Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበመጪው ክረምት ከባድ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል ተተነበዬ

በመጪው ክረምት ከባድ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል ተተነበዬ

ቀን:

የኢትዮጵያ ሜትሪዮሎጂ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የዝናብ ሁኔታ በክረምት ወራት እንደሚታይ ተነበዬ፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች የክረምቱ አገባብ እንደሚዘገይ፣ በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ የክረምቱ አወጣጥ የዘገየ ሊሆን እንደሚችል የኢንስቲትዩቱ ትንበያ ያመላክታል፡፡ በሚያዝያና ግንቦት እየተመዘገበ ያለውን ከፍተኛ የሙቀት ሁኔታ በተመለከተ፣ እጅግ ከፍተኛ ሆኗል ለማለት ከዚህ ቀደም ከተመዘገቡ መጠኖች ጋር ማነፃፀር እንደሚያስፈልግም ኢንስቲትዩቱ ተናግሯል፡፡

በዘንድሮው ክረምት የአየር ጠባይ ሁኔታ ላይ አዎንታዊና አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ዓለም አቀፋዊና ቀጣናዊ የአየር ሁኔታዎችን ሲገመግም መቆየቱን ኢንስቲትዩቱ ተናግሯል፡፡ በኢንስቲትዩቱ የትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዳይሬክተር ጫሊ ደበሊ እንደተናገሩት፣ መጪው ክረምት ከበድ ያለ ዝናብ የሚታይበት እንደሚሆን በግምገማ ተረጋግጧል፡፡

‹‹የሰላማዊ ውቅያኖስ ምሥራቅና ማዕከላዊ ክፍሉ ከመደበኛ በላይ ወይም በታች መሞቅና መቀዝቀዝ በኢትዮጵያ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ ዘንድሮ የዚህ ውቂያኖስ ምሥራቅና መካከለኛ ክፍሉ በመቀዝቀዙ በበልግ ወቅት የነበረውን የዝናብ ሽፋን ቀንሶበታል፡፡ ይህ ደግሞ በክረምት ወቅት በተቃራኒው የዝናቡን ሁኔታ ይጨምረዋል ተብሎ ይገመታል፤›› በማለት ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

በሌላም በኩል ለኢትዮጵያ የእርጥበት ምንጭ የሆኑ የደቡብ ህንድና የደቡብ አትላንቲክ ውቂያኖሶችን አየር ሁኔታም ኢንስቲትዩቱ መገምገሙን ዳይሬክተሯ ይጠቅሳሉ፡፡ በዚህም በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍሎች የተጠናከረ የዝናብ መጠን ሊያገኙ እንደሚችሉ መተንበይ መቻሉን አመልክተዋል፡፡

‹‹ሐምሌና ነሐሴ ከባድ ዝናብ በብዙ አካባቢዎች ሊፈጠር ይችላል፡፡ ጭጋጋማ  የአየር ጠባይ፣ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት የመሳሰሉ ችግሮች ሊከሰቱ ይችላሉ፤›› ሲሉ የገለጹት ባለሙያዋ፣ ቅድመ ጥንቃቄ ከወዲሁ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

በቅርብ ሰሞን በተለይ በሚያዝያና ግንቦት ወራቶች እየታየ ስላለው የሙቀት ጭማሪ ማብራሪያ የሰጡት ዳይሬክተሯ፣ ከመደበኛው የተለየ ስለመሆኑ ማጥናት ይጠይቃል ብለዋል፡፡

እ.ኤ.አ. ግንቦት 15 በድሬዳዋ 40.1 ዲግሪ ሴሊሺየስ ሙቀት ታይቷል ያሉት ባለሙያዋ በጎዴ፣ ቀብሪደሃር፣ ሰመራ፣ ሁመራ፣ ማንኩሽና ጋምቤላ በመሳሰሉ አካባቢዎች ግን በተደጋጋሚ ከ40 በላይ መመዝገቡን አመልክተዋል፡፡ በሞቃትና ቆላማ የኢትዮጵያ ክፍሎች በበልግ ወራት ሙቀት መጨመሩ የሚጠበቅ መሆኑን በማመልከትም ‹‹የዘንድሮውን ከፍተኛ ነው ለማለት ካለፉ ወቅቶች ጋር ማነጻጸር ያስፈልጋል፤›› ብለዋል፡፡

የአፍሪካ መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ፓናል ከሰሞኑ ባወጣው አኅጉራዊ ትንበያ ከባድ የክረምት ወቅት አገሮች ያስተናግዳሉ ብሏል፡፡ በተለይ ኢትዮጵያን ጨምሮ የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ከዚህ ቀደም ክረምት 40 ከመቶ የጨመረ ዝናብ ያገኛሉ ብሏል፡፡ የአፍሪካ አገሮች ከባድ ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ እንዲጠበቁ ፓናሉ በትንበያው አስጠንቅቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...