መራጃዬን ይዤ – ልፈልጠው አስቤ
ልፈረካክሰው – በእሳት ለብልቤ
ቃላቶት – አምክኖ
የቅርብ – ሩቅ ሆኖ
ከውስጤ – አትንኖ
የቀለም ቀንዲሌ – ከውስጤ አምኖ
ቃላት መንኩሰው – ወረቀት አድርጎ ልብሰ ተክህኖ
የእኔው – ጥቁር ድንጋይ
የውስጤ ውስጥ – ዓባይ
በብዕር ልፈልጠው – ልገባ ከውስጡ
እምቢ አለኝ አልቻልኩም – ጨክኜ መፍለጡ
ሳሳሁ – ለመሀሉ
እንዲፈስ – አስኳሉ
ቀልብና ህሊናዬን – አድርጎት በረሃ
በውስጤ ሰውሮት – የቃላቴን ፅዋ
ወሰደብኝ – የቃላቴን ሲሳይ
ቀምቶብኝ – የክህነቴን አዋይ
ከልሎኝ ቋጥኜ – የእኔው ጥቁር ድንጋይ
ዘርይሁን ወልደ ፃዲቅ