Friday, June 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልሰብዓዊ መብቶች ተኮሩ 16ኛው አዲስ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል

ሰብዓዊ መብቶች ተኮሩ 16ኛው አዲስ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል

ቀን:

የዘንድሮ አዲስ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል ‹‹ሰብዓዊ መብቶችና ዓለም አቀፍ ቀውስ›› በሚል መሪ ቃል ለአምስት ቀናት እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡

ኢንሼቲቭ አፍሪካ ለ16ኛ ጊዜ ባዘጋጀው የፊልም ፌስቲቫል ከ15 በላይ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ዘጋቢ ፊልሞች እንደሚቀርቡ ተቋሙ አስታውቋል፡፡

የመክፈቻው ሥነ ሥርዓት ረቡዕ ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም. ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት የሚከናወነው በጣሊያን ባህል ማዕከል በሚቀርበው ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው ‹‹አመንግ ኣስ ውሜን›› ፊልም ሲሆን፣ በሳራ ኖአ በዘንሃርድን የተዘጋጀ ነው፡፡

እስከ ግንቦት 21 ቀን ድረስ የሚዘልቀው ፌስቲቫሉ፣ ዘጋቢ ፊልሞቹ ከጣሊያን ባህል ማዕከል በተጨማሪ፣ በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴዝና በሀገር ፍቅር ቴአትር ይቀርባሉ፡፡ መዝጊያው እንደ መክፈቻው ሁሉ በጣሊያን ባህል ማዕከል ይሆናል፡፡

በፌስቲቫሉ ስለሚታዩ ፊልሞች እንዲሁም የፊልም ዝግጅትና ሥራን አስመልክቶ ውይይት እንደሚደረግ፣ በተለይም ከጀርመን ከመጣው ‹‹ሪፍት ፊንፊኔ›› (ሪፍት አዲስ አበባ) ፊልም ዳይሬክተር ዳንኤል ኮተር፣ ከኖርዌይ ከመጡት የ‹‹ሰርያን አቴስ›› ዳይሬክተር ኔፊሴ አዝካልና የ‹‹አመንግ ኣስ ውሜን›› (በኛ በሴቶች መካከል) ዳይሬክተር ሳራ ኖኣ ቦዘንሃርድ ጋር የቀጥታ ጥያቄና መልስ መድረክ እንደሚዘጋጅ ኢንሼቲቭ አፍሪካ አስታውቋል፡፡

አንጋፋና ወጣት ኢትዮጵያውያን ፊልም ሠሪዎችም በውይይቱ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡

የዘጋቢ ፊልሞቹ ዓላማ ወቅታዊው ዓለም አቀፋዊ ጉዳይ በሰብዓዊ መብቶች ላይ ያለውን ተፅዕኖ ለማሳየት ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የአዲስ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል በ1999 ዓ.ም. በአቶ ክቡር ገና የተመሠረተ ሲሆን፣ በ15 የተለያዩ መሰናዶዎቹ በአገር ውስጥና በውጭ አገር የተሠሩ በርካታ ዘጋቢ ፊልሞችን ማስተናገዱ ይታወሳል፡፡

ቀደም ባሉት ዓመታት ፌስቲቫሉ ከዳሰሳቸው ጭብጦች መካከል የአካባቢ ጥበቃ፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ የሥነ ፆታ ጉዳይና ሌሎችም ማኅበራዊ ጉዳዮች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ፌስቲቫሉ የፊልም ባለሙያዎችን ከተለያዩ አኅጉሮች በመጋበዝና መድረክ በማመቻቸት የሚታወቅ ሲሆን፣ ተሳታፊ አገሮቹ የሚገኙበትን ነባራዊ ሁኔታ የሚያንፀባርቁ ፊልሞችን ለታዳሚዎች በማሳየትም ተጠቃሽ ነው፡፡

የዓምናው ፌቲቫል በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የተካሄደው የታዳሚዎችን ቁጥር በመቀነስ እንደነበርም አይዘነጋም፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ