Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናተፎካካሪ ፓርቲዎች በሕግ ማስከበር ስም አባሎቻችን እየታፈኑ ነው አሉ

ተፎካካሪ ፓርቲዎች በሕግ ማስከበር ስም አባሎቻችን እየታፈኑ ነው አሉ

ቀን:

መንግሥት ከሰሞኑ በከፈተው የሕግ ማስከበር ዘመቻ አባሎቻቸውና አመራሮቻቸው ያለአግባብ እየታሰሩ መሆኑን ተፎካካሪ ፓርቲዎች ገለጹ፡፡ በሕግ ማስከበር ሰበብ መንግሥት ተቃዋሚዎችን ማዳከሙን እንዲያቆም ጠይቀዋል፡፡

በሕግ ማስከበር ዕርምጃው ግለሰቦች በጅምላ መታሰራቸውን፣ አንዳንዶችም የገቡበት አለመታወቁ አሳሳቢ ነው ሲሉ ፓርቲዎቹ አስታውቀዋል፡፡

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌጥዬ ያለው፣ ‹‹የወል እስራትና ሕገ መንግሥታዊ አፈና እየተፈጸመ ነው፤›› በማለት የመንግሥትን ዕርምጃን ወቅሰዋል፡፡ ‹‹አንዳንድ ዜጎች ለእስራትም፣ ለክስም ሆነ ለፍርድ የሚያበቃ ጥፋት ሳይኖርባቸው ነው የሚታፈሱት፡፡ አሁን መንግሥት ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር በማሰብ ጠረጠርኩ እያለ ግለሰቦችን እያሰረ ነው፡፡ በአብዛኛው የዘመቻ እስሩ የሚካሄደው ተጨባጭ ፍንጭ በመያዝ ሳይሆን አስበሃል በሚል ነው፤›› ሲሉ አቶ ጌጥዬ አስረድተዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

እስካሁን 12 አባሎቻቸው እንደታሰሩባቸው የተናገሩት አቶ ጌጥዬ፣ በሌሎች ላይም ዘመቻ ለመክፈት መንግሥት እንደተዘጋጀ ፓርቲያቸው መረጃ እንደ ደረሰው ጠቁመዋል፡፡ በቅርቡ የካራማራ ድል በዓልን ለማክበር በተዘጋጁ 40 አባሎቻቸው ላይ እስራት እንደተፈጸመ ተናግረው፣ ይህ ዕርምጃ  መቀጠሉን ገልጸዋል፡፡ ‹‹እኔንም ጭምር እንደሚፈልጉኝ መረጃ አግኝቻለሁ፤›› ያሉት አቶ ጌጥዬ፣ መንግሥት ሕግ በማስከበር ስም ተቃዋሚዎችን ያሳድዳል ብለዋል፡፡

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ደሳለኝ በበኩላቸው፣ ‹‹በሕግ ማስከበር ስም ሕግ ያልተከተለ ዕርምጃ እየተወሰደ ነው፤›› ብለዋል፡፡ የእነሱን ጨምሮ የሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላት እየታሰሩ መሆኑን የተናገሩት አቶ ስንታየሁ፣ ‹‹የወረዳና የዞን አመራሮች ሳይቀሩ እየታሰሩ የማይታወቅ አካባቢ ይወሰዳሉ፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

‹‹በወንጀል የተጠረጠረ ሁሉ ወንጀለኛ ነው ተብሎ አይታሰብም፡፡ ወንጀል መፈጸሙ በሕግ የተረጋገጠበት ዕርምጃ ቢወስድበት እንደግፋለን፡፡ ከዚህ ውጪ በየቦታው በጅምላ ዜጎችን ማፈስ ግን ሕዝብን ለአመፅ እንዲነሳሳ የሚገፋፋ ዕርምጃ ነው፤›› በማለት አቶ ስንታየሁ የመኢአድን አቋም ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የመንግሥትን የሕግ ማስከበር ዕርምጃ የሚቃወም ጠንካራ መግለጫ ያወጣው እናት ፓርቲ፣ ‹‹በቀጠለው መንግሥታዊ የአፈና ዕርምጃ የተነሳ አመራሮቻችን የገቡበት አልታወቀም፤›› ብሏል፡፡ በወላይታ፣ በሰቆጣ፣ በአዊና በሞጣ አካባቢዎች የሚገኙ አመራሮቹ መያዛቸውን ፓርቲው አስታውቋል፡፡ ‹‹መንግሥት ልክ እንደ አሸባሪ ድርጅት ዜጎችን ማሰርና መሰወሩን ያቁም፤›› በማለትም በመግለጫው ጠይቋል፡፡

ይህን የፖለቲካ ፓርቲዎችን አባሎቻችን ታፈኑ የሚል ስሞታን በተመለከተ ማብራሪያ ለመጠየቅ ለመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ቢደረግም፣ ምላሽ ለማግኘት ግን አልተቻለም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...