Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለድንገተኛ የትራፊክ አደጋ ሕክምና ውይይት እየተደረገ ነው

ለድንገተኛ የትራፊክ አደጋ ሕክምና ውይይት እየተደረገ ነው

ቀን:

በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የተዘጋጀው የመንገድ ደኅንነትና መድንን ፈንድ አገልግሎት ደንብ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቀ በኋላ፣ ለድንገተኛ አደጋ ሕክምና ይከፈል የነበረው 2,000 ብር በቂ ባለመሆኑ ጭማሪ ለማድረግ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡

ከመንገድ ፈንድ ክፍያ ውስጥ ለድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት ይከፈል የነበረው የተተመነ ክፍያ የሕክምና ወጪ በመጨመሩ ምክንያት፣ ጥናት ተደርጎ በቂ አይደለም ተብሏል፡፡

በዚህም ምክንያት የአካል ጉዳት ለደረሰባቸውና ለሞት አደጋ የካሳ ክፍያ ለማሻሻል ውይይት እየተደረገ ነው፡፡

በመንገድ ፈንድ ማሻሻያው መሠረትም ከእዚህ በፊት ለማንኛውም ድኅረ ድንገተኛ ሕክምና አገልግሎት የተተመነ ወጪ 2,000 ብር ነበር፡፡ ክፍያው ሲሻሻል የሕክምና ወጪው ቢያንስ አምስት በመቶ ክፍያ እንደሚሆን፣ እንዲሁም የሞት አደጋ ለደረሰባቸው ተጎጂዎች የካሳ ማሻሻያ እንደሚደረግበት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ታጠቅ ነጋሽ ተናግረዋል፡፡

ይህም ዕርምጃ ከመንገድ ደኅንነት ጋር በተያዘ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ ተጨማሪ ፋይናንስ ለማግኘት ይረዳል ብለዋል፡፡

በተሽከርካሪ አደጋ ለተጎዱ ሰዎች ድንገተኛ ሕክምና መስጠት የሚቻለው እስከ ሁለት ሺሕ ብር ብቻ በመሆኑ፣ አሁን ካለው የሕክምና ወጪ ጋር ተመጣጣኝ አለመሆኑ በጥናት መረጋገጡን አስረድተዋል፡፡

ለተለያዩ ምርመራዎች፣ ለመድኃኒቶችና ለሌሎች የድንገተኛ ሕክምና አገልግሎቶች የሚያስፈልገው ወጪ ከፍተኛ በመሆኑ፣ ክፍያው ማሻሻያ እንዲደረግበት እየተሠራ ነው ሲሉ አቶ ታጠቅ ጠቁመዋል።

በማንኛውም ዓይነት የትራፊክ አደጋ ሰለባ ለሚሆኑ ተጎጂዎች እስከ ሁለት ሺሕ ብር ድረስ የሕክምና አገልግሎት በነፃ ማግኘት የሚያስችል መመርያ መውጣቱ  ይታወሳል፡፡

በመመርያው መሠረት አገልግሎቱ የሚሰጠው ጉዳቱ የደረሰው በትራፊክ አደጋ መሆኑ በፖሊስ ሲረጋገጥ፣ የሕክምና ተቋማቱም ከሚመለከታቸው አካላት ሕጋዊ ማስረጃ ሲያገኙ ብቻ ነው።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም. የአሥር ወራት አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ የመንገድ ደኅንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ማቋቋሚያ ደንብ፣ የተሽከርካሪዎች ክብደትና ልክ መወሰኛና መቆጣጠሪያ ደንብ፣ የባለሞተር ተሽከርካሪዎች ፍጥነት ወሰን ደንብ፣ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት እንደ ገና ማቋቋሚያ ደንብና የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ደንብ ፀድቀው ወደ ተግባር ገብተዋል፡፡

ከፀደቁት ደንቦች አንዱ የመንገድ ደኅንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ደንብ ሲሆን፣ ሁለት የተለያዩ ተግባራት የነበራቸው ማለትም የመንገድ ደኅንነትና የመድን ፈንድ በጋራ ሆነው ውጤታማ ሥራ የሚያከናውኑበት አደረጃጀት ነው፡፡

የመንገድ ደኅንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ተበታትነው የነበሩ የተለያዩ የትራንስፖርት መዋቅሮች ተቀናጅተው እንዲሠሩ የሚያስችል መሆኑን፣ ሁለቱ ተቋማት በጋራ የሚያከናውኑት ተመሳሳይ ተግባር ቢኖራቸውም ቀድሞ የነበሯቸውን ሥራዎች እንደሚቀጥሉ አቶ ታጠቅ ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...