የዘንድሮውን ዒድ አልፈጥርን አስመልክቶ፣ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል የዒድ ኤክስፖ ተከናውኗል፡፡ የ‹‹ከዒድ እስከ ዒድ›› አስተባባሪ ኮሚቴ እንዳስታወቀው ከዒድ እስከ ዒድ ጥሪን ለማስተባበር ከ2500 በላይ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ተሳትፈዋል፡፡ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣርን ጨምሮ መርሐ ግብሩ የኢትዮጵያን መልካም ጎን ለዓለም ለማስተዋወቅ ዕድል ይፈጥራልም ተብሏል፡፡ ፎቶዎቹ የኤክስፖውን ከፊል ገጽታዎች ያሳያሉ፡፡
- ፎቶ መስፍን ሰሎሞን