተኞችና ነጋዴዎች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

ከጂንካ ከተማም ውጪም እንደ ጋዘር፣ ቶልታና ሜፅር ባሉ አካባቢዎች ቤቶች ሲቃጠሉና ሱቆች ሲዘረፉ፣ እንዲሁም ሰዎች ወደ ጫካ ሲሸሹ የነበረ ሲሆን፣ በዕለቱ የአካባቢው ገበሬዎችና የፀጥታ ኃይሉ የተኩስ ልውውጥ ሲያደርጉ ማደራቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታውቆ ነበር፡፡ የመከላከያ ሠራዊት ቅዳሜ ሌሊት ወደ ጂንካ ከተማ ከገባ በኋላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመጣሉ የነዋሪዎች እንቅስቃሴ በሰዓት ተገድቦ፣ ምንም ዓይነት የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እንዳያደርግ መታገዱ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...