Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበተመጣጠነ ምግብ ዕጥረት ለተጎዱ የጎዴ ሕፃናት ዕርዳታ ተበረከተ  

በተመጣጠነ ምግብ ዕጥረት ለተጎዱ የጎዴ ሕፃናት ዕርዳታ ተበረከተ  

ቀን:

በሶማሌ ክልል ጎዴ ሆስፒታል እንክብካቤ እየተደረገላቸው ለሚገኙና በተመጣጠነ የምግብ እጥረት ክፉኛ ለተጎዱ ሕፃናት አገልግሎት የሚውሉና የአሜሪካ መንግሥት የላካቸው አስቸኳይ አልሚ ምግቦች ርክክብ ተደረገ፡፡  አስታወቀ፡፡

የአሜሪካ ኤምባሲ ሚያዝያ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳስታወቀው፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ ፈጻሚ አምባሳደር ትራሲ ኦን ጃኮብሰን አልሚ ምግቦች ያስረከቡት ለጎዴ ሆስፒታል ነው፡፡

በአካባቢው በከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለሚሰቃዩ ሕፃናት ዋና የሕክምና ማዕከል ለሆነው ለጎዴ ሆስፒታል አልሚ ምግብን ያስረከቡት አምባሳደር ጃኮብሰን ‹‹ዩናይትድ ስቴትስ፣ በሁሉም በድርቅ ለተጠቁ ክልሎች ከ343 ሺሕ በላይ ለሆኑ ተጋላጭ ሴቶችና ሕፃናት የሕይወት አድን ሥራን በገንዘብ በመደገፏ ኩራት ይሰማታል፤›› ብለዋል።

አምባሳደሯ ከርክክቡ ቀደም ብሎ ጎዴ የሚገኘው የዓለም የምግብ ፕሮግራም መጋዘንን ጎብኝተዋል፡፡ መጋዘኑ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የድርቅ ተጠቂዎች ዕርዳታውን የሚያደርሰው በ910 ማደያ ጣቢያዎቹ አማካይነት መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከመግለጫው ለመረዳት እንደተቻለው፣ አምባሳደር ጃኮብሰን ከሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ መሐመድ ጋር የተነጋገሩ ሲሆን፣ ዩኤስ የሶማሌ ክልልን ጨምሮ በድርቅ በተጎዱ ክልሎች ላሉ ኢትዮጵያውያን የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ቃል ገብተዋል። በኢትዮጵያ ከድርቅ ጋር የተያያዘ ሰብአዊ ርዳታ ከሚሰጡት ትልቁ ለጋሽና ከ110 ሚሊዮን ዶላር በላይ መደገፏን አስታውሰዋል፡፡

የተባበሩት መንግሽታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት እስከ እስከ መጪው ሰኔ ወር እንደሚያስፈልግ የገለጸውን የ275 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋውን ክፍተት ለመድፈን ለጋሽ ድርጅቶችና መንግሥት ድጋፍ እንዲያደርጉ አምባሳደር ጃኮብሰን መጠየቃቸውን መግለጫው ገልጿል።

አምባሳደሯ ልዩ ስሙ ሂግሎ በተባለው መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የሚሰጠውን ዕርዳታ ከመመልከታቸውም በላይ ስለፍላጎታቸው ከማኅበረሰቡ ተወካዮችና ከጎሳ መሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...