Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየመድኃኒት አስመጪ ወኪሎች ብዛት ገደብ ቢነሳም በአዲሱ አሠራር እየተገለገሉ አይደለም

የመድኃኒት አስመጪ ወኪሎች ብዛት ገደብ ቢነሳም በአዲሱ አሠራር እየተገለገሉ አይደለም

ቀን:

የመድኃኒት አስመጪ ወኪሎች ሦስት ብቻ እንዲሆኑ የሚያስገድደው አሠራር ቢነሳም፣ በርካታ አስመጪዎች በአዲሱ አሠራር እየተገለገሉ አለመሆኑን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ገለጸ።

መድኃኒቶችን ከውጭ አምራች ድርጅቶች ማስመጣት የሚችሉ ወኪሎች ሦስት ብቻ እንዲሆኑ የሚያስገድድ አሠራር የነበረ መሆኑን፣ ከወራት በፊት ግን የወኪሎቹ ቁጥር ከሦስት በላይ እንዲሆን መወሰኑን በምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የመድኃኒት ምዝገባና ፈቃድ ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ በየነ ለሪፖርተር ገልጸዋል።

ከዚህ በፊት በነበረው አሠራር ከውጭ አምራቾች መድኃኒቶችን ለማስመጣት አንድ ዋና ወኪል ብቻ እንደሚኖር፣ ሌሎች ሁለት ወኪሎች ደግሞ ከዋናው ወኪል ገዝተው ማከፋፈል የሚችሉበት ነበር ብለዋል። በዚህም መሠረት ዋናው ወኪል ፈቃድ ያላገኘበትን መድኃኒት ሌሎችም ወኪሎች መሸጥ እንዳይችሉ አድርጓቸው መቆየቱን አስረድተዋል።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በአዲሱ አሠራር መሠረት አንድ አምራች ቁጥራቸው ያልተወሰነ ወኪሎች እንዲኖሩት ይፈቀዳል ያሉት አቶ ሀብታሙ፣ ሁሉም ወኪሎች ዋና ወኪል ሳይኖርባቸው መድኃኒቶችን የማስመጣት ፈቃድ ማግኘት እንደሚችሉ ተናግረዋል። ከዚህ በፊት ዋናው ወኪል ያልፈለጋቸውን መድኃኒቶች ሌሎችም ማስመጣት አለመቻላቸው ዘርፉን ገበያ ተኮር ብቻ አድርጎት ቆይቷል ብለዋል። አሁን ግን አሠራሩ ቢቀየርም አስመጪዎች እየተጠቀሙበት እንዳልሆነና በነበረው አካሄድ መቀጠላቸውን ገልጸዋል።

የወኪሎች ቁጥር ከሦስት ከፍ መደረጉና ሁሉም ወኪሎች ማስመጣት መቻላቸው፣ በተለይም በመድኃኒት ዘርፉ እየተፈጠረ ያለውን እጥረት ለመቅረፍ እንደሚያግዝ አቶ ሀብታሙ ተናግረዋል። መድኃኒቶቹ ለትርፍ ብቻ ሳይሆን ለኅብረተሰቡ ከሚሰጡት ጥቅም አንፃር አይተው ለሚያስመጡ ወኪሎችም ዕድል እንደሚሰጥ አክለዋል።

ኢትዮጵያ በ2013 በጀት ዓመት 26.6 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን መድኃኒቶችና የሕክምና ቁሳቁሶችን ከውጭ አስገብታለች። ይህም ከቀደመው ዓመት በአምስት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ገደማ የሚበልጥ ሲሆን፣ ዋጋውም ከሦስት ቢሊዮን ዶላር ወደ 4.4 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ያለ ነው። ከአጠቃላይ አገራዊ ፍጆታው ውስጥ በአገር ውስጥ የሚመረተው ከአምስት በመቶ በላይ እንደማይበልጥና የአገር ውስጥ አምራቾች ከሚጠቀሙት ግብዓት ውስጥ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነውን ከውጭ እንደሚያስመጡ አምራቾች ይገልጻሉ። ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነው መድኃኒትና የሕክምና ግብዓትም ከውጭ የሚመጣ ነው።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...