Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈናቀሉ ተማሪዎች ዲግሪ እንደማይሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

ከትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈናቀሉ ተማሪዎች ዲግሪ እንደማይሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

ቀን:

የከፍተኛ ትምህርት ምደባ ወጥ አሠራር እንደሚበጅለት ገልጿል

ከትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ተፈናቅለው በአደራ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተምረው ለተመረቁ ተማሪዎች፣ መደበኛ ዲግሪ ሚኒስቴሩ ለመስጠት እንደሚቸገር ተገለጸ፡፡ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በትምህርት ሚኒስቴር ዋስትና ገብተው የተመረቁ ከትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች የተፈናቀሉ ከ4,000 በላይ ተማሪዎች መደበኛ ዲግሪ ስለተከለከልን ሥራ ለመቀጠርና ለመወዳዳር አልቻልንም ሲሉ ለሪፖርተር ተደጋጋሚ ቅሬታዎችን ሲያሰሙ ቆይተዋል፡፡

የእነዚሁ የተማሪዎች ቅሬታ የቀረበላቸው ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ (ፕሮፌሰር) እንደተናገሩት፣ ‹‹የተማሪዎቹ ሙሉ መረጃ ሳይገኝ መደበኛ ዲግሪ ለመስጠት እንቸገራለን፡፡ ጦርነቱ ሲቆምና ሰላምና መረጋጋት በሰሜን ኢትዮጵያ በአስተማማኝ ሁኔታ ሲሰፍን ከመጡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት ያቆሙበት መረጃ ተሟልቶ ሲቀርብ ዲግሪው ይሰጣቸዋል፡፡ እስከዚያው ግን በተሰጣቸው ውጤታቸውን በሚገልጽ ሰርተፊኬት ሥራ መፈለግ ይችላሉ፤›› ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ ይህን ቢሉም ከትግራይ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች በጦርነት ሳቢያ ተፈናቅለው ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ለመመረቅ የተገደዱ ተማሪዎች ግን፣ ትምህርት ሚኒስቴር በአንድ ሴሚስተር የውጤት መግለጫ ወረቀት (በግሬድ ሪፖርት) አሰናብቶናል ሲሉ ቅሬታ ያሰማሉ፡፡ ይህ ወረቀት ደግሞ በሥራ ዓለም ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቀጠር እንደማያስችላቸው በመጥቀስ፣ ትምህርት ሚኒስቴር ዘላቂ መፍትሔ እንዲፈልግላቸው እየጠየቁ ነው፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ግን አሁን ካደረኩት የተለየ አማራጭ የለኝም የሚል ምላሽ ነው የሰጠው፡፡

የከፍተኛ ትምህርት የመግቢያ መሥፈርትና ድልድል ወጥ የሆነ አሠራር እንደሚበጅለት የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ከከፍተኛ ትምህርት የመግቢያ ጊዜ መራዘም ጋር በተያያዘ የሚነሱ ቅሬታዎችን በሚመልስ ሁኔታ፣ መደበኛ የቅበላ መሥፈርትና የጊዜ ሰሌዳ እንደሚወጣ ሚኒስቴሩ ለሪፖርተር አስታውቋል፡፡  

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚገቡ ተማሪዎች ምደባ መሥፈርትም ሆነ የቅበላ የጊዜ ሰሌዳ መደበኛ ወጥ የሆነ አሠራር ይዘጋጅለታል ብለዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ምደባና የቅበላ መሥፈርት በጊዜ እየተካሄደ አይደለም የሚለው ቅሬታ አብሮ እንደሚመለስ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በግል ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ገብቶ ለመማር በትምህርት ሚኒስቴር በኩል የቅበላ ውጤት ይፋ ሳይደረግ ለረዥም ጊዜ በመዘግየቱ ላይ ተቋማቱ ቅሬታ ሲያሰሙ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ ዋናው የገቢ ምንጫችን ተማሪዎችን በመቀበል የሚገኝ የምዝገባና መማሪያ ክፍያ መሆኑ እየታወቀ፣ ትምህርት ሚኒስቴር የመግቢያውን ጊዜ አጓትቶታል በማለት የግል ተቋማቱ ስሞታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ ይህ ጉዳይ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት መልስ እንደሚያገኝ የገለጸው ትምህርት ሚኒስቴርም፣ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ምደባን ሰኞ ዕለት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ (ፕሮፌሰር) ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቆይታ ስለዚሁ ጉዳይ ጥያቄ የቀረበላቸው ሲሆን፣ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ያቀረቡት ቅሬታ ተገቢ መሆኑንና ችግሩን እንደሚረዱት ገልጸዋል፡፡ ‹‹ችግሩ በመጪው ሳምንት መጀመሪያ ግፋ ቢል በቀናት ውስጥ ዕልባት ያገኛል፤›› ሲሉ ገልጸው፣ ‹‹የትምህርት ሚኒስቴር ይህን መሰል ችግር ለመቅረፍ መደበኛ የሆነ የከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎች ምደባ የጊዜ ሰሌዳና የመግቢያ መሥፈርቶችን ወደፊት በማውጣት ችግሩን ይቀርፋል፤›› በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡  

 

 

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...