የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) የተቋማቸውን የአሥር ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት የተናገሩት፡፡ ሚኒስትሩ አያይዘውም ንዝህላልነቱ የንግድ ሚኒስቴርም የኛም ነው በማለት አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ በስሚንቶ ላይ እንደሚታየው የንግድ ሰንሰለቱ የተወሳሰበ ነው ያሉት ሚኒስትሩ 35 ሚሊዮን ቶን ጨው ከአፍዴራ ሐይቅ ጎን ቁጭ ብሎ ሰው ከውጭ የሚያስገባበት ሞራል የለውም ሲሉ አሳስበዋል፡፡